ወጣቶች የሚጠይቋቸው ጥያቄዎችና ተግባራዊ መሆን የሚችሉ መልሶች፣ ጥራዝ 1
‘ከወላጆቼ ጋር መነጋገር የምችለው እንዴት ነው?’ ‘ጓደኞች ማፍራት የምችለው እንዴት ነው?’ ‘የፍቅር ጓደኝነት ሳይኖር ካገኙት ሰው ጋር የፆታ ግንኙነት መፈጸም ምን ስህተት አለው?’ ‘ይህን ያህል የማዝነው ለምንድን ነው?’
ከላይ ያሉት ጥያቄዎች የሚያሳስቡህ ከሆነ እንዲህ የሚሰማህ አንተ ብቻ አይደለህም። ለጥያቄዎችህ መልስ ስትፈልግ ደግሞ እርስ በርስ የሚጋጩ ሐሳቦች አግኝተህ ይሆናል። ወጣቶች የሚጠይቋቸው ጥያቄዎችና ተግባራዊ መሆን የሚችሉ መልሶች፣ ጥራዝ 1 የተባለው መጽሐፍ በዚህ ረገድ ሊረዳህ ይችላል። በመጽሐፉ ላይ የሚገኘው ምክር በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ባሉት ጠቃሚ መመሪያዎች ላይ የተመሠረተ ነው። የአምላክ ቃል በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች በሕይወታቸው የሚያጋጥሟቸውን ተፈታታኝ ሁኔታዎች በተሳካ ሁኔታ እንዲወጡ አስችሏቸዋል። አንተም ይህን በራስህ ሕይወት ማየት እንድትችል እንጋብዝሃለን!
በዚህ መጽሐፍ ውስጥ የሚገኙት ክፍሎች፦
ከቤተሰብህ ጋር ያለህ ግንኙነት
ማንነትህ
የትምህርት ቤት ሕይወት
የፆታ ግንኙነት፣ ሥነ ምግባር እና ፍቅር
ራስን የሚጎዱ ልማዶች
ትርፍ ጊዜህ
መንፈሳዊ ነገሮች
ተጨማሪ ክፍል ለወላጆች
ይህን መጽሐፍ በፒዲኤፍ ፎርማት ማውረድ ወይም መጽሐፉ እንዲላክልህ ወደ ቅርንጫፍ ቢሮዎቻችን በመጻፍ መጠየቅ ትችላለህ።
ማስታወሻ፦ የዚህ መጽሐፍ ፒዲኤፍ ፋይል የተዘጋጀው ጽሑፍ ለማስፈር በሚያስችል መንገድ ነው። መጽሐፉን ካወረድህ በኋላ በፒዲኤፍ ማንበቢያ ሶፍትዌር ተጠቅመህ ሐሳብህንና መልሶችህን መጻፍ ትችላለህ።