1. አምላክ ማን ነው? አጫውት 1. አምላክ ማን ነው? ይቅርታ፣ ማጫወቻው መሥራት አልቻለም። ይህን ቪዲዮ አውርድ ጽሑፉን አሳይ ጽሑፉን ደብቅ 1 አምላክ ማን ነው? ‘ሁሉንም ነገሮች ፈጥረሃል።’—ራእይ 4:11 መጽሐፍ ቅዱስ ስለ አምላክ ምን ያስተምረናል? ራእይ 15:3 አምላክ ሁሉን ቻይ ከመሆኑም ሌላ በጽንፈ ዓለም ውስጥ ከማንም በላይ ኃያል ነው። መዝሙር 90:2 አምላክ መጀመሪያም መጨረሻም የለውም። ማቴዎስ 6:9 አምላክ አባታችን ነው። ደስተኞች እንድንሆን ይፈልጋል። የሐዋርያት ሥራ 17:27 አምላክ ወደ እኛ መቅረብ ይፈልጋል። 2 አምላክ ስም አለው “ይሖዋ . . . ለዘላለም ስሜ ነው።”—ዘፀአት 3:15 የአምላክን ስም መጠቀም ያለብን ለምንድን ነው? መዝሙር 83:18 አምላክ ስሙ ይሖዋ እንደሆነ ገልጾልናል። “እግዚአብሔር፣” “አምላክ” እና “ጌታ” የሚሉት ቃላት መጠሪያ ስሞች አይደሉም። “ንጉሥ” እና “ፕሬዚዳንት” እንደሚሉት ያሉ የማዕረግ ስሞች ናቸው። ይሖዋ በስሙ እንድትጠቀም ይፈልጋል። ዘፀአት 3:14 የአምላክ ስም “እንዲሆን ያደርጋል” የሚል ትርጉም አለው። ሁሉንም ነገር የፈጠረው ይሖዋ ስለሆነ የገባውን ቃልም ሆነ ዓላማውን መፈጸም ይችላል። 3 ይሖዋ ይወደናል “አምላክ ፍቅር ነው።”—1 ዮሐንስ 4:8 አምላክ ለእኛ ያለውን ፍቅር የሚያሳየው እንዴት ነው? ዘፀአት 34:6፤ መዝሙር 37:28 አምላክ መሐሪና ሩኅሩኅ ነው። በተጨማሪም እውነትንና ፍትሕን ይወዳል። መዝሙር 86:5 ይቅር ባይ ነው። 2 ጴጥሮስ 3:9 ታጋሽ ነው። ራእይ 15:4 ታማኝ ነው። 4 አምላክ ስለ አንተ ያስባል “የሚያስጨንቃችሁንም ነገር ሁሉ በእሱ ላይ ጣሉ፤ ምክንያቱም እሱ ስለ እናንተ ያስባል።”—1 ጴጥሮስ 5:7 አምላክ ስለ አንተ እንደሚያስብ እንዴት ማወቅ ትችላለህ? መዝሙር 37:9-11 አምላክ መከራን እንደሚያስወግድ እንዲሁም ክፋት ያስከተላቸውን መጥፎ ውጤቶች ሙሉ በሙሉ እንደሚያስቀር ቃል ገብቷል። ያዕቆብ 4:8 ይሖዋ ወደ እሱ እንድትቀርብ ይፈልጋል። ዮሐንስ 17:3 ስለ አምላክ ይበልጥ ስታውቅ እየወደድከው ትሄዳለህ። ተመለስ ቀጥል አትም አጋራ አጋራ 1. አምላክ ማን ነው? Summary 1: አምላክ ማን ነው? የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ Summary 1: አምላክ ማን ነው? https://assetsnffrgf-a.akamaihd.net/assets/ct/1add6d1d93/images/syn_placeholder_sqr.png bhssm ገጽ 1