መጽሐፍ ቅዱስ የሰዎችን ሕይወት ይለውጣል
‘ከፍተኛ ዋጋ ያለውን ዕንቁ’ አግኝተዋል
ኢየሱስ እንዳስተማረው የሰውን ልጅ እየተፈታተኑ ላሉ ችግሮች በሙሉ እልባት የሚሰጠው የአምላክ መንግሥት ነው። (ማቴዎስ 6:10) ኢየሱስ፣ ስለ አምላክ መንግሥት የሚገልጸው እውነት ያለውን ውድ ዋጋ ለማጉላት በማቴዎስ 13:44-46 ላይ የሚገኙትን የሚከተሉትን ሁለት ምሳሌዎች ተናግሯል፦
እርሻ ውስጥ እየሠራ ያለ አንድ ሰው የተደበቀ ውድ ሀብት ሳያስበው አገኘ።
ጥሩ ዕንቁ እየፈለገ ያለ አንድ ተጓዥ ነጋዴ ከፍተኛ ዋጋ ያለው አንድ ዕንቁ አገኘ።
ሁለቱም ሰዎች በጣም ከመደሰታቸው የተነሳ ያገኙትን ውድ ሀብት እጃቸው ለማስገባት ሲሉ ያላቸውን ሁሉ ሸጠዋል። በምሳሌው ላይ የተገለጹት ሰዎች የሚያመለክቱት የአምላክን መንግሥት እንደ ውድ ሀብት የሚመለከቱ ሰዎችን ነው፤ ይህ መንግሥት የሚያስገኘውን በረከት ለማግኘት ሲሉ ብዙ መሥዋዕትነት ከፍለዋል። (ሉቃስ 18:29, 30) ለአብነት ያህል፣ ይህ ቪዲዮ የሁለት ሰዎችን ታሪክ ያወሳል።