14. ቤተሰብህ ደስተኛ ሊሆን የሚችለው እንዴት ነው?

14. ቤተሰብህ ደስተኛ ሊሆን የሚችለው እንዴት ነው?

1 ቤተሰብን ያቋቋመው ይሖዋ ነው

“በዚህም ምክንያት በአብ ፊት ለመጸለይ እንበረከካለሁ፤ በሰማይና በምድር ያለ እያንዳንዱ ቤተሰብ ስያሜውን ያገኘው ከእሱ ነው።”—ኤፌሶን 3:14, 15

ቤተሰብህ ደስተኛ ሊሆን የሚችለው እንዴት ነው?

  • ዘፍጥረት 1:26-28

    የመጀመሪያውን ቤተሰብ ያቋቋመው ይሖዋ ነው።

  • ኤፌሶን 5:1, 2

    የቤተሰብን ሕይወት አስደሳች ለማድረግ ቁልፉ ይሖዋንና ኢየሱስን መምሰል ነው።

2 ጥሩ ባል ወይም ጥሩ ሚስት መሆን የሚቻለው እንዴት ነው?

‘ከእናንተ እያንዳንዱ ሚስቱን ይውደድ፤ በሌላ በኩል ደግሞ ሚስት ባሏን በጥልቅ ታክብር።’—ኤፌሶን 5:33

ባልና ሚስት አንዳቸው ለሌላው ምን ዓይነት ባሕርይ ሊያሳዩ ይገባል?

  • ኤፌሶን 5:22-29

    ባል ቤተሰቡን የመምራት ኃላፊነት አለበት። በተጨማሪም ሚስቱን መውደድ ይኖርበታል፤ ሚስት ደግሞ ባሏ የሚያደርጋቸውን ውሳኔዎች መደገፍ አለባት።

  • ቆላስይስ 3:19፤ 1 ጴጥሮስ 3:4

    ባልና ሚስት አንዳቸው ለሌላው ደግና አሳቢ መሆን ያስፈልጋቸዋል።

  • 1 ጴጥሮስ 3:1, 2, 7

    ባልና ሚስት እርስ በርስ ሊከባበሩ ይገባል።

  • 1 ጢሞቴዎስ 5:8፤ ቲቶ 2:4, 5

    ባል ለቤተሰቡ የሚያስፈልገውን ነገር ማቅረብ ይኖርበታል። ሚስት ደግሞ ቤተሰቧን መንከባከብ አለባት።

3 ጥሩ ወላጅ መሆን የሚቻለው እንዴት ነው?

“ልጆቻችሁን አታስመርሯቸው፤ ከዚህ ይልቅ በይሖዋ ተግሣጽና ምክር አሳድጓቸው።”—ኤፌሶን 6:4

ወላጆች ምን ኃላፊነት አለባቸው?

  • ዘዳግም 6:4-9፤ ምሳሌ 22:6

    ልጆቻችሁን ስለ ይሖዋ ለማስተማር ጊዜ መመደብ ይኖርባችኋል። ከሕፃንነታቸው ጀምሮ የይሖዋ ወዳጅ መሆን እንዲችሉ በትዕግሥት እርዷቸው።

  • 1 ጴጥሮስ 5:8

    ልጆቻችሁ ከፆታ ጥቃትም ሆነ ከሌሎች አደገኛ ሁኔታዎች ራሳቸውን መጠበቅ የሚችሉት እንዴት እንደሆነ አስተምሯቸው።

  • ኤርምያስ 30:11፤ ዕብራውያን 12:9-11

    ለልጆቻችሁ ተግሣጽ መስጠት ይኖርባችኋል፤ ሆኖም እንዲህ የምታደርጉት ተበሳጭታችሁ ባላችሁበት ሰዓት ወይም ጭካኔ በሚንጸባረቅበት መንገድ መሆን የለበትም።

4 ልጆች ምን ማድረግ ይጠበቅባቸዋል?

“ልጆች ሆይ፣ . . . ለወላጆቻችሁ ታዘዙ።”—ኤፌሶን 6:1

ልጆች፣ ወላጆቻችሁን መታዘዝ ያለባችሁ ለምንድን ነው?

  • ምሳሌ 23:22-25፤ ቆላስይስ 3:20

    ታዛዦች ከሆናችሁ ይሖዋንና ወላጆቻችሁን ታስደስታላችሁ።

  • 1 ቆሮንቶስ 15:33

    ይሖዋን የሚወዱ ጓደኞች መምረጥ ይኖርባችኋል። እንዲህ ካደረጋችሁ ትክክል የሆነውን ነገር ማድረግ ቀላል ይሆንላችኋል።