12. የአምላክ ወዳጅ መሆን የምትችለው እንዴት ነው? አጫውት 12. የአምላክ ወዳጅ መሆን የምትችለው እንዴት ነው? ይቅርታ፣ ማጫወቻው መሥራት አልቻለም። ይህን ቪዲዮ አውርድ ጽሑፉን አሳይ ጽሑፉን ደብቅ 1 የይሖዋ ወዳጆች እሱን ይታዘዛሉ “ድምፄን ስሙ፤ እኔም አምላካችሁ እሆናለሁ፤ እናንተም ሕዝቤ ትሆናላችሁ።”—ኤርምያስ 7:23 የአምላክ ወዳጅ መሆን ይቻላል? ዘፍጥረት 22:18፤ ያዕቆብ 2:23 አብርሃም የይሖዋ ወዳጅ የተባለው እሱን ይሰማ ስለነበርና በእሱ ላይ እምነት ስለነበረው ነው። 2 ዜና መዋዕል 16:9 ይሖዋ ታዛዥ የሆኑ ሰዎችን ይረዳል። መዝሙር 25:14፤ 32:8 ይሖዋ ለወዳጆቹ ማስተዋል ይሰጣል። መዝሙር 55:22 ይሖዋ ወዳጆቹን ይጠብቃል። 2 ኢዮብ የአምላክ ወዳጅ ነበር፤ እስከ መጨረሻው ለእሱ ታማኝ ሆኗል “ኢዮብ ይህ ሁሉ ቢደርስበትም ኃጢአት አልሠራም ወይም አምላክን በደል ሠርቷል ብሎ አልወነጀለም።”—ኢዮብ 1:22 ሰይጣን በኢዮብ ላይ ጥቃት የሰነዘረው እንዴት ነው? በዚህ ጊዜ ኢዮብ ምን አደረገ? ኢዮብ 1:10, 11 ሰይጣን፣ ኢዮብ ራስ ወዳድ እንደሆነና ለአምላክ ፍቅር እንደሌለው ተናግሯል። ኢዮብ 1:12-19፤ 2:7 ሰይጣን በኢዮብ ላይ ጥቃት እንዲሰነዝርና የነበረውን ነገር በሙሉ እንዲያሳጣው ይሖዋ ፈቅዶለታል፤ ከዚህም ሌላ ሰይጣን፣ ኢዮብን በከባድ በሽታ አሠቃይቶታል። ኢዮብ 27:5 ኢዮብ ብዙ መከራ የደረሰበት ለምን እንደሆነ ባያውቅም ለይሖዋ ታማኝ ሆኗል። 3 ሰይጣን ከይሖዋ እንድትርቅ ለማድረግ ይሞክራል “[ሰው] ለሕይወቱ ሲል ያለውን ነገር ሁሉ ይሰጣል።”—ኢዮብ 2:4 ሰይጣን ከይሖዋ ጋር የመሠረትነው ወዳጅነት እንዲቋረጥ ለማድረግ የሚሞክረው እንዴት ነው? 2 ቆሮንቶስ 11:14 ሰይጣን እኛን በማታለል ይሖዋን እንዳንታዘዝ ለማድረግ ይሞክራል። ምሳሌ 24:10 ይሖዋን ለማገልገል ብቁ እንዳልሆንን እንዲሰማን ለማድረግ ይሞክራል። 1 ጴጥሮስ 5:8 ሰይጣን ስደት ያደርስብናል። ምሳሌ 27:11 ይሖዋን በመታዘዝና የእሱ ታማኝ ወዳጅ በመሆን ሰይጣን ውሸታም እንደሆነ ማሳየት ትችላለህ። 4 ይሖዋን የምንታዘዘው እሱን ስለምንወደው ነው “አምላክን መውደድ ማለት ትእዛዛቱን መጠበቅ ማለት ነው።”—1 ዮሐንስ 5:3 የይሖዋ ወዳጅ መሆን የምትችለው እንዴት ነው? ዘዳግም 6:5 አምላክን መውደድህ ታዛዥ እንድትሆን ይረዳሃል። ኢሳይያስ 48:17, 18 ይሖዋን መታዘዝ ምንጊዜም ጥቅም ያስገኝልሃል። ዘዳግም 30:11-14 ይሖዋ ከአቅምህ በላይ የሆነ ነገር እንድታደርግ እንደማይጠይቅህ እርግጠኛ ሁን። ፊልጵስዩስ 4:13 ትክክል የሆነውን ነገር አድርግ፤ ይሖዋም እንዲህ ለማድረግ የሚያስችል ኃይል ይሰጥሃል። ተመለስ ቀጥል አትም አጋራ አጋራ 12. የአምላክ ወዳጅ መሆን የምትችለው እንዴት ነው? ክለሳ 12: የአምላክ ወዳጅ መሆን የምትችለው እንዴት ነው? የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ክለሳ 12: የአምላክ ወዳጅ መሆን የምትችለው እንዴት ነው? https://assetsnffrgf-a.akamaihd.net/assets/ct/1add6d1d93/images/syn_placeholder_sqr.png bhssm ገጽ 12