ምዕራፍ 12

መጽሐፍ ቅዱስን መማርህን እንድትቀጥል ምን ሊረዳህ ይችላል?

መጽሐፍ ቅዱስን መማርህን እንድትቀጥል ምን ሊረዳህ ይችላል?
ጽሑፉን አሳይ ጽሑፉን ደብቅ

መጽሐፍ ቅዱስን መማር ወደ አንድ አስደሳች ቦታ ከምናደርገው ጉዞ ጋር ይመሳሰላል። ሆኖም እንዲህ ያለ ጉዞ ስናደርግ አንዳንድ ተፈታታኝ ሁኔታዎች ሊያጋጥሙን ይችላሉ። መጽሐፍ ቅዱስን ስትማርም ተመሳሳይ ሁኔታ ያጋጥምህ ይሆናል። ‘መጽሐፍ ቅዱስን መማሬን ማቆም ይኖርብኝ ይሆን?’ ብለህ እንድታስብ የሚያደርጉህ ሁኔታዎች ሊያጋጥሙህ ይችላሉ። ይሁንና የጀመርከውን ጉዞ ለመቀጠል ጥረት ማድረግህ የሚክስ ነው የምንለው ለምንድን ነው? ተፈታታኝ ሁኔታዎች ቢያጋጥሙህም እንድትጸና ሊረዳህ የሚችለው ምንድን ነው?

1. መጽሐፍ ቅዱስን መማርህ ጠቃሚ የሆነው ለምንድን ነው?

“የአምላክ ቃል ሕያውና ኃይለኛ ነው።” (ዕብራውያን 4:12) መጽሐፍ ቅዱስ ልዩ መጽሐፍ ነው፤ ምክንያቱም የአምላክን አስተሳሰብና እሱ ለአንተ ያለውን ስሜት እንድታውቅ ይረዳሃል። እውቀት ብቻ ሳይሆን ጥበብና አስተማማኝ ተስፋ እንዲኖርህ ያስችልሃል። ከሁሉ በላይ ደግሞ መጽሐፍ ቅዱስ የይሖዋ ወዳጅ እንድትሆን ይረዳሃል። መጽሐፍ ቅዱስን ስትማር፣ የአምላክ ቃል ያለው ኃይል ሕይወትህን ያሻሽልልሃል።

2. የመጽሐፍ ቅዱስ እውነቶች ያላቸውን ውድ ዋጋ መገንዘባችን አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያሉት እውነቶች ልክ እንደ ውድ ሀብት ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ “እውነትን ግዛ፤ ፈጽሞም አትሽጣት” የሚል ማበረታቻ የሚሰጠን ለዚህ ነው። (ምሳሌ 23:23) የመጽሐፍ ቅዱስ እውነቶች ምን ያህል ውድ እንደሆኑ የምናስታውስ ከሆነ ተፈታታኝ ሁኔታዎች ቢያጋጥሙንም መጽሐፍ ቅዱስን መማራችንን ለመቀጠል ጥረት እናደርጋለን።—ምሳሌ 2:4, 5⁠ን አንብብ።

3. ይሖዋ መጽሐፍ ቅዱስን መማርህን እንድትቀጥል ሊረዳህ የሚችለው እንዴት ነው?

ሁሉን ቻይ ፈጣሪና ወዳጅህ የሆነው ይሖዋ ስለ እሱ እንድትማር ሊረዳህ ይፈልጋል። ‘ለተግባር የሚያነሳሳ ፍላጎትም ሆነ ኃይል’ ይሰጥሃል። (ፊልጵስዩስ 2:13⁠ን አንብብ።) መጽሐፍ ቅዱስን ለመማር ወይም የተማርከውን ነገር ተግባር ላይ ለማዋል ተጨማሪ ተነሳሽነት በሚያስፈልግህ ጊዜ ሊረዳህ ይችላል። ያጋጠመህን ተፈታታኝ ሁኔታ ወይም ተቃውሞ ለመቋቋም የሚያስችል ተጨማሪ ኃይልም ይሰጥሃል። እንግዲያው መጽሐፍ ቅዱስን መማርህን እንድትቀጥል እንዲረዳህ አዘውትረህ ይሖዋን በጸሎት ለምነው።—1 ተሰሎንቄ 5:17

ጠለቅ ያለ ጥናት

ጊዜህ የተጣበበ ቢሆንም ወይም ከሌሎች ተቃውሞ ቢያጋጥምህም መጽሐፍ ቅዱስን መማርህን እንድትቀጥል የሚረዳህ ምን እንደሆነ እንመለከታለን። በተጨማሪም ይሖዋ በዚህ ረገድ የሚረዳህ እንዴት እንደሆነ እንወያያለን።

4. ለመጽሐፍ ቅዱስ ጥናትህ ቅድሚያ ስጥ

አንዳንዴ ጊዜያችን በጣም ከመጣበቡ የተነሳ መጽሐፍ ቅዱስን ለመማር በቂ ጊዜ እንደሌለን ይሰማን ይሆናል። ታዲያ ምን ሊረዳን ይችላል? ፊልጵስዩስ 1:10ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ፦

  • በሕይወታችን ውስጥ ‘ይበልጥ አስፈላጊ ከሆኑት ነገሮች’ አንዳንዶቹ የትኞቹ ይመስሉሃል?

  • ለመጽሐፍ ቅዱስ ጥናትህ ቅድሚያ ለመስጠት ምን ማድረግ ይኖርብሃል?

  1. ሀ. ባልዲው ውስጥ መጀመሪያ ላይ አሸዋ ከጨመርክ በኋላ ድንጋዮቹን ለመጨመር ብትሞክር ለሁሉም ድንጋዮች የሚሆን በቂ ቦታ አታገኝም

  2. ለ. አስቀድመህ ድንጋዮቹን ካስገባህ ግን አብዛኛውን አሸዋ ለማስገባት የሚያስችል ቦታ ታገኛለህ። በተመሳሳይም በሕይወት ውስጥ ‘ይበልጥ አስፈላጊ ለሆኑት ነገሮች’ ቅድሚያ ከሰጠህ ለሌሎች ነገሮችም የሚሆን ጊዜ ታገኛለህ

መጽሐፍ ቅዱስን መማራችን መንፈሳዊ ፍላጎታችንን ማለትም አምላክን የማወቅና እሱን የማምለክ ፍላጎታችንን ለማሟላት ያስችለናል። ማቴዎስ 5:3ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተለው ጥያቄ ላይ ተወያዩ፦

  • ለመጽሐፍ ቅዱስ ጥናታችን ቅድሚያ መስጠታችን ምን ጥቅም ያስገኝልናል?

5. የሚያጋጥምህን ተቃውሞ በጽናት ተቋቋም

አንዳንድ ጊዜ ሌሎች ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስን መማርህን እንድታቆም ተጽዕኖ ሊያሳድሩብህ ይሞክራሉ። ፍራንሲስኮ የተባለ ሰው ያጋጠመውን ነገር ተመልከት። ቪዲዮውን ተመልከቱ ከዚያም በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ፦

  • በቪዲዮው ላይ የፍራንሲስኮ ጓደኞችና ቤተሰቦች ፍራንሲስኮ ስለሚማረው ነገር ሲነግራቸው ምን ተሰማቸው?

  • መጽናቱ ምን ጥቅም አስገኝቶለታል?

ሁለተኛ ጢሞቴዎስ 2:24, 25ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ፦

  • ቤተሰቦችህና ጓደኞችህ ስለምትማረው ነገር ምን ይሰማቸዋል?

  • በዚህ ጥቅስ መሠረት አንድ ሰው መጽሐፍ ቅዱስን በመማርህ ቢቃወምህ ምላሽ መስጠት ያለብህ እንዴት ነው? ለምን?

6. ይሖዋ እንደሚረዳህ ተማመን

ወደ ይሖዋ ይበልጥ በቀረብን መጠን እሱን ለማስደሰት ያለን ፍላጎትም የዚያኑ ያህል ይጨምራል። ያም ሆኖ ግን ከእሱ መሥፈርቶች ጋር ተስማምተን ለመኖር ስንል በሕይወታችን ላይ አንዳንድ ለውጦችን ማድረግ ተፈታታኝ ሊሆንብን ይችላል። አንተም እንደዚህ ተሰምቶህ የሚያውቅ ከሆነ ተስፋ አትቁረጥ። ይሖዋ ይረዳሃል። ቪዲዮውን ተመልከቱ ከዚያም በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ፦

  • በቪዲዮው ላይ እንደታየው፣ ጂም ይሖዋን ለማስደሰት ሲል ምን ለውጦች አድርጓል?

  • ከእሱ ታሪክ ትኩረትህን የሳበው ምንድን ነው?

ዕብራውያን 11:6ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ፦

  • ይሖዋ “ከልብ ለሚፈልጉት” ሰዎች ማለትም እሱን ለማወቅና ለማስደሰት ጥረት ለሚያደርጉ ሰዎች ምን ያደርግላቸዋል?

  • ከዚህ አንጻር ይሖዋ መጽሐፍ ቅዱስን ለመማር የምታደርገውን ጥረት ሲመለከት ምን የሚሰማው ይመስልሃል?

አንድ ሰው እንዲህ ብሎ ቢጠይቅህስ? “መጽሐፍ ቅዱስን የምትማረው ለምንድን ነው?”

  • ምን ብለህ ትመልሳለህ?

ማጠቃለያ

አንዳንድ ጊዜ ተፈታታኝ ሊሆን ቢችልም መጽሐፍ ቅዱስን መማርህ ለዘላለም በደስታ መኖር የምትችልበት አጋጣሚ ይከፍትልሃል። በይሖዋ መታመንህን ከቀጠልክ እሱ ወሮታህን ይከፍልሃል።

ክለሳ

  • የመጽሐፍ ቅዱስን እውነቶች እንደ ውድ ሀብት አድርገህ የምትመለከታቸው ለምንድን ነው?

  • ‘ይበልጥ አስፈላጊ ለሆኑት ነገሮች’ ቅድሚያ እንደምትሰጥ ማሳየት የምትችለው እንዴት ነው?

  • ይሖዋ መጽሐፍ ቅዱስን መማርህን እንድትቀጥል እንዲረዳህ መጸለይ ያለብህ ለምንድን ነው?

ግብ

ምርምር አድርግ

አንዲት ሴት አምላክን ለማስደሰት ጥረት ስታደርግ ባለቤቷ ይቃወማት ጀመር። ይሖዋ ይህችን ሴት የረዳት እንዴት ነው?

ይሖዋ ኃላፊነታችንን እንድንወጣ ብርታት ይሰጠናል (5:05)

አንድ ሰው ባለቤቱ በመጽናቷ ምን ጥቅም አግኝቷል?

እውነትን መርምሬ አረጋገጥኩ (6:30)

የይሖዋ ምሥክሮች ‘ቤተሰብ ይከፋፍላሉ’ የሚል ነቀፋ የሚሰነዘርባቸው ጊዜ አለ። ሆኖም ይህ እውነት ነው?

“የይሖዋ ምሥክሮች ቤተሰብን ያፈርሳሉ? ወይስ የቤተሰብ ትስስር እንዲጠናከር ይረዳሉ?” (ድረ ገጻችን ላይ የወጣ ርዕስ)