ምዕራፍ 31 የአምላክ መንግሥት ምንድን ነው? አጫውት የአምላክ መንግሥት ምንድን ነው? ይቅርታ፣ ማጫወቻው መሥራት አልቻለም። ይህን ቪዲዮ አውርድ ጽሑፉን አሳይ ጽሑፉን ደብቅ ዲጂታል እትም በወረቀት የሚታተመው የመጽሐፍ ቅዱስ ዋነኛ መልእክት በአምላክ መንግሥት ላይ ያተኮረ ነው። ይሖዋ ምድርን ገነት ለማድረግ ያለውን የመጀመሪያ ዓላማ ዳር የሚያደርሰው በዚህ መንግሥት አማካኝነት ነው። ለመሆኑ የአምላክ መንግሥት ምንድን ነው? በአሁኑ ጊዜ በመግዛት ላይ እንዳለ እንዴት እናውቃለን? እስካሁን ምን ነገሮችን አከናውኗል? ወደፊትስ ምን ነገሮችን ያከናውናል? ይህ ምዕራፍና ቀጣዮቹ ሁለት ምዕራፎች ለእነዚህ ጥያቄዎች መልስ ይሰጣሉ። 1. የአምላክ መንግሥት ምንድን ነው? ንጉሡስ ማን ነው? የአምላክ መንግሥት ይሖዋ አምላክ ያቋቋመው መስተዳድር ነው። የዚህ መንግሥት ንጉሥ ኢየሱስ ክርስቶስ ሲሆን የሚገዛውም ከሰማይ ነው። (ማቴዎስ 4:17፤ ዮሐንስ 18:36) መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ኢየሱስ ሲናገር “ለዘላለም ንጉሥ ሆኖ ይገዛል” ይላል። (ሉቃስ 1:32, 33) የአምላክ መንግሥት ንጉሥ የሆነው ኢየሱስ ወደፊት በምድር ላይ ያሉ ሰዎችን ሁሉ ይገዛል። 2. ከኢየሱስ ጋር አብረው የሚገዙት እነማን ናቸው? ኢየሱስ የሚገዛው ብቻውን አይደለም። “ከየነገዱ፣ ከየቋንቋው፣ ከየሕዝቡና ከየብሔሩ” የተውጣጡ ሰዎች ‘በምድር ላይ ነገሥታት ሆነው ይገዛሉ።’ (ራእይ 5:9, 10) ከክርስቶስ ጋር የሚገዙት ሰዎች ምን ያህል ናቸው? ኢየሱስ ወደ ምድር ከመጣ ወዲህ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ክርስቲያኖች የእሱ ተከታዮች ሆነዋል። ሆኖም ወደ ሰማይ ሄደው ከኢየሱስ ጋር የሚገዙት 144,000 የሚያህሉ ሰዎች ብቻ ናቸው። (ራእይ 14:1-4ን አንብብ።) በምድር ላይ የሚቀሩት ሌሎች ክርስቲያኖች በሙሉ የአምላክ መንግሥት ተገዢዎች ይሆናሉ።—መዝሙር 37:29 3. የአምላክን መንግሥት ሰዎች ከሚያስተዳድሯቸው መንግሥታት የተሻለ የሚያደርገው ምንድን ነው? የመንግሥት ባለሥልጣናት ጥሩ ነገሮችን ማድረግ ቢፈልጉም እንኳ የፈለጉትን ሁሉ ለማድረግ የሚያስችል ኃይል የላቸውም። በተጨማሪም የጊዜ ጉዳይ ነው እንጂ፣ ራስ ወዳድ በሆኑና ሰዎችን መርዳት በማይፈልጉ ሌሎች ባለሥልጣናት መተካታቸው አይቀርም። የአምላክ መንግሥት ንጉሥ የሆነው ኢየሱስ ግን በማንም አይተካም። አምላክ ያቋቋመው መንግሥት “ፈጽሞ የማይጠፋ” ነው። (ዳንኤል 2:44) ኢየሱስ መላዋን ምድር የሚገዛ ሲሆን አንዱን ከሌላው አያበላልጥም። አፍቃሪ፣ ደግና ፍትሐዊ ከመሆኑም በላይ ሰዎችም ልክ እንደ እሱ እነዚህን ባሕርያት እንዲያንጸባርቁ ያስተምራል።—ኢሳይያስ 11:9ን አንብብ። ጠለቅ ያለ ጥናት የአምላክን መንግሥት ሰዎች ከሚያስተዳድሩት ከየትኛውም መንግሥት የተሻለ የሚያደርገው ምን እንደሆነ እንመለከታለን። 4. መላዋ ምድር በአንድ ታላቅ መስተዳድር ሥር ትሆናለች ኢየሱስ ክርስቶስ እስከ ዛሬ ድረስ በምድር ላይ ከተነሱት ገዢዎች ሁሉ የበለጠ ሥልጣን አለው። ማቴዎስ 28:18ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተለው ጥያቄ ላይ ተወያዩ፦ ኢየሱስ በምድር ላይ ካለ ከየትኛውም ገዢ የበለጠ ሥልጣን አለው የምንለው ለምንድን ነው? በዓለም ላይ ያሉት መንግሥታት በየጊዜው ይቀያየራሉ፤ ደግሞም አንድ መንግሥት የሚያስተዳድረው የዓለማችንን የተወሰነ ክፍል ነው። የአምላክ መንግሥትስ? ዳንኤል 7:14ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ፦ የአምላክ መንግሥት “የማይጠፋ” መሆኑ ምን ጥቅም አለው? መላዋን ምድር የሚገዛ መሆኑ ምን ጥቅም አለው? 5. የሰዎች አገዛዝ መተካት አለበት የሰዎች አገዛዝ በአምላክ መንግሥት ሊተካ የሚገባው ለምንድን ነው? ቪዲዮውን ተመልከቱ፤ ከዚያም በሚከተለው ጥያቄ ላይ ተወያዩ፦ ቪዲዮ፦ የአምላክ መንግሥት ምንድን ነው?—ተቀንጭቦ የተወሰደ (1:38) የሰዎች አገዛዝ ምን ውጤት አስከትሏል? መክብብ 8:9ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ፦ የሰዎች አገዛዝ በአምላክ መንግሥት ሊተካ እንደሚገባ ይሰማሃል? እንዲህ ብለህ የመለስከው ለምንድን ነው? 6. የአምላክ መንግሥት ገዢዎች ያለንበትን ሁኔታ ይረዱልናል ንጉሣችን ኢየሱስ በአንድ ወቅት ሰው ሆኖ ስለኖረ ‘በድካማችን ይራራልናል።’ (ዕብራውያን 4:15) ይሖዋ ከኢየሱስ ጋር እንዲገዙ የመረጣቸው 144,000 ታማኝ ወንዶችና ሴቶች “ከየነገዱ፣ ከየቋንቋው፣ ከየሕዝቡና ከየብሔሩ” የተውጣጡ ናቸው።—ራእይ 5:9 ኢየሱስና ከእሱ ጋር የሚገዙት ሰዎች በሙሉ በአንድ ወቅት እንደ እኛው ሰው የነበሩ መሆናቸውን ማወቃችን የሚያጽናናን ለምንድን ነው? ይሖዋ ከኢየሱስ ጋር እንዲገዙ የመረጣቸው ወንዶችና ሴቶች የተለያየ ዘርና አስተዳደግ ያላቸው ናቸው 7. የአምላክ መንግሥት ሰዎች ከሚያስተዳድሩት ከየትኛውም መንግሥት የላቁ ሕጎች አሉት መንግሥታት ለዜጎቻቸው ጥቅምና ጥበቃ ያስገኛሉ ብለው የሚያስቧቸውን ሕጎች ያወጣሉ። የአምላክ መንግሥትም ተገዢዎቹ ሊያከብሯቸው የሚገቡ ሕጎች አሉት። አንደኛ ቆሮንቶስ 6:9-11ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ፦ ሁሉም ሰው አምላክ ያወጣቸውን የሥነ ምግባር ደንቦች ቢከተል ዓለማችን ምን መልክ የሚኖራት ይመስልሃል? a ይሖዋ የመንግሥቱ ተገዢዎች እነዚህን ሕጎች እንዲያከብሩ መጠበቁ ምክንያታዊ ይመስልሃል? እንዲህ ብለህ የመለስከው ለምንድን ነው? እነዚህን ሕጎች የማይታዘዙ ሰዎች ሊለወጡ እንደሚችሉ የሚያሳይ ምን ማስረጃ አለ?—ቁጥር 11ን ተመልከት። መንግሥታት ለዜጎቻቸው ጥበቃና ጥቅም የሚያስገኙ የተለያዩ ሕጎችን ያወጣሉ። የአምላክ መንግሥት ለተገዢዎቹ ጥበቃና ጥቅም የሚያስገኙ የላቁ ሕጎች አሉት አንድ ሰው እንዲህ ብሎ ቢጠይቅህስ? “የአምላክ መንግሥት ምንድን ነው?” ምን ብለህ ትመልሳለህ? ማጠቃለያ የአምላክ መንግሥት በሰማይ ያለ መስተዳድር ሲሆን ወደፊት መላዋን ምድር ይገዛል። ክለሳ የአምላክ መንግሥት ገዢዎች እነማን ናቸው? የአምላክ መንግሥት ሰዎች ከሚያስተዳድሩት ከየትኛውም መንግሥት የተሻለ የሆነው በየትኞቹ መንገዶች ነው? ይሖዋ ከመንግሥቱ ተገዢዎች የሚጠብቃቸው አንዳንድ ነገሮች ምንድን ናቸው? ምዕራፉ የተጠናቀቀበት ቀን፦ ግብ ኢሳይያስ 11:2-9 ላይ የሚገኘውን ስለ ኢየሱስ አገዛዝ የሚገልጽ ሐሳብ አንብብ፤ ከዚያም የኢየሱስ አገዛዝ ከሰዎች አገዛዝ የሚለየው እንዴት እንደሆነ ለማስተዋል ሞክር። ሌላ፦ ሌላ ግብ ምርምር አድርግ ኢየሱስ የአምላክ መንግሥት የሚገኝበትን ቦታ በተመለከተ ምን አስተምሯል? “የአምላክ መንግሥት በሰዎች ልብ ውስጥ ያለ ነገር ነው?” (ድረ ገጻችን ላይ የወጣ ርዕስ) የይሖዋ ምሥክሮች፣ ከሰዎች መንግሥት ይልቅ ለአምላክ መንግሥት ታማኝ ለመሆን የሚመርጡት ለምንድን ነው? ለአምላክ መንግሥት ታማኝ መሆን (1:43) መጽሐፍ ቅዱስ፣ ይሖዋ ከኢየሱስ ጋር እንዲገዙ የመረጣቸውን 144,000 ሰዎች አስመልክቶ ምን ይላል? “ወደ ሰማይ የሚሄዱት እነማን ናቸው?” (ድረ ገጻችን ላይ የወጣ ርዕስ) a ከእነዚህ የሥነ ምግባር ደንቦች መካከል አንዳንዶቹ ክፍል 3 ላይ ይብራራሉ። ተመለስ ቀጥል አትም አጋራ አጋራ የአምላክ መንግሥት ምንድን ነው? ለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ የአምላክ መንግሥት ምንድን ነው? የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ የአምላክ መንግሥት ምንድን ነው? https://cms-imgp.jw-cdn.org/img/p/1102021231/univ/art/1102021231_univ_sqr_xl.jpg lff ትምህርት 31