13. አምላክ ለሰጠህ ሕይወት አድናቆት ይኑርህ

13. አምላክ ለሰጠህ ሕይወት አድናቆት ይኑርህ

1 አምላክ ለሰጠህ ሕይወት አድናቆት ይኑርህ

“የሕይወት ምንጭ ከአንተ ዘንድ ነው።”—መዝሙር 36:9

ለሕይወት አድናቆት እንዳለን የምናሳየው እንዴት ነው?

2 ሕይወትና ደም

“የሥጋ ሁሉ ሕይወት ደሙ ነውና፤ ምክንያቱም በውስጡ ሕይወት አለ።”—ዘሌዋውያን 17:14

አምላክ ለሕይወትና ለደም ምን አመለካከት አለው?

3 ይሖዋ ደም ለምን ዓላማዎች እንዲውል ፈቅዷል?

“የኢየሱስ ደም ከኃጢአት ሁሉ ያነጻናል።”—1 ዮሐንስ 1:7

የኢየሱስ መሥዋዕት ምን አጋጣሚ ከፍቶልናል?

  • ዘሌዋውያን 17:11

    በጥንት ዘመን እስራኤላውያን ኃጢአት በሚሠሩበት ጊዜ መሥዋዕት የሚሆን እንስሳ በካህኑ ፊት ያቀርቡ ነበር፤ ካህኑ ደግሞ የእንስሳውን ደም መሠዊያው ላይ ይረጨዋል፤ በዚህ መንገድ እስራኤላውያን የይሖዋን ይቅርታ ማግኘት ይችሉ ነበር።

  • ማቴዎስ 20:28፤ ዕብራውያን 9:11-14

    ኢየሱስ ወደ ምድር በመጣበት ጊዜ የኃጢአት ይቅርታ እንድናገኝ ሲል ሕይወቱን ወይም ደሙን መሥዋዕት አድርጎ ሰጥቷል፤ በመሆኑም የእንስሳ መሥዋዕት እንዲቀርብ የሚያዘው ሕግ ቀርቷል።

  • ዮሐንስ 3:16

    ይሖዋ፣ የኢየሱስ ሕይወት በጣም ውድ ከመሆኑ የተነሳ ከሞት ካስነሳው በኋላ በኢየሱስ የሚያምኑ ሰዎች ሁሉ ለዘላለም መኖር የሚችሉበት አጋጣሚ እንዲያገኙ አድርጓል።