ጥር 7, 2021
ፊጂ
ያሳ የተባለው ኃይለኛ አውሎ ነፋስ ፊጂን መታ
ቦታ
ፊጂ
የደረሰው አደጋ
ያሳ የተባለውና አምስተኛ እርከን የተሰጠው ኃይለኛ አውሎ ነፋስ ከፊጂ ደሴቶች በትልቅነቷ ሁለተኛ የሆነችውን ቫኑዋ ሌቩን ሐሙስ፣ ታኅሣሥ 17, 2020 መታ
ያሳ፣ ፊጂን እንደመቷት ከተመዘገቡት አውሎ ነፋሶች በኃይለኝነቱ ሁለተኛውን ደረጃ ይዟል። ነፋሱ በሰዓት 260 ኪሎ ሜትር የሚደርስ ፍጥነት ነበረው
አደጋው በደረሰበት አካባቢ ቢያንስ 30 ጉባኤዎችና ገለልተኛ ቡድኖች አሉ
በወንድሞቻችንና በእህቶቻችን ላይ የደረሰ ጉዳት
ከወንድሞቻችንና ከእህቶቻችን አንዳቸውም ጉዳት አልደረሰባቸውም
የመጀመሪያዎቹ ሪፖርቶች እንደሚያሳዩት 20 ቤተሰቦች ከመኖሪያቸው ተፈናቅለዋል
አውሎ ነፋሱ በሰብል ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል፤ በአካባቢው የሚኖሩ 430 አስፋፊዎች ዋነኛ ምግባቸው ወድሞባቸዋል
በንብረት ላይ የደረሰ ጉዳት
10 ቤቶች ፈርሰዋል
25 ቤቶች ጉዳት ደርሶባቸዋል
1 የስብሰባ አዳራሽ ቀላል ጉዳት ደርሶበታል
የእርዳታ እንቅስቃሴ
የፊጂ ቅርንጫፍ ቢሮ ሦስት የአደጋ ጊዜ እርዳታ አስተባባሪ ኮሚቴዎችን አቋቁሟል። እነዚህ ኮሚቴዎች እንደ ንጹሕ የመጠጥ ውኃ፣ ልብስ፣ ምግብና የፕላስቲክ ድንኳን ያሉ መሠረታዊ ነገሮችን በአደጋው ለተጎዱ አስፋፊዎች አከፋፍለዋል። በተጨማሪም በአደጋው ምክንያት የተፈናቀሉትን አስፋፊዎች ጊዜያዊ ማረፊያ እንዲያገኙ ረድተዋቸዋል
ከፊጂ ቅርንጫፍ ቢሮ የተላኩ ወንድሞችና በአካባቢው ያሉ የወረዳ የበላይ ተመልካቾች በአደጋው ለተጎዱት እረኝነት እያደረጉ ነው
በእርዳታ ሥራዎችና በእረኝነት ጉብኝት የተካፈሉት ሁሉ ይህን እያደረጉ ያሉት ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ ጋር በተያያዘ የወጡትን የደህንነት ደንቦች ባገናዘበ መልኩ ነው
ወንድሞቻችንና እህቶቻችን በዚህ ኃይለኛ አውሎ ነፋስ የተነሳ ያጡት ነገር ቢኖርም በመዝሙር 46:1 ላይ የሚገኘውን “አምላክ መጠጊያችን . . . ነው” የሚለውን ሐሳብ እውነተኝነት እየተመለከቱ ነው።