ምዕራፍ 57 ከባድ ኃጢአት ብትፈጽም ምን ማድረግ ይኖርብሃል? አጫውት ከባድ ኃጢአት ብትፈጽም ምን ማድረግ ይኖርብሃል? ይቅርታ፣ ማጫወቻው መሥራት አልቻለም። ይህን ቪዲዮ አውርድ ጽሑፉን አሳይ ጽሑፉን ደብቅ ዲጂታል እትም በወረቀት የሚታተመው ይሖዋን ከልብ የምትወድና እሱን ላለማሳዘን የቻልከውን ያህል ጥረት የምታደርግ ቢሆንም አልፎ አልፎ ስህተት መሥራትህ አይቀርም። ይሁንና አንዳንድ ስህተቶች ከሌሎቹ የበለጠ ክብደት አላቸው። (1 ቆሮንቶስ 6:9, 10) ከባድ ኃጢአት ከፈጸምክ ይሖዋ ለአንተ ያለው ፍቅር እንደማይለወጥ እንዲሁም ይቅር ሊልህና ሊረዳህ ፈቃደኛ እንደሆነ አስታውስ። 1. ይሖዋ ይቅር እንዲለን ምን ማድረግ ይኖርብናል? ይሖዋን የሚወዱ ሰዎች ከባድ ኃጢአት እንደፈጸሙ ሲገነዘቡ ከልብ እንደሚያዝኑ የታወቀ ነው። ይሁንና ይሖዋ ለሕዝቡ የገባውን ቃል ማስታወሳቸው ያጽናናቸዋል። ይሖዋ “ኃጢአታችሁ እንደ ደም ቢቀላ እንደ በረዶ ይነጣል” ብሏል። (ኢሳይያስ 1:18) ከልባችን ንስሐ ከገባን ይሖዋ ሙሉ በሙሉ ይቅር ይለናል። ንስሐ እንደገባን ማሳየት የምንችለው እንዴት ነው? በፈጸምነው ኃጢአት ከልብ ማዘን፣ መጥፎ ድርጊታችንን ማቆምና ይሖዋ ይቅር እንዲለን መለመን ይኖርብናል። ከዚያም ኃጢአት ወደመፈጸም የመራንን የተሳሳተ አስተሳሰብ ወይም ልማድ ለማስወገድ እንዲሁም ከይሖዋ መሥፈርቶች ጋር ተስማምተን ለመኖር ከፍተኛ ጥረት ማድረጋችን አስፈላጊ ነው።—ኢሳይያስ 55:6, 7ን አንብብ። 2. ኃጢአት ስንሠራ ይሖዋ በሽማግሌዎች አማካኝነት የሚረዳን እንዴት ነው? ይሖዋ ከባድ ኃጢአት ከፈጸምን ‘የጉባኤ ሽማግሌዎችን እንድንጠራ’ ነግሮናል። (ያዕቆብ 5:14, 15ን አንብብ።) እነዚህ የተሾሙ ወንዶች ይሖዋንና ሕዝቦቹን ይወዳሉ። በተጨማሪም ኃጢአት የፈጸሙ ሰዎች ከይሖዋ ጋር ያላቸውን ዝምድና ማደስ እንዲችሉ ለመርዳት በቂ ሥልጠና አግኝተዋል።—ገላትያ 6:1 ከባድ ኃጢአት ስንፈጽም ሽማግሌዎች የሚረዱን እንዴት ነው? ሁለት ወይም ሦስት ሽማግሌዎች በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ተመሥርተው እርማት ይሰጡናል። በተጨማሪም ዳግመኛ ኃጢአት ከመፈጸም እንድንርቅ የሚረዳ ጠቃሚ ሐሳብ ወይም ማበረታቻ ያካፍሉናል። ሽማግሌዎች ጉባኤውን ከጎጂ ተጽዕኖ ለመጠበቅ ሲሉ፣ ከባድ ኃጢአት ፈጽመው ንስሐ ለመግባት ፈቃደኛ ያልሆኑ ሰዎች ከጉባኤው እንዲወገዱ ያደርጋሉ። ጠለቅ ያለ ጥናት ከባድ ኃጢአት ስንፈጽም ይሖዋ ስለሚሰጠን እርዳታ ያለህን ግንዛቤና አድናቆት እንድታሳድግ የሚረዳ ሐሳብ እንመለከታለን። 3. ኃጢአታችንን መናዘዛችን ፈውስ እንድናገኝ ይረዳናል ማንኛውንም ኃጢአት ስንፈጽም ይሖዋን ስለምናሳዝን ኃጢአታችንን ለእሱ መናዘዛችን ተገቢ ነው። መዝሙር 32:1-5ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተለው ጥያቄ ላይ ተወያዩ፦ የፈጸምነውን ኃጢአት ከመሸፋፈን ይልቅ ለይሖዋ መናዘዛችን የተሻለ የሆነው ለምንድን ነው? ኃጢአታችንን ለይሖዋ ከመናዘዝ በተጨማሪ የሽማግሌዎችን እርዳታ መጠየቃችን እረፍት ያስገኝልናል። ቪዲዮውን ተመልከቱ፤ ከዚያም በሚከተለው ጥያቄ ላይ ተወያዩ፦ ቪዲዮ፦ “ይሖዋ የሚወዳቸውን ይገሥጻል” (3:01) በቪዲዮው ላይ ሽማግሌዎች ካነንን ወደ ይሖዋ እንዲመለስ የረዱት እንዴት ነው? የፈጸምነውን ኃጢአት ለሽማግሌዎች በግልጽና በሐቀኝነት መናገራችን አስፈላጊ ነው፤ ዋነኛ ዓላማቸው እኛን መርዳት ነው። ያዕቆብ 5:16ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተለው ጥያቄ ላይ ተወያዩ፦ ሐቀኛ መሆናችን ሽማግሌዎች እኛን መርዳት ቀላል እንዲሆንላቸው የሚያደርገው እንዴት ነው? ኃጢአትህን ተናዘዝ፣ ለሽማግሌዎች በሐቀኝነት ተናገር እንዲሁም ይሖዋ በፍቅር ተነሳስቶ የሚያደርግልህን እርዳታ ተቀበል 4. ይሖዋ ለኃጢአተኞች ምሕረት ያደርጋል ከባድ ኃጢአት የፈጸመ ሰው ከይሖዋ መሥፈርቶች ጋር ተስማምቶ ለመኖር ፈቃደኛ ካልሆነ ከጉባኤው ይወገዳል። እንዲህ ካለው ሰው ጋር ጊዜ አናሳልፍም። አንደኛ ቆሮንቶስ 5:6, 11ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተለው ጥያቄ ላይ ተወያዩ፦ ጥቂት እርሾ ሊጡን ሁሉ እንደሚያቦካው ሁሉ ንስሐ ከማይገባ ኃጢአተኛ ጋር ጊዜ ማሳለፍም በጉባኤ ውስጥ ባሉት ላይ ምን ጉዳት ይኖረዋል? ይሖዋ ፍጹም ላልሆኑ ኃጢአተኞች ምሕረት ያሳያል፤ ሽማግሌዎችም ከጉባኤ የተወገዱትን ለመርዳት ጥረት በማድረግ የእሱን ምሳሌ ይከተላሉ። ብዙዎች የተሰጣቸው ተግሣጽ ቢያሳዝናቸውም ወደ ልቦናቸው እንዲመለሱ ስለረዳቸው ወደ ጉባኤው ተመልሰዋል።—መዝሙር 145:5 • ይሖዋ ኃጢአት የፈጸሙ ሰዎችን የሚይዝበት መንገድ ፍትሐዊ፣ መሐሪና አፍቃሪ መሆኑን የሚያሳየው እንዴት ነው? 5. ንስሐ ከገባን ይሖዋ ይቅር ይለናል ኢየሱስ፣ ይሖዋ ንስሐ ለገባ ኃጢአተኛ ያለውን አመለካከት የሚያሳይ ምሳሌ ተናግሯል። ሉቃስ 15:1-7ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተለው ጥያቄ ላይ ተወያዩ፦ ይህ ጥቅስ ስለ ይሖዋ ምን ያስተምርሃል? ሕዝቅኤል 33:11ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተለው ጥያቄ ላይ ተወያዩ፦ ንስሐ መግባት የትኛውን አስፈላጊ እርምጃ መውሰድን ይጨምራል? ልክ እንደ አንድ እረኛ ይሖዋም ለበጎቹ ከልብ ያስባል አንዳንዶች እንዲህ ይላሉ፦ “የፈጸምኩትን ኃጢአት ለሽማግሌዎች ብናገር ከጉባኤ እወገዳለሁ ብዬ እፈራለሁ።” እንዲህ ለሚሰማው ሰው ምን ልትለው ትችላለህ? ማጠቃለያ ከባድ ኃጢአት ስንፈጽም ከልባችን ካዘንን እና መጥፎ ድርጊታችንን ለመተው ቁርጥ ውሳኔ ካደረግን ይሖዋ ይቅር ይለናል። ክለሳ ኃጢአታችንን ለይሖዋ መናዘዛችን ጥሩ የሆነው ለምንድን ነው? ይሖዋ ኃጢአታችንን ይቅር እንዲል ከፈለግን ምን ማድረግ ይኖርብናል? ከባድ ኃጢአት ከፈጸምን የሽማግሌዎችን እርዳታ ለማግኘት ጥረት ማድረግ ያለብን ለምንድን ነው? ምዕራፉ የተጠናቀቀበት ቀን፦ ግብ የጉባኤህን ሽማግሌዎች በደንብ ለማወቅ ጥረት አድርግ። ሌላ፦ ሌላ ግብ ምርምር አድርግ አንድ ሰው በኢሳይያስ 1:18 ላይ የተገለጸውን የይሖዋን ምሕረት በሕይወቱ ማየት የቻለው እንዴት ነው? የይሖዋን ምሕረት ፈጽሞ አትጠራጠሩ (5:02) ተመለስ ቀጥል አትም አጋራ አጋራ ከባድ ኃጢአት ብትፈጽም ምን ማድረግ ይኖርብሃል? ለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ ከባድ ኃጢአት ብትፈጽም ምን ማድረግ ይኖርብሃል? የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ከባድ ኃጢአት ብትፈጽም ምን ማድረግ ይኖርብሃል? https://cms-imgp.jw-cdn.org/img/p/1102021257/univ/art/1102021257_univ_sqr_xl.jpg lff ትምህርት 57