ምዕራፍ 15 ኢየሱስ ማን ነው? አጫውት ኢየሱስ ማን ነው? ይቅርታ፣ ማጫወቻው መሥራት አልቻለም። ይህን ቪዲዮ አውርድ ጽሑፉን አሳይ ጽሑፉን ደብቅ ዲጂታል እትም በወረቀት የሚታተመው ኢየሱስ በታሪክ ውስጥ እጅግ ታዋቂ ከሆኑ ሰዎች መካከል አንዱ ነው። ያም ሆኖ ግን ብዙዎች ከስሙ በቀር ስለ እሱ እምብዛም አያውቁም፤ ሰዎች ስለ እሱ ማንነት ያላቸው አመለካከትም የተለያየ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ኢየሱስ ምን ይላል? 1. ኢየሱስ ማን ነው? ኢየሱስ በሰማይ የሚኖር ኃያል መንፈሳዊ ፍጡር ነው። ይሖዋ አምላክ ከሌሎች ነገሮች ሁሉ በፊት አስቀድሞ የፈጠረው እሱን ነው። በዚህም ምክንያት “የፍጥረት ሁሉ በኩር” ተብሎ ተጠርቷል። (ቆላስይስ 1:15) መጽሐፍ ቅዱስ ኢየሱስ የአምላክ ‘አንድያ ልጅ’ እንደሆነ ይናገራል፤ ምክንያቱም ይሖዋ በቀጥታ የፈጠረው ኢየሱስን ብቻ ነው። (ዮሐንስ 3:16) ኢየሱስ የአባቱ የይሖዋ የቅርብ ረዳት በመሆን፣ ሌሎች ነገሮችን ሁሉ ሲፈጥር አብሮት ሠርቷል። (ምሳሌ 8:30ን አንብብ።) ኢየሱስ ከዚያ በኋላም ቢሆን ከይሖዋ ጋር ያለውን የቅርብ ዝምድና ይዞ ቀጥሏል። “ቃል” ማለትም የአምላክ ቃል አቀባይ በመሆን የእሱን መልእክቶችና መመሪያዎች በታማኝነት አስተላልፏል።—ዮሐንስ 1:14 2. ኢየሱስ ወደ ምድር የመጣው ለምንድን ነው? ከ2,000 ዓመታት ገደማ በፊት ይሖዋ በሰማይ የነበረውን የኢየሱስን ሕይወት ማርያም ወደተባለች ድንግል ማሕፀን አዛውሯል፤ ይህን ተአምር የፈጸመው በቅዱስ መንፈሱ ተጠቅሞ ነው። ኢየሱስ ሰው ሆኖ የተወለደው በዚህ መንገድ ነው። (ሉቃስ 1:34, 35ን አንብብ።) ኢየሱስ ወደ ምድር የመጣው በትንቢት የተነገረለት መሲሕ ወይም ክርስቶስ በመሆን የሰው ልጆችን ለማዳን ነው። a ስለ መሲሑ የተነገሩት የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢቶች በሙሉ በእሱ ላይ ተፈጽመዋል። ይህም ሰዎች ኢየሱስ ተራ ሰው ሳይሆን “ክርስቶስ፣ የሕያው አምላክ ልጅ” መሆኑን እንዲያውቁ አስችሏቸዋል።—ማቴዎስ 16:16 3. ኢየሱስ አሁን በምን ሁኔታ ላይ ይገኛል? ኢየሱስ ሰው ሆኖ በምድር ላይ ያሳለፈውን ሕይወት ካጠናቀቀ በኋላ መንፈስ ሆኖ ከሞት በመነሳት ወደ ሰማይ ተመልሷል። በዚያም “አምላክ የላቀ ቦታ በመስጠት ከፍ ከፍ አደረገው።” (ፊልጵስዩስ 2:9) በአሁኑ ጊዜ ኢየሱስ ከይሖዋ ቀጥሎ ያለውን ከፍተኛ ሥልጣን ይዟል። ጠለቅ ያለ ጥናት ኢየሱስ በእርግጥ ማን እንደሆነና ስለ እሱ ማወቅ አስፈላጊ የሆነው ለምን እንደሆነ በስፋት እንመለከታለን። 4. ኢየሱስ ሁሉን ቻይ አምላክ አይደለም ኢየሱስ በሰማይ ያለ ኃያል መንፈሳዊ ፍጡር ቢሆንም አምላኩና አባቱ ለሆነው ለይሖዋ እንደሚገዛ መጽሐፍ ቅዱስ ያስተምራል። እንዲህ የምንለው ለምንድን ነው? ኢየሱስ ሁሉን ቻይ ከሆነው አምላክ አንጻር ስላለው ቦታ መጽሐፍ ቅዱስ ምን እንደሚያስተምር ለማየት ቪዲዮውን ተመልከቱ። ቪዲዮ፦ ኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ ነው? (3:22) የሚከተሉት ጥቅሶች ይሖዋና ኢየሱስ ስላላቸው ቦታ ለማወቅ ይረዱናል። እያንዳንዱን ጥቅስ አንብቡ፤ ከዚያም በጥያቄዎቹ ላይ ተወያዩ። ሉቃስ 1:30-32ን አንብቡ። መልአኩ በኢየሱስና ‘በልዑሉ አምላክ’ በይሖዋ መካከል ያለውን ዝምድና የገለጸው እንዴት ነው? ማቴዎስ 3:16, 17ን አንብቡ። ኢየሱስ በተጠመቀበት ወቅት ከሰማያት ምን የሚል ድምፅ ተሰማ? ይህ ድምፅ የማን ይመስልሃል? ዮሐንስ 14:28ን አንብቡ። ከአባትና ከልጅ በዕድሜም ሆነ በሥልጣን የሚበልጠው ማን ነው? ኢየሱስ ይሖዋን “አብ” ወይም አባት ብሎ መጥራቱ ምን ያመለክታል? ዮሐንስ 12:49ን አንብቡ። ኢየሱስ እሱና አባቱ እኩል እንደሆኑ ያስባል? አንተስ ስለዚህ ጉዳይ ምን ይሰማሃል? 5. ኢየሱስ መሲሕ እንደሆነ እንዴት እናውቃለን? መጽሐፍ ቅዱስ መሲሑን ማለትም በአምላክ የተመረጠውን የሰው ዘር አዳኝ ለይቶ ለማወቅ የሚያስችሉ በርካታ ትንቢቶችን ይዟል። ኢየሱስ ወደ ምድር በመጣበት ወቅት በእሱ ላይ ፍጻሜያቸውን ያገኙ አንዳንድ ትንቢቶችን ለማየት ቪዲዮውን ተመልከቱ። ቪዲዮ፦ ኢየሱስ ትንቢቶች እንዲፈጸሙ አድርጓል (3:03) የሚከተሉትን የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢቶች አንብቡ፤ ከዚያም በጥያቄዎቹ ላይ ተወያዩ፦ መሲሑ ስለሚወለድበት ቦታ ለማወቅ ሚክያስ 5:2ን አንብቡ። b ይህ ትንቢት በኢየሱስ ላይ ፍጻሜውን አግኝቷል?—ማቴዎስ 2:1 ከመሲሑ ሞት ጋር በተያያዘ የተነገሩትን ትንቢቶች ለማየት መዝሙር 34:20ን እና ዘካርያስ 12:10ን አንብቡ። እነዚህ ትንቢቶች ፍጻሜያቸውን አግኝተዋል?—ዮሐንስ 19:33-37 ኢየሱስ ሁኔታዎችን በመቆጣጠር እነዚህ ትንቢቶች በእሱ ላይ ፍጻሜያቸውን እንዲያገኙ ማድረግ የሚችል ይመስልሃል? ይህ ኢየሱስን በተመለከተ ምን ያረጋግጣል? 6. ስለ ኢየሱስ ማወቃችን ይጠቅመናል መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ኢየሱስና እሱ ስለሚጫወተው ሚና ማወቅ ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ ጎላ አድርጎ ይገልጻል። ዮሐንስ 14:6ን እና 17:3ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተለው ጥያቄ ላይ ተወያዩ፦ ስለ ኢየሱስ ማወቅ አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? ኢየሱስ የአምላክ ወዳጅ መሆን የምንችልበትን መንገድ ከፍቷል። ስለ ይሖዋ እውነቱን አስተምሯል፤ እንዲሁም በእሱ አማካኝነት የዘላለም ሕይወት ማግኘት እንችላለን አንዳንዶች እንዲህ ይላሉ፦ “የይሖዋ ምሥክሮች በኢየሱስ አያምኑም።” አንተ ምን መልስ ትሰጣለህ? ማጠቃለያ ኢየሱስ ኃያል መንፈሳዊ ፍጡር ነው። በተጨማሪም የአምላክ ልጅና መሲሕ ነው። ክለሳ ኢየሱስ “የፍጥረት ሁሉ በኩር” ተብሎ የተጠራው ለምንድን ነው? ኢየሱስ ወደ ምድር ከመምጣቱ በፊት ምን ነገሮችን አከናውኗል? ኢየሱስ መሲሕ እንደሆነ እንዴት እናውቃለን? ምዕራፉ የተጠናቀቀበት ቀን፦ ግብ ‘በእርግጥም አምላክ ኢየሱስን ጌታም ክርስቶስም አደረገው’—ክፍል 1 የሚለውን ድራማ በመመልከት ወይም ሉቃስ ምዕራፍ 2ን እና 3ን በማንበብ ኢየሱስ ምድር ላይ ስላሳለፈው ሕይወት ተማር። ሌላ፦ ሌላ ግብ ምርምር አድርግ መጽሐፍ ቅዱስ አምላክ የኢየሱስ አባት እንደሆነ ሲናገር ሰዎች ልጅ በሚወልዱበት መንገድ ቃል በቃል እንደወለደው መናገሩ ነው? “ኢየሱስ የአምላክ ልጅ ተብሎ የተጠራው ለምንድን ነው?” (ድረ ገጻችን ላይ የወጣ ርዕስ) ሥላሴ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት አይደለም የምንለው ለምንድን ነው? “ኢየሱስ አምላክ ነው?” (መጠበቂያ ግንብ ሚያዝያ 1, 2009) a ምዕራፍ 26 እና 27 ላይ የሰው ልጆች መዳን የሚያስፈልጋቸው ለምን እንደሆነና ኢየሱስ የሚያድነን እንዴት እንደሆነ ይብራራል። b ኢየሱስ ምድር ላይ የሚገለጠው መቼ እንደሆነ የሚገልጽ ትንቢት ለማየት ተጨማሪ ሐሳብ 2ን ተመልከት። ተመለስ ቀጥል አትም አጋራ አጋራ ኢየሱስ ማን ነው? ለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ ኢየሱስ ማን ነው? የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ኢየሱስ ማን ነው? https://cms-imgp.jw-cdn.org/img/p/1102021215/univ/art/1102021215_univ_sqr_xl.jpg lff ትምህርት 15