ምዕራፍ 24 መላእክትን በተመለከተ እውነታው ምንድን ነው? አጫውት መላእክትን በተመለከተ እውነታው ምንድን ነው? ይቅርታ፣ ማጫወቻው መሥራት አልቻለም። ይህን ቪዲዮ አውርድ ጽሑፉን አሳይ ጽሑፉን ደብቅ ዲጂታል እትም በወረቀት የሚታተመው ይሖዋ በሰማይ ስላለው ቤተሰቡ እንድናውቅ ይፈልጋል። በሰማይ ያለው የአምላክ ቤተሰብ ‘የአምላክ ልጆች’ ተብለው የተጠሩትን መላእክትን ይጨምራል። (ኢዮብ 38:7) መጽሐፍ ቅዱስ ስለ መላእክት ምን ይላል? መላእክት በሰዎች ላይ ምን ተጽዕኖ ያሳድራሉ? ሁሉም መላእክት የአምላክ ቤተሰብ አባላት ናቸው? 1. መላእክት እነማን ናቸው? ይሖዋ መላእክትን የፈጠረው ምድርን ከመፍጠሩ በፊት ነው። መላእክት ልክ እንደ እሱ በዓይን የማይታዩና በሰማይ የሚኖሩ መንፈሳዊ አካላት ናቸው። (ዕብራውያን 1:14) በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ መላእክት ያሉ ሲሆን እያንዳንዳቸው ልዩ የሚያደርጋቸው የራሳቸው የሆነ ባሕርይ አላቸው። (ራእይ 5:11) እነዚህ መላእክት ‘የይሖዋን ትእዛዛት በማክበር ቃሉን ይፈጽማሉ።’ (መዝሙር 103:20) በጥንት ዘመን ይሖዋ መልእክት እንዲያደርሱ እንዲሁም ሕዝቡን እንዲረዱና እንዲያድኑ መላእክቱን የላከባቸው ጊዜያት ነበሩ። በዛሬው ጊዜ መላእክት ክርስቲያኖችን ስለ አምላክ ማወቅ ወደሚፈልጉ ሰዎች ይመሯቸዋል። 2. ሰይጣንና አጋንንቱ እነማን ናቸው? አንዳንድ መላእክት ለይሖዋ ታማኝ ሆነው አልቀጠሉም። በአምላክ ላይ ያመፀው የመጀመሪያው መልአክ “መላውን ዓለም እያሳሳተ ያለው ዲያብሎስና ሰይጣን” ነው። (ራእይ 12:9) ሰይጣን በሌሎች ላይ የበላይ ሆኖ መግዛት ስለፈለገ አዳምና ሔዋን በኋላም ሌሎች መላእክት ጭምር አብረውት እንዲያምፁ አደረገ። እነዚህ ዓመፀኛ መላእክት አጋንንት ተብለው ይጠራሉ። ይሖዋ ከሰማይ ወደ ምድር ያባረራቸው ሲሆን ወደፊት ጥፋት ይጠብቃቸዋል።—ራእይ 12:9, 12ን አንብብ። 3. ሰይጣንና አጋንንቱ ሊያታልሉን የሚሞክሩት እንዴት ነው? ሰይጣንና አጋንንቱ፣ በአጋንንታዊ ወይም በመናፍስታዊ ድርጊቶች አማካኝነት ብዙዎችን ለማታለል ይሞክራሉ፤ አጋንንታዊ ወይም መናፍስታዊ ድርጊት የሚባለው ከመናፍስት ጋር ለመገናኘት የሚደረገው ጥረት ነው። ለምሳሌ ያህል፣ አንዳንድ ሰዎች ጠንቋዮችን፣ “አዋቂ” ተብለው የሚጠሩ ሰዎችን፣ ኮከብ ቆጣሪዎችንና ምትሃታዊ ኃይል አላቸው የሚባሉ ሰዎችን ያማክራሉ። ሌሎች ደግሞ ከመናፍስት ጋር ንክኪ ያላቸው የሕክምና አማራጮችን ይጠቀማሉ። የሞቱ ሰዎችን ማነጋገር ይቻላል ብለው የሚያስቡ ሰዎችም አሉ። ይሖዋ ግን “ወደ መናፍስት ጠሪዎች አትሂዱ፤ ጠንቋዮችንም አትጠይቁ” በማለት አስጠንቅቆናል። (ዘሌዋውያን 19:31) ይህን ማስጠንቀቂያ የሰጠን ሰይጣንና አጋንንቱ ከሚያሳድሩት ተጽዕኖ ጥበቃ ሊያደርግልን ስለሚፈልግ ነው። የአምላክ ጠላት የሆኑት እነዚህ ክፉ መናፍስት በእኛ ላይ ጉዳት ሊያደርሱ ይፈልጋሉ። ጠለቅ ያለ ጥናት መላእክት ስለሚያከናውኑት ጠቃሚ ሥራ፣ መናፍስታዊ ድርጊት ስላለው አደጋ እንዲሁም ከሰይጣንና ከአጋንንቱ ራሳችንን መጠበቅ ስለምንችልበት መንገድ እንመለከታለን። 4. መላእክት ሰዎች ስለ ይሖዋ እንዲማሩ ይረዳሉ የአምላክ መላእክት በቀጥታ ለሰዎች አይሰብኩም። ሆኖም የይሖዋን አገልጋዮች ስለ አምላክ መማር ወደሚፈልጉ ሰዎች ሊመሯቸው ይችላሉ። ራእይ 14:6, 7ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ፦ የስብከቱን ሥራ ስናከናውን የመላእክት እርዳታ የሚያስፈልገን ለምንድን ነው? መላእክት መጽሐፍ ቅዱስን መማር ወደሚፈልጉ ሰዎች ሊመሩህ እንደሚችሉ ማወቅህ ያበረታታሃል? እንዲህ ብለህ የመለስከው ለምንድን ነው? 5. ከመናፍስታዊ ድርጊቶች ራቅ ሰይጣንና አጋንንቱ የይሖዋ ጠላቶች ናቸው። የእኛም ጠላቶች ናቸው። ሉቃስ 9:38-42ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተለው ጥያቄ ላይ ተወያዩ፦ አጋንንት በሰዎች ላይ ምን ጉዳት ያደርሳሉ? አጋንንት በሕይወታችን ላይ ተጽዕኖ እንዲያሳድሩ መፍቀድ አይኖርብንም። ዘዳግም 18:10-12ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ፦ አጋንንት በእኛ ላይ ተጽዕኖ ለማሳደር ወይም ከእኛ ጋር ለመገናኘት የትኞቹን ዘዴዎች ይጠቀማሉ? አንተ በምትኖርበት አካባቢ የትኞቹን ልማዶች አስተውለሃል? ይሖዋ መናፍስታዊ ድርጊቶችን መከልከሉ ምክንያታዊ እንደሆነ ይሰማሃል? እንዲህ ብለህ የመለስከው ለምንድን ነው? ቪዲዮውን ተመልከቱ፤ ከዚያም በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ፦ ቪዲዮ፦ ‘ዲያብሎስን ተቃወሙት’ (5:02) የፓሌሳ ልጅ ያደረገችው ክታብ ጉዳት ያለው ይመስልሃል? እንዲህ ብለህ የመለስከው ለምንድን ነው? ፓሌሳ አጋንንት ከሚያሳድሩባት ተጽዕኖ ለመላቀቅ ምን ማድረግ ነበረባት? እውነተኛ ክርስቲያኖች ከጥንት ጊዜ አንስቶ አጋንንትን ሲቃወሙ ቆይተዋል። የሐዋርያት ሥራ 19:19ን እና 1 ቆሮንቶስ 10:21ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተለው ጥያቄ ላይ ተወያዩ፦ ከመናፍስታዊ ድርጊት ጋር ንክኪ ያለውን ማንኛውንም ነገር ማስወገድህ አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? 6. ከሰይጣንና ከአጋንንቱ ጋር በምታደርገው ውጊያ አሸናፊ መሆን ትችላለህ አጋንንትን የሚመራቸው ሰይጣን ነው። ታማኝ መላእክትን የሚመራው ግን የመላእክት አለቃ ሚካኤል ነው፤ ሚካኤል የኢየሱስ ሌላ መጠሪያ ነው። ሚካኤል ምን ያህል ኃያል ነው? ራእይ 12:7-9ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ፦ የበለጠ ኃይል ያላቸው እነማን ይመስሉሃል? ሚካኤልና መላእክቱ ወይስ ሰይጣንና አጋንንቱ? የኢየሱስ ተከታዮች ሰይጣንንና አጋንንቱን መፍራት የሚኖርባቸው ይመስልሃል? ከሰይጣንና ከአጋንንቱ ጋር በምታደርገው ውጊያ አሸናፊ መሆን ትችላለህ። ያዕቆብ 4:7ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተለው ጥያቄ ላይ ተወያዩ፦ ሰይጣንና አጋንንቱ ከሚያሳድሩት ተጽዕኖ ራስህን መጠበቅ የምትችለው እንዴት ነው? አንዳንዶች እንዲህ ይላሉ፦ “ከመናፍስታዊ ድርጊት ጋር ንክኪ ያላቸውን ጌሞች መጫወት ወይም ፊልሞች ማየት ምንም ችግር የለውም። እንዲሁ ዘና ለማለት ተብሎ የሚደረግ ነው።” ይህ አመለካከት አደገኛ የሆነው ለምንድን ነው? ማጠቃለያ ታማኝ መላእክት እኛን የሚጠቅም ሥራ ያከናውናሉ። ሰይጣንና አጋንንቱ ግን የይሖዋ ጠላቶች ናቸው፤ ሰዎችን ለማታለል መናፍስታዊ ድርጊቶችን ይጠቀማሉ። ክለሳ የይሖዋ መላእክት ሰዎች ስለ አምላክ እንዲማሩ እየረዱ ያሉት እንዴት ነው? ሰይጣንና አጋንንቱ እነማን ናቸው? ከመናፍስታዊ ድርጊት ጋር ምንም ዓይነት ንክኪ እንዳይኖርህ መጠንቀቅ ያለብህ ለምንድን ነው? ምዕራፉ የተጠናቀቀበት ቀን፦ ግብ ከመናፍስታዊ ድርጊት ጋር ንክኪ ያላቸው ዕቃዎች ይኖሩህ እንደሆነ ለማሰብ ሞክር፤ ከዚያም እነዚህን ዕቃዎች ምን እንደምታደርጋቸው ለመወሰን የሚያስችል ጥበብ እንዲሰጥህ ወደ አምላክ ጸልይ። ሌላ፦ ሌላ ግብ ምርምር አድርግ ኢየሱስ የመላእክት አለቃ ሚካኤል እንደሆነ የሚያሳዩ ምን ማስረጃዎች አሉ? “የመላእክት አለቃ ሚካኤል ማን ነው?” (ድረ ገጻችን ላይ የወጣ ርዕስ) ዲያብሎስ በሰዎች ውስጥ ያለ ክፉ ሐሳብ እንዳልሆነ የሚያሳይ ምን ማስረጃ አለ? “ዲያብሎስ በእርግጥ አለ?” (ድረ ገጻችን ላይ የወጣ ርዕስ) ተመለስ ቀጥል አትም አጋራ አጋራ መላእክትን በተመለከተ እውነታው ምንድን ነው? ለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ መላእክትን በተመለከተ እውነታው ምንድን ነው? የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ መላእክትን በተመለከተ እውነታው ምንድን ነው? https://cms-imgp.jw-cdn.org/img/p/1102021224/univ/art/1102021224_univ_sqr_xl.jpg lff ትምህርት 24