10. መላእክትንና አጋንንትን በተመለከተ እውነታው ምንድን ነው? አጫውት 10. መላእክትንና አጋንንትን በተመለከተ እውነታው ምንድን ነው? ይቅርታ፣ ማጫወቻው መሥራት አልቻለም። ይህን ቪዲዮ አውርድ ጽሑፉን አሳይ ጽሑፉን ደብቅ 1 መላእክት የአምላክ ቤተሰብ አባላት ናቸው “እናንተ ብርቱዎችና ኃያላን መላእክቱ ሁሉ፣ ይሖዋን አወድሱ።”—መዝሙር 103:20 ስለ መላእክት ምን የምናውቀው ነገር አለ? ኢዮብ 38:4-7 ይሖዋ ምድርን ከመፍጠሩ በፊት መላእክትን ፈጥሯል። ራእይ 5:11 በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ መላእክት አሉ። 1 ጴጥሮስ 1:11, 12 መላእክት፣ ይሖዋ ለምድር ካለው ዓላማ ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን ለማወቅ ይጓጓሉ። ሉቃስ 15:10 መላእክት በተለይ አምላክን የሚያገለግሉ ሰዎችን በትኩረት ይከታተላሉ። 2 መላእክት የአምላክን አገልጋዮች ይረዳሉ “የይሖዋ መልአክ በሚፈሩት ዙሪያ ይሰፍራል፤ ደግሞም ይታደጋቸዋል።”—መዝሙር 34:7 መላእክት ሰዎችን ሊረዱ ይችላሉ የምንለው ለምንድን ነው? ዘፍጥረት 19:15, 16፤ ዳንኤል 6:22፤ ሉቃስ 22:43፤ የሐዋርያት ሥራ 12:6-11 መላእክት ሎጥን፣ ዳንኤልን፣ ኢየሱስንና ጴጥሮስን ረድተዋል። ዕብራውያን 1:7, 14 ይሖዋ በዛሬው ጊዜ ያሉ አገልጋዮቹን ለመርዳትና ለመጠበቅ በመላእክቱ ይጠቀማል። 3 ክፉ መላእክት ሊጎዱን ይሞክራሉ “ሰይጣን መግቢያ ቀዳዳ እንዳያገኝ ነው፤ እሱ የሚሸርበውን ተንኮል እናውቃለንና።”—2 ቆሮንቶስ 2:11 አጋንንት እነማን ናቸው? አደገኛ የሆኑትስ ለምንድን ነው? ራእይ 12:9 አንድ መልአክ በይሖዋ ላይ ዓምጿል። ይህ መልአክ ሰይጣን ተብሎ ተጠርቷል። ዘፍጥረት 6:2 በኖኅ ዘመን አንዳንድ መላእክት በአምላክ ላይ በማመፅ ወደ ምድር መጥተዋል። ማቴዎስ 9:34 እነዚህ መላእክት ከሰይጣን ጋር በመተባበር አጋንንት ሆነዋል። ዘዳግም 18:10, 11 አጋንንት የተለያዩ ዘዴዎችን በመጠቀም ሰዎችን ለማታለልና ለመጉዳት ይሞክራሉ። 4 ሰይጣንን እና አጋንንቱን መቃወም ትችላለህ “ዲያብሎስን . . . ተቃወሙት፤ እሱም ከእናንተ ይሸሻል።”—ያዕቆብ 4:7 ሰይጣንን እና አጋንንቱን ለመቃወም ጥረት በምታደርግበት ጊዜ የይሖዋን እርዳታ ማግኘት የምትችለው እንዴት ነው? የሐዋርያት ሥራ 19:19 አስማትንና አጋንንትን ምንም ጉዳት እንደማያመጡ ወይም አስደሳች እንደሆኑ አድርገው የሚያቀርቡ ነገሮችን በሙሉ አስወግድ። ኤፌሶን 6:16, 18 መጽሐፍ ቅዱስን በማጥናት እምነትህን አጠናክር፤ እንዲሁም የአምላክን ጥበቃ ለማግኘት ጸልይ። ምሳሌ 18:10 በምትጸልይበት ጊዜ የይሖዋን ስም ተጠቀም። ተመለስ ቀጥል አትም አጋራ አጋራ 10. መላእክትንና አጋንንትን በተመለከተ እውነታው ምንድን ነው? Summary 10: መላእክትንና አጋንንትን በተመለከተ እውነታው ምንድን ነው? የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ Summary 10: መላእክትንና አጋንንትን በተመለከተ እውነታው ምንድን ነው? https://assetsnffrgf-a.akamaihd.net/assets/ct/1add6d1d93/images/syn_placeholder_sqr.png bhssm ገጽ 10