ምዕራፍ 56

ለጉባኤው አንድነት የበኩልህን አስተዋጽኦ አበርክት

ለጉባኤው አንድነት የበኩልህን አስተዋጽኦ አበርክት
ጽሑፉን አሳይ ጽሑፉን ደብቅ

ከወንድሞቻችንና ከእህቶቻችን ጋር ስንሆን እንደ ንጉሥ ዳዊት ዓይነት ስሜት ይሰማናል፤ ዳዊት “ወንድሞች በአንድነት አብረው ቢኖሩ ምንኛ መልካም ነው! ምንኛስ ደስ ያሰኛል!” ብሎ ነበር። (መዝሙር 133:1) በመካከላችን ያለው አንድነት እንዲሁ በአጋጣሚ የተገኘ አይደለም። አንድነታችንን ለመጠበቅ ሁላችንም የምናበረክተው አስተዋጽኦ አለ።

1. በአምላክ ሕዝቦች መካከል ምን አስገራሚ ነገር ይታያል?

ወደ ሌላ አገር ሄደህ በጉባኤ ስብሰባ ላይ ብትገኝ ቋንቋው ባይገባህ እንኳ የእንግድነት ስሜት አይሰማህም። ለምን? ምክንያቱም በዓለም ዙሪያ ያለን የይሖዋ ምሥክሮች መጽሐፍ ቅዱስን የምናጠናው ተመሳሳይ ጽሑፍ ተጠቅመን ነው። በተጨማሪም አንዳችን ለሌላው ፍቅር ለማሳየት ጥረት እናደርጋለን። የምንኖረው የትም ይሁን የት ሁላችንም ‘የይሖዋን ስም በመጥራት በአንድነት እናመልከዋለን።’ሶፎንያስ 3:9 የግርጌ ማስታወሻ

2. በጉባኤው መካከል አንድነት እንዲሰፍን ምን አስተዋጽኦ ማበርከት ትችላለህ?

መጽሐፍ ቅዱስ “እርስ በርሳችሁ አጥብቃችሁ ከልብ ተዋደዱ” የሚል ምክር ይሰጣል። (1 ጴጥሮስ 1:22) ይህን ምክር ተግባራዊ ማድረግ የምትችለው እንዴት ነው? በሌሎች ድክመት ላይ ከማተኮር ይልቅ ያሏቸውን ጥሩ ባሕርያት ለማስተዋል ጥረት አድርግ። ከአንተ ጋር ተመሳሳይ ፍላጎት ካላቸው ሰዎች ጋር ብቻ ጊዜ አታሳልፍ፤ ከሌሎች ወንድሞችና እህቶችም ጋር ለመተዋወቅ ጥረት አድርግ። በተጨማሪም በውስጣችን ያለውን ማንኛውንም ዓይነት ጭፍን ጥላቻ ለማስወገድ ከፍተኛ ጥረት ማድረጋችን አስፈላጊ ነው።—1 ጴጥሮስ 2:17⁠ን አንብብ። a

3. ከአንድ ወንድም ወይም ከአንዲት እህት ጋር አለመግባባት ቢያጋጥምህ ምን ማድረግ ይኖርብሃል?

በመካከላችን አንድነት ቢኖርም ሁላችንም ፍጹም አይደለንም። አንዳችን ሌላውን ቅር የምናሰኝበት አልፎ ተርፎም የምንጎዳበት ጊዜ አለ። የአምላክ ቃል “በነፃ ይቅር መባባላችሁን ቀጥሉ” የሚል ምክር የሚሰጠን ለዚህ ነው። ጥቅሱ አክሎም “ይሖዋ በነፃ ይቅር እንዳላችሁ ሁሉ እናንተም እንዲሁ አድርጉ” ይላል። (ቆላስይስ 3:13⁠ን አንብብ።) ይሖዋ በተደጋጋሚ ብናሳዝነውም ይቅር ይለናል። በመሆኑም እኛም ወንድሞቻችንን ይቅር እንድንል ይጠብቅብናል። አንድን ሰው ቅር እንዳሰኘህ ከተገነዘብክ ቅድሚያ ወስደህ ሰላም ለመፍጠር ጥረት አድርግ።—ማቴዎስ 5:23, 24⁠ን አንብብ። b

ጠለቅ ያለ ጥናት

ለጉባኤው ሰላምና አንድነት የበኩልህን አስተዋጽኦ ማበርከት የምትችልባቸውን መንገዶች እንመለከታለን።

ሰላም ለመፍጠር ምን ታደርጋለህ?

4. ጭፍን ጥላቻን አስወግድ

ሁሉንም ወንድሞቻችንን መውደድ እንዳለብን እናውቃለን። ሆኖም ከእኛ የተለየ ዘር ወይም ባሕል ያላቸውን ሰዎች መውደድ ከባድ ሊሆንብን ይችላል። በዚህ ረገድ ምን ይረዳናል? የሐዋርያት ሥራ 10:34, 35ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ፦

  • ይሖዋ ሁሉንም ዓይነት ሰዎች ምሥክሮቹ አድርጎ ይቀበላል። ይህን ማወቅህ ከአንተ የተለየ ዘር ወይም ባሕል ላላቸው ሰዎች ባለህ አመለካከት ላይ ምን ለውጥ ሊያመጣ ይገባል?

  • በአካባቢህ የሚኖሩ በርካታ ሰዎች ምን ዓይነት ጭፍን ጥላቻ አላቸው? እንዲህ ያለውን ጭፍን ጥላቻ ማስወገድ ያለብህ ለምንድን ነው?

ሁለተኛ ቆሮንቶስ 6:11-13ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተለው ጥያቄ ላይ ተወያዩ፦

  • ከአንተ የተለየ ባሕልና አስተዳደግ ካላቸው ሰዎች ጋር ለመቀራረብ ምን ይረዳሃል?

5. በነፃ ይቅር በል እንዲሁም ሰላም ፍጠር

ይሖዋ የእኛ ይቅርታ ፈጽሞ አያስፈልገውም፤ ሆኖም እኛን በነፃ ይቅር ለማለት ፈቃደኛ ነው። መዝሙር 86:5ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ፦

  • ይሖዋ ምን ያህል ይቅር ባይ ነው?

  • ይሖዋ ይቅር ባይ በመሆኑ አመስጋኝ የሆንከው ለምንድን ነው?

  • ከሌሎች ጋር መግባባት ከባድ እንዲሆንብን የሚያደርጉ አንዳንድ ምክንያቶች የትኞቹ ናቸው?

ይሖዋን መምሰል እንዲሁም ከወንድሞቻችንና ከእህቶቻችን ጋር ያለንን አንድነት መጠበቅ የምንችለው እንዴት ነው? ምሳሌ 19:11ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተለው ጥያቄ ላይ ተወያዩ፦

  • አንድ ሰው ሲያበሳጭህ ወይም ቅር ሲያሰኝህ ሰላም ለመፍጠር ምን ማድረግ ትችላለህ?

አንዳንድ ጊዜ እኛ ራሳችን ሌሎችን ቅር ልናሰኝ እንችላለን። እንዲህ ያለ ሁኔታ ሲፈጠር ምን ማድረግ ይኖርብናል? ቪዲዮውን ተመልከቱ ከዚያም በሚከተለው ጥያቄ ላይ ተወያዩ፦

  • በቪዲዮው ላይ የታየችው እህት ሰላም ለመፍጠር ስትል ምን አድርጋለች?

6. በወንድሞችህና በእህቶችህ መልካም ጎን ላይ አተኩር

ከወንድሞቻችንና ከእህቶቻችን ጋር ይበልጥ እየተቀራረብን ስንሄድ ጠንካራም ሆነ ደካማ ጎናቸው በግልጽ ይታየናል። ታዲያ በጠንካራ ጎናቸው ላይ ማተኮር የምንችለው እንዴት ነው? ቪዲዮውን ተመልከቱ ከዚያም በሚከተለው ጥያቄ ላይ ተወያዩ፦

  • በወንድሞችህና በእህቶችህ ጥሩ ጎን ላይ ለማተኮር ምን ይረዳሃል?

ይሖዋ የሚያተኩረው በጥሩ ጎናችን ላይ ነው። ሁለተኛ ዜና መዋዕል 16:9ሀን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተለው ጥያቄ ላይ ተወያዩ፦

  • ይሖዋ በጥሩ ጎንህ ላይ እንደሚያተኩር ማወቅህ ምን እንዲሰማህ ያደርጋል?

በጣም የሚያምር አልማዝም እንኳ እንከኖች አሉበት፤ ያም ሆኖ ከፍተኛ ዋጋ ያወጣል። በተመሳሳይም ሁሉም ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ጉድለት ቢኖርባቸውም በይሖዋ ፊት ውድ ናቸው

አንዳንዶች እንዲህ ይላሉ፦ “በቅድሚያ እሱ ይቅርታ ሊጠይቀኝ ይገባል።”

  • በነፃ ይቅር ማለታችን አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?

ማጠቃለያ

ይቅር ባይ በመሆን እንዲሁም ሁሉንም ወንድሞችና እህቶች በመውደድ ለጉባኤው አንድነት የበኩልህን አስተዋጽኦ ማበርከት ትችላለህ።

ክለሳ

  • ጭፍን ጥላቻን ማስወገድ የምትችለው እንዴት ነው?

  • ከአንድ ወንድም ወይም ከአንዲት እህት ጋር አለመግባባት ቢያጋጥምህ ምን ማድረግ ይኖርብሃል?

  • ይቅር ባይ በመሆን ረገድ የይሖዋን ምሳሌ መከተል የምትፈልገው ለምንድን ነው?

ግብ

ምርምር አድርግ

ኢየሱስ ከሰጣቸው ምሳሌዎች መካከል አንዱ በሌሎች ላይ ከመፍረድ እንድንቆጠብ የሚረዳን እንዴት ነው?

ግንዱን አውጣ (7:01)

አንዳንዶች አድልዎ አለማድረግን የተማሩት እንዴት ነው?

የሰውን ውጫዊ ገጽታ በማየት አትፍረዱ (5:06)

a ተጨማሪ ሐሳብ 6 ለሌሎች ያለን ፍቅር ከተላላፊ በሽታዎች ጋር በተያያዘ ጥንቃቄ እንድናደርግ የሚያነሳሳን እንዴት እንደሆነ ያብራራል።

b ተጨማሪ ሐሳብ 7 ከገንዘብና ከሕግ ነክ ጉዳዮች ጋር በተያያዘ አለመግባባት ሲያጋጥም እንዴት መፍታት እንዳለብን ያብራራል።