ችግርና ስቃይ የሚወገደው መቼ ነው? አጫውት ችግርና ስቃይ የሚወገደው መቼ ነው? ይቅርታ፣ ማጫወቻው መሥራት አልቻለም። ይህን ቪዲዮ አውርድ ጽሑፉን አሳይ ጽሑፉን ደብቅ መልስህ ምንድን ነው? ይወገዳል? አይወገደም? ወይስ ምናልባት? መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል? “እሱም እንባን ሁሉ ከዓይናቸው ያብሳል፤ ከእንግዲህ ወዲህ ሞት አይኖርም፤ ሐዘንም ሆነ ጩኸት እንዲሁም ሥቃይ ከእንግዲህ ወዲህ አይኖርም።”—ራእይ 21:3, 4 አዲስ ዓለም ትርጉም ይህን ማወቅህ ለአንተ ምን ጥቅም አለው? በሰው ልጆች ላይ ለሚደርሱት ችግሮች መንስኤው አምላክ እንዳልሆነ ማረጋገጫ ይሰጥሃል።—ያዕቆብ 1:13 መከራ ሲደርስብህ አምላክ እንደሚያዝንልህ ስለምታውቅ ትጽናናለህ።—ዘካርያስ 2:8 ሁሉም ዓይነት መከራ እንደሚወገድ ተስፋ እንድታደርግ ይረዳሃል።—መዝሙር 37:9-11. መጽሐፍ ቅዱስ በሚናገረው ነገር ላይ እምነት መጣል እንችላለን? አዎ፣ ቢያንስ ሁለት ምክንያቶችን መጥቀስ ይቻላል፦ አምላክ መከራንና ኢፍትሐዊነትን ይጠላል። በመጽሐፍ ቅዱስ ዘመን፣ ይሖዋ አምላክ በሕዝቦቹ ላይ ግፍ ሲፈጸም ምን እንደተሰማው እስቲ እንመልከት። ሕዝቡ “በሚጨቁኗቸውና በሚያንገላቷቸው ሰዎች የተነሳ ሲቃትቱ” አምላክ እንዳዘነ መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል።—መሳፍንት 2:18 አምላክ በሌሎች ላይ ጉዳት የሚያደርሱ ሰዎችን ይጠላል። ለምሳሌ ያህል፣ “ንጹሕ ደም የሚያፈሱ እጆች” በአምላክ ዘንድ የተጠሉ እንደሆኑ መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል።—ምሳሌ 6:16, 17 አምላክ በግለሰብ ደረጃ ያስብልናል። አንድ ሰው መከራ አጋጥሞት ‘ጭንቀትና ሥቃይ’ ሲሰማው ይሖዋም የዚህ ሰው ‘ጭንቀትና ሥቃይ’ ይሰማዋል።—2 ዜና መዋዕል 6:29, 30 ይሖዋ በመንግሥቱ አማካኝነት የእያንዳንዱን ሰው መከራ በቅርቡ ያስወግዳል። (ማቴዎስ 6:9, 10) እስከዚያው ግን እሱን ከልብ የሚፈልጉ ሰዎችን በደግነት ያጽናናቸዋል።—የሐዋርያት ሥራ 17:27፤ 2 ቆሮንቶስ 1:3, 4 ምን ይመስልሃል? አምላክ መከራ እንዲኖር የፈቀደው ለምንድን ነው? መጽሐፍ ቅዱስ ለዚህ ጥያቄ የሚሰጠው መልስ ሮም 5:12 እና 2 ጴጥሮስ 3:9 ላይ ይገኛል። እነዚህንስ አይተሃቸዋል? ስለ እኛ መጽሐፍ ቅዱስን መማር የሚኖርብን ለምንድን ነው? መጽሐፍ ቅዱስ፣ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ለሚያሳስቧቸው ጥያቄዎች መልስ ይሰጣል። አንተስ ለጥያቄዎችህ መልስ ማግኘት ትፈልጋለህ? የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርቶች የመጽሐፍ ቅዱስ ኮርሳችንን ለምን አትሞክረውም? አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ ኮርስ ከአስተማሪ ጋር። አትም አጋራ አጋራ ችግርና ስቃይ የሚወገደው መቼ ነው? መጻሕፍትና ብሮሹሮች ችግርና ስቃይ የሚወገደው መቼ ነው? የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ችግርና ስቃይ የሚወገደው መቼ ነው? https://cms-imgp.jw-cdn.org/img/p/1102013410/univ/art/1102013410_univ_sqr_xl.jpg T-34 ገጽ 2-4