በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

የሕይወት ክህሎቶች

አዋቂ ስትሆን የሚጠቅሙህ ወሳኝ ክህሎቶችና ባሕርያት አሉ፤ እነዚህን ከአሁኑ ተማር!

ስሜትን መቆጣጠር

ስሜቴን መቆጣጠር የምችለው እንዴት ነው?

የስሜት መለዋወጥ የተለመደ ነገር ቢሆንም ብዙ ወጣቶች እንዲህ ያለ ሁኔታ ሲያጋጥማቸው ግራ ይጋባሉ። ደስ የሚለው ግን እነዚህን ስሜቶች መረዳት አልፎ ተርፎም መቆጣጠር ትችላለህ።

አሉታዊ ስሜቶችን መቆጣጠር

ይህ የመልመጃ ሣጥን የተዘጋጀው የስሜት መለዋወጥ ሲያጋጥምህ ችግሩን መቋቋም እንድትችል ለመርዳት ነው

ሐዘንን አሸንፎ ደስተኛ መሆን

ከባድ ሐዘን የሚሰማህ ከሆነ ምን ማድረግ ትችላለህ?

አሉታዊ አመለካከትን ማስወገድ የምችለው እንዴት ነው?

እነዚህ ሐሳቦች አዎንታዊ አመለካከት ለማዳበር ይረዱሃል።

ቁጣዬን መቆጣጠር የምችለው እንዴት ነው?

የሚያበሳጭ ነገር ሲያጋጥምህ ቁጣህን ለመቆጣጠር ሊረዱህ የሚችሉ አምስት ጥቅሶች።

ቁጣን መቆጣጠር የሚቻልበት መንገድ

ቁጣን ለመቆጣጠር የሚረዱ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሠረቱ አምስት ምክሮች።

ጭንቀትን መቋቋም የምችለው እንዴት ነው?

የሚሰማህ ጭንቀት እንዲጎዳህ ሳይሆን እንዲጠቅምህ የሚያደርጉ ስድስት ነጥቦች።

ሐዘንን መቋቋም የምችለው እንዴት ነው?

ከከባድ ሐዘን ለማገገም ጊዜ ይወስዳል። በዚህ ርዕስ ውስጥ የተሰጡትን ሐሳቦች ልብ በል፤ ምናልባት አንዳንዶቹ ለአንተም ይጠቅሙህ ይሆናል።

የደረሰብኝን አሳዛኝ ሁኔታ መቋቋም የምችለው እንዴት ነው?

እንዲህ ዓይነት ሁኔታ ያጋጠማቸው ወጣቶች ችግሩን እንዲቋቋሙ ምን እንደረዳቸው ተናግረዋል።

ፈታኝ ሁኔታዎችን መቋቋም የምችለው እንዴት ነው?

ተገቢ ያልሆኑ ምኞቶችን ለመቆጣጠር ልትወስዳቸው የምትችላቸውን ሦስት እርምጃዎች አንብብ።

ፈታኝ ስሜቶችን መቋቋም የሚቻልበት መንገድ

ሰዎች ከፈለጉ ፈታኝ የሆኑ ስሜቶችን ማሸነፍ ይችላሉ። ሁልጊዜ ትክክለኛ የሆነውን ለማድረግ ያለህን ቁርጠኝነት ለማጠናከር እንዲሁም በፈተና እንዳትሸነፍ የሚረዱህን ስድስት ምክሮች ተመልከት።

ጊዜ እና ገንዘብ

ጊዜዬን በአግባቡ መጠቀም የምችለው እንዴት ነው?

ውድ የሆነውን ጊዜህን እንዳታባክን ሊረዱህ የሚችሉ አምስት ጠቃሚ ነጥቦች።

ኃይሌ እንዳይሟጠጥና እንዳልዝል ምን ሊረዳኝ ይችላል?

አንድን ሰው ኃይሉ እንዲሟጠጥና እንዲዝል የሚያደርገው ምን ሊሆን ይችላል? ይህ ሁኔታ አንተንስ ያሰጋሃል? ከሆነ ምን ልታደርግ ትችላለህ?

ዛሬ ነገ የማለት ልማዴን ማስተካከል የምችለው እንዴት ነው?

ዛሬ ነገ የማለት ልማድህን ለማስተካከል የሚረዱ ጠቃሚ ምክሮችን ተመልከት!

ወጣቶች፣ ዛሬ ነገ ስለ ማለት ምን ይላሉ?

ዛሬ ነገ ማለት ስለሚያስከትላቸው ጉዳቶችና ጊዜን በአግባቡ መጠቀም ስላሉት ጥቅሞች አንዳንድ ወጣቶች የተናገሩትን እንድትመለከት እንጋብዝሃለን።

ወጣቶች ስለ ገንዘብ የሰጡት ሐሳብ

ገንዘብን መቆጠብ፣ በአግባቡ መጠቀም እንዲሁም ለገንዘብ ተገቢ አመለካከት መያዝ የሚቻለው እንዴት እንደሆነ ተመልከት

ወጪዎቼን መቆጣጠር የምችለው እንዴት ነው?

ገበያ ወጥተህ ያላሰብከውን ውድ ዕቃ ገዝተህ ተመልሰህ ታውቃለህ? ከሆነ ይህን ርዕስ ማንበብህ በጣም ይጠቅምሃል።

የገንዘብ አያያዝ

የሚያስፈልጉህን እና የምትፈልጋቸውን ነገሮች በሚገባ ካመዛዝንክ በኋላ ሁለቱንም ግምት ውስጥ ያስገባ በጀት ለማውጣት እንድትችል ይህን የመልመጃ ሣጥን ተጠቀም።

የገንዘብ አያያዝ

የገንዘብ አያያዝ ከተማርክ ሲያስፈልግህ ገንዘብ አታጣም!

ስብዕና ግንባታ

ስህተት ስሠራ ምን ማድረግ ይኖርብኛል?

የማይሳሳት ሰው የለም፤ ከስህተቱ የሚማረው ግን ሁሉም ሰው አይደለም።

ከስህተት መማር

ይህ የመልመጃ ሣጥን ከስህተትህ መማር እንድትችል ይረዳሃል።

እርማት ሲሰጠኝ ምን ላድርግ?

አንዳንድ ሰዎች ትንሽ እርማት ሲሰጣቸው ቅስማቸው ወዲያው ይሰበራል። አንተስ እንዲህ ዓይነት ባሕርይ አለህ?

የሚሰጥህን እርማት እንዴት ልትቀበል ይገባል?

ስሜትህን እንደጎዳ የተሰማህ ምክር ወይም እርማት እንዲያውም በጣም ጠቃሚ ሊሆን ይችላል፤ እንዴት?

ሐቀኝነት ያዋጣል?

ስኬታማ ለመሆን የግድ መዋሸት ያስፈልግሃል? ሐቀኛ መሆን ምን ጥቅም እንዳለው እንድትመለከት እንጋብዝሃለን።

ሐቀኛ መሆን ለምን አስፈለገ?

ሐቀኛ ያልሆኑ ሰዎች ይጠቀሙ የለ?

ምን ያህል ሐቀኛ ነህ?

ይህን ባለሦስት ክፍል መልመጃ በመጠቀም ራስህን መርምር።

ለውጥን ማስተናገድ የሚቻለው እንዴት ነው?

ለውጥ የማይቀር ነገር ነው። አንዳንዶች ያጋጠማቸውን ለውጥ ለማስተናገድ ምን እንዳደረጉ እንድታነብ እንጋብዝሃለን።

ኃላፊነት የሚሰማው ሰው ነኝ?

አንዳንድ ወጣቶች ከሌሎች የበለጠ ነፃነት ይሰጣቸዋል። ለምን?

መንፈሰ ጠንካራ ነኝ?

ችግር ማጋጠሙ አይቀርም፤ ያጋጠመህ ችግር ቀላልም ሆነ ከባድ የመንፈስ ጥንካሬ ማዳበር ያስፈልግሃል።

ትኩረቴን መሰብሰብ የምችለው እንዴት ነው?

ቴክኖሎጂ ትኩረት መሰብሰብ ከባድ እንዲሆንብን የሚያደርግባቸውን ሦስት ሁኔታዎችና መፍትሔውን እንመልከት።

አዲስ ቋንቋ መማር ጠቃሚ የሆነው ለምንድን ነው?

ምን ተፈታታኝ ሁኔታዎች አሉት? ምን ጥቅሞችስ ያስገኛል?

ቋንቋ ለመማር የሚረዱ ሐሳቦች

አዲስ ቋንቋ መማር ልምምድ፣ ጊዜና ጥረት ይጠይቃል። ይህ የመልመጃ ሣጥን አዲስ ቋንቋ ለመማር የሚስችል ጥሩ ዕቅድ ለማውጣት ይረዳሃል።

ራሴን ችዬ ለመኖር ደርሻለሁ?

እንዲህ ያለውን ትልቅ ውሳኔ ከማድረግህ በፊት የትኞቹን ነገሮች ከግምት ማስገባት ይኖርብሃል?

ወደ ቤተሰቦችህ መመለስ ሲኖርብህ

ከቤት ወጥተህ ራስህን ችለህ መኖር ከጀመርክ በኋላ ኑሮ ከብዶሃል? በዚህ ርዕስ ውስጥ የቀረቡት ሐሳቦች እንደገና ራስህን ችለህ እንድትኖር ሊረዱህ ይችላሉ።

ማኅበራዊ ኑሮ

ዓይናፋርነትን ማሸነፍ የምችለው እንዴት ነው?

ጥሩ ወዳጅነት መመሥረትና አስደሳች ጊዜ ማሳለፍ የምትችልበት አጋጣሚ እንዲያልፍህ አትፍቀድ።

ሌሎች ጓደኛቸው ሊያደርጉኝ ባይፈልጉ ምን ላድርግ?

ትልቅ ቦታ የምትሰጠው ነገር ምንድን ነው? ጥሩ አቋም በሌላቸው ሰዎች መወደድ ወይስ ራስህን መሆን?

ከሰዎች ጋር የመጨዋወት ችሎታዬን ማሻሻል የምችለው እንዴት ነው?

ጭውውት ለመጀመርና ለማስቀጠል የሚረዷችሁ ሦስት ምክሮች።

መልካም ምግባር ማሳየት አስፈላጊ ነው?

ጊዜ ያለፈበት ነገር ነው? ወይስ ዛሬም አስፈላጊ ነው?

የማልፈልገውን ነገር የምናገረው ለምንድን ነው?

ከመናገርህ በፊት ቆም ብለህ እንድታስብ የሚረዳህ የትኛው ምክር ነው?

ይቅርታ መጠየቅ ያለብኝ ለምንድን ነው?

ጥፋቱ የአንተ ብቻ እንዳልሆነ ቢሰማህም እንኳ ይቅርታ መጠየቅ ያለብህ ለምን እንደሆነ የሚያሳዩ ሦስት ምክንያቶችን ተመልከት።

ሌሎችን መርዳት ያለብኝ ለምንድን ነው?

ለሌሎች ጥሩ ነገር ማድረግ ቢያንስ በሁለት መንገዶች ጥቅም ያስገኝልሃል። እነዚህ ሁለት ጥቅሞች ምንድን ናቸው?

ሌሎችን ለመርዳት ላደርጋቸው ያሰብኳቸው ነገሮች

ለሰዎች እርዳታ ለመስጠት ሩቅ መሄድ አያስፈልግህም። ይህ የመልመጃ ሣጥን በዚህ ረገድ የሚረዱ ሦስት ቀላል እርምጃዎችን ይዟል።

ሰዎች ስለ እኔ የሚያወሩት ለምንድን ነው?

የተሰራጨብህ ሐሜት እንዳይቆጣጠርህ እንዲሁም መልካም ስምህን እንዳያጠፋብህ ማድረግ የምትችለው እንዴት ነው?

ጓደኛዬ ቢበድለኝ ምን ላድርግ?

ሁሉም ጓደኛሞች ችግር እንደሚያጋጥማቸው ማወቅ ይኖርብሃል። ሆኖም ጓደኛህ አንተን የሚጎዳ ነገር ቢናገር አሊያም ቢያደርግ ምን ማድረግ ትችላለህ?

ጉልበተኞች ቢያስቸግሩኝ ምን ላድርግ?

ጉልበተኞች የሚያስቸግሯቸው ብዙ ልጆች ማንም ሊረዳቸው እንደማይችል ይሰማቸዋል። ይህን ሁኔታ ለመቋቋም ምን ማድረግ እንደሚቻል በዚህ ርዕስ ላይ ይብራራል።

የጉልበተኞችን ጥቃት መቋቋም

የጉልበተኛውን ድርጊት መቆጣጠር አትችል ይሆናል፤ አንተ ለዚያ የምትሰጠውን ምላሽ ግን መቆጣጠር ትችላለህ።

ቡጢ ሳትሰነዝር ጉልበተኞችን ማሸነፍ

ጉልበተኞች ጥቃት የሚያደርሱት ለምንድን ነው? ጥቃቱን ማሸነፍ የምትችለው እንዴት ነው?