ሚያዝያ 12, 2023
ፔሩ
ያኩ የተባለ ኃይለኛ አውሎ ነፋስ ፔሩን መታ
መጋቢት 2023 መጀመሪያ አካባቢ፣ ያኩ የተባለው ኃይለኛ አውሎ ነፋስ የፔሩን ሰሜናዊ የባሕር ዳርቻ መታ። አካባቢው በጎርፍ የተጥለቀለቀ ሲሆን የመሬት መንሸራተትም ተከስቷል፤ ከሁለት ቀናት በኋላ በአገሪቱ ሰሜናዊና ማዕከላዊ ክልሎች የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ታውጇል። ጎርፉ ቤቶችን፣ ድልድዮችንና አውራ ጎዳናዎችን አፈራርሷል፤ ይህም ሰዎችን ከአካባቢው ለማስወጣት የሚደረገውን ጥረት አስተጓጉሎታል።
በወንድሞቻችንና በእህቶቻችን ላይ የደረሰ ጉዳት
በአደጋው የሞተ የይሖዋ ምሥክር የለም
2 አስፋፊዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል
106 አስፋፊዎች ከመኖሪያቸው ተፈናቅለዋል
70 መኖሪያ ቤቶች ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል
130 መኖሪያ ቤቶች ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል
5 የስብሰባ አዳራሾች ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል
5 የስብሰባ አዳራሾች ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል
የእርዳታ እንቅስቃሴ
የወረዳ የበላይ ተመልካቾችና የጉባኤ ሽማግሌዎች፣ ጉዳት በደረሰባቸው አካባቢዎች ለሚኖሩት ወንድሞች መንፈሳዊ ማበረታቻና ተግባራዊ እገዛ እየሰጡ ነው
የእርዳታ ሥራውን ለማስተባበር 3 የአደጋ ጊዜ እርዳታ አስተባባሪ ኮሚቴዎች ተቋቁመዋል
በፔሩ ያሉ ወንድሞቻችን “በትዕግሥትና በደስታ ሁሉንም ነገር በጽናት [እንዲቋቋሙ]” ይሖዋ እንደሚረዳቸው እንተማመናለን።—ቆላስይስ 1:11