15. እውነተኛውን ሃይማኖት ለይቶ ማወቅ የሚቻለው እንዴት ነው?

15. እውነተኛውን ሃይማኖት ለይቶ ማወቅ የሚቻለው እንዴት ነው?

1 እውነተኛውን ሃይማኖት ለይቶ ማወቅ የሚቻልበት መንገድ

“ወደ ሕይወት የሚወስደው በር ግን ጠባብ፣ መንገዱም ቀጭን ነው፤ የሚያገኙትም ጥቂቶች ናቸው።”—ማቴዎስ 7:14

አምላክ የማይቀበለው ሃይማኖት እንዳለ እንዴት እናውቃለን?

  • ማቴዎስ 7:21-23

    አምላክ የሚቀበለው ሁሉንም ሃይማኖቶች አይደለም። ምክንያቱም የአምላክን ፈቃድ የማያደርጉ ሃይማኖቶች አሉ።

  • ማቴዎስ 7:13, 14

    እውነተኛውን ሃይማኖት መከተል የዘላለም ሕይወት ያስገኛል። የሐሰት ሃይማኖትን መከተል ግን ዘላለማዊ ጥፋት ያስከትላል።

  • ማቴዎስ 7:16, 17

    እውነተኛውን ሃይማኖት የሚከተሉ ሰዎችን በሥራቸው መለየት ይቻላል። ሁሉንም ሃይማኖቶች መመርመር አያስፈልግህም፤ መጽሐፍ ቅዱስ የሚናገረውን ማጥናት ብቻ በቂ ነው።

2 አምላክ መመለክ ያለበት እንዴት ነው?

3 የምታምንበትን ነገር ተግባራዊ አድርግ

አምላክ የምታቀርበውን አምልኮ እንዲቀበልህ ከፈለግክ ምን ማድረግ ይኖርብሃል?

  • ያዕቆብ 2:19

    በአምላክ ማመን ብቻ በቂ አይደለም። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኙትን የእሱን ትእዛዛት ተግባራዊ ማድረግ ይኖርብሃል።

  • ኢሳይያስ 52:11፤ ራእይ 17:5

    የሐሰት ሃይማኖት ወይም “ታላቂቱ ባቢሎን” ሰዎች አምላክን እሱ በማይቀበለው መንገድ እንዲያመልኩት ታስተምራለች። የሐሰት ሃይማኖቶች ከሚያስተምሯቸው ትምህርቶች መካከል ሥላሴ፣ እሳታማ ሲኦልና ነፍስ አትሞትም የሚሉት ይገኙበታል።

  • ራእይ 18:4, 8

    ይሖዋ በቅርቡ የሐሰት ሃይማኖቶችን በሙሉ ያጠፋል። ከሐሰት አምልኮ ጋር ንክኪ ያላቸውን ነገሮች በሙሉ ማስወገድ አለብህ።

  • ማርቆስ 10:28-30

    ተቃውሞ ሊያጋጥምህ ይችላል፤ ሆኖም ይሖዋ ፈጽሞ አይተውህም።