11. መከራና ሥቃይ የበዛው ለምንድን ነው? አጫውት 11. መከራና ሥቃይ የበዛው ለምንድን ነው? ይቅርታ፣ ማጫወቻው መሥራት አልቻለም። ይህን ቪዲዮ አውርድ ጽሑፉን አሳይ ጽሑፉን ደብቅ 1 ይሖዋ በሰው ልጆች ላይ መከራ አያመጣም “‘ሁሉን ቻይ የሆነው አምላክ በደል ይፈጽማል’ ብሎ ማሰብ የማይመስል ነገር ነው።”—ኢዮብ 34:10 በዓለም ላይ መከራ የበዛው ለምንድን ነው? 1 ዮሐንስ 5:19 የዚህ ዓለም ገዢ ሰይጣን ዲያብሎስ ነው። መክብብ 8:9 የሰው ልጆች፣ አንዳቸው ሌላውን ያሠቃያሉ። መክብብ 9:11 አንዳንድ ጊዜ፣ ሰዎች በመጥፎ ጊዜ የማይሆን ቦታ ላይ በመገኘታቸው መከራና ሥቃይ ይደርስባቸዋል። 1 ጴጥሮስ 5:7 ይሖዋ ሰዎችን በጣም ይወዳል። ሰዎች እንዲሠቃዩ አይፈልግም። 2 ሰይጣን በይሖዋ የመግዛት መብት ላይ ጥያቄ አንስቷል “አምላክ . . . ዓይኖቻችሁ እንደሚገለጡና መልካምና ክፉን በማወቅ ረገድ እንደ አምላክ እንደምትሆኑ ስለሚያውቅ ነው።”—ዘፍጥረት 3:5 ይሖዋ፣ ሰይጣንን ወዲያውኑ ያላጠፋው ለምንድን ነው? ዘፍጥረት 3:2-5 ሰይጣን አምላክን ‘ክፉ ገዢ ነው’ ሲል ከሶታል። ሰይጣን፣ የሰው ልጆች ትክክልና ስህተት የሆነውን ነገር በራሳቸው መወሰን እንደሚችሉ እንዲሰማቸው ማድረግ ፈልጎ ነበር። አምላክ፣ ሰይጣን የሰነዘረው ክስ ውሸት መሆኑ እንዲረጋገጥ ሲል ጊዜ ሰጥቷል። ኢዮብ 38:7 ሰይጣን ይሖዋን የከሰሰው በሚሊዮን በሚቆጠሩ መላእክት ፊት ነው። 3 ሰይጣን የሰነዘረው ክስ ውሸት መሆኑ ተረጋግጧል “[ሰው] አካሄዱን እንኳ በራሱ አቃንቶ መምራት አይችልም።”—ኤርምያስ 10:23 ይሖዋ፣ በሰው ልጆች ላይ ለረጅም ጊዜ መከራ እንዲደርስ የፈቀደው ለምንድን ነው? ኢሳይያስ 55:9 የሰው ልጆች የተለያዩ የአገዛዝ ሥርዓቶችን ቢሞክሩም ያለአምላክ እርዳታ ምድርን በተሳካ ሁኔታ ማስተዳደር አልቻሉም። 2 ጴጥሮስ 3:9, 10 ይሖዋ ታጋሽ ነው፤ እሱን ማወቅ እንዲሁም ገዢያችን እንዲሆን እንደምንፈልግ ማሳየት የምንችልበት አጋጣሚ ሰጥቶናል። 1 ዮሐንስ 3:8 ይሖዋ፣ በኢየሱስ አማካኝነት ሰይጣን ያመጣውን መጥፎ ነገር ሁሉ ያስወግዳል። 4 የመምረጥ ነፃነትህን ተጠቅመህ ይሖዋን ለማገልገል ቁርጥ ውሳኔ አድርግ “ልጄ ሆይ፣ ለሚነቅፈኝ መልስ መስጠት እችል ዘንድ ጥበበኛ ሁን።”—ምሳሌ 27:11 ይሖዋ እሱን እንድናገለግለው የማያስገድደን ለምንድን ነው? ምሳሌ 30:24 እንስሳት የሚንቀሳቀሱት በደመ ነፍስ ነው፤ እኛ ግን የመምረጥ ነፃነት ተሰጥቶናል። ይሖዋን የምናገለግለው በምርጫችን ነው። ማቴዎስ 22:37, 38 ይሖዋ በፍቅር ተነሳስተን እንድናገለግለው ይፈልጋል። ተመለስ ቀጥል አትም አጋራ አጋራ 11. መከራና ሥቃይ የበዛው ለምንድን ነው? ክለሳ 11: መከራና ሥቃይ የበዛው ለምንድን ነው? የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ክለሳ 11: መከራና ሥቃይ የበዛው ለምንድን ነው? https://assetsnffrgf-a.akamaihd.net/assets/ct/1add6d1d93/images/syn_placeholder_sqr.png bhssm ገጽ 11