16. አምላክን በትክክለኛው መንገድ ለማምለክ ቁርጥ ውሳኔ አድርግ አጫውት 16. አምላክን በትክክለኛው መንገድ ለማምለክ ቁርጥ ውሳኔ አድርግ ይቅርታ፣ ማጫወቻው መሥራት አልቻለም። ይህን ቪዲዮ አውርድ ጽሑፉን አሳይ ጽሑፉን ደብቅ 1 ከሐሰት አምልኮ ራቅ “ከመካከላቸው ውጡና ራሳችሁን ለዩ . . . ርኩስ የሆነውንም ነገር አትንኩ።”—2 ቆሮንቶስ 6:17 ምስሎችን ለአምልኮ መጠቀምና ወደ ሞቱ ሰዎች መጸለይ ስህተት የሆነው ለምንድን ነው? ዘፀአት 20:4, 5፤ 1 ዮሐንስ 5:21 ይሖዋ ምስሎችን ለአምልኮ እንድንጠቀም አይፈልግም። ዘዳግም 18:10-12 ከሞቱ ሰዎች ጋር ለመነጋገር የሚሞክሩ ሰዎች የሚነጋገሩት ከአጋንንት ጋር ነው። 2 በአምላክ ፊት ተቀባይነት ያላቸው ሁሉም በዓላት አይደሉም “በጌታ ዘንድ ተቀባይነት ያለው ነገር ምን እንደሆነ ምንጊዜም መርምራችሁ አረጋግጡ።”—ኤፌሶን 5:10 አንድን በዓል ማክበር ይኖርብህ እንደሆነና እንዳልሆነ መወሰን የምትችለው እንዴት ነው? ሕዝቅኤል 44:23፤ 2 ቆሮንቶስ 6:14, 15 በዓሉ ከጣዖት አምልኮ የመጣ መሆን አለመሆኑን ለማወቅ ሞክር። ዘፀአት 32:2-10 በዓላትን የሚያከብሩ ሰዎች ይህን የሚያደርጉት መልካም ነገር አስበው ቢሆንም በዓሉ አምላክን ላያስደስተው ይችላል። ዳንኤል 3:1-27 ሰዎችን፣ ሰብዓዊ ድርጅቶችን ወይም ብሔራዊ አርማዎችን ከፍ ከፍ የሚያደርጉ በዓላትን ማክበር አይኖርብህም። 1 ጢሞቴዎስ 1:18, 19 የማመዛዘን ችሎታህን ተጠቀም፤ ምንጊዜም በይሖዋ ፊት ጥሩ ሕሊና እንዲኖርህ ጥረት አድርግ። 3 የምታምንበትን ነገር ለሌሎች በአክብሮት አስረዳ “ለእያንዳንዱ ሰው እንዴት መልስ መስጠት እንደሚገባችሁ ታውቁ ዘንድ ንግግራችሁ ምንጊዜም በጨው የተቀመመ ያህል ለዛ ያለው ይሁን።”—ቆላስይስ 4:6 እምነትህን ለሌሎች ማስረዳት ያለብህ እንዴት ነው? ማቴዎስ 7:12 ሌሎች ውሳኔህን እንዲያከብሩልህ እንደምትፈልግ ሁሉ አንተም የእነሱን ውሳኔ አክብር። 2 ጢሞቴዎስ 2:24 ምንጊዜም ለሌሎች አሳቢነት አሳይ፤ የምታምንበትን ነገር ለሌሎች ስታስረዳ መጨቃጨቅ አይኖርብህም። 1 ጴጥሮስ 3:15 የምታምንበትን ነገር በገርነትና በአክብሮት አስረዳ። ዕብራውያን 10:24, 25 በክርስቲያናዊ ስብሰባዎች ላይ ስትገኝ ማበረታቻ የምታገኝ ከመሆኑም ሌላ ስለ እምነትህ ጥያቄ ሲቀርብልህ ምን መልስ መስጠት እንደምትችል ትማራለህ። ተመለስ ቀጥል አትም አጋራ አጋራ 16. አምላክን በትክክለኛው መንገድ ለማምለክ ቁርጥ ውሳኔ አድርግ ክለሳ 16: አምላክን በትክክለኛው መንገድ ለማምለክ ቁርጥ ውሳኔ አድርግ የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ክለሳ 16: አምላክን በትክክለኛው መንገድ ለማምለክ ቁርጥ ውሳኔ አድርግ https://assetsnffrgf-a.akamaihd.net/assets/ct/1add6d1d93/images/syn_placeholder_sqr.png bhssm ገጽ 16