17. ወደ አምላክ የመጸለይ ውድ መብት

17. ወደ አምላክ የመጸለይ ውድ መብት

1 ይሖዋ የምናቀርበውን ጸሎት መስማት ይፈልጋል

“ይሖዋ ለሚጠሩት ሁሉ፣ በእውነት ለሚጠሩት ሁሉ ቅርብ ነው።”—መዝሙር 145:18

ይሖዋ ጸሎታችንን እንዲሰማ ከፈለግን ምን ማድረግ ይኖርብናል?

  • ዕብራውያን 11:6

    እምነት ሊኖረን ይገባል።

  • መዝሙር 138:6

    ትሕትናና አክብሮት ልናሳይ ይገባል።

  • ያዕቆብ 2:26

    የምናደርገው ነገር ከጸሎታችን ጋር የሚስማማ መሆን አለበት።

  • ማቴዎስ 6:7, 8

    የውስጥ ስሜታችንን አውጥተን በመግለጽ ከልብ መጸለይ ይኖርብናል። በጸሎታችን ላይ ተመሳሳይ ቃላት መደጋገም የለብንም።

  • ኢሳይያስ 1:15

    ከአምላክ ፈቃድ ጋር በሚስማማ መንገድ መኖር አለብን።

2 ጸሎትን በተመለከተ ብዙ ጊዜ የሚነሱ ጥያቄዎች

3 ስለ ምን ነገሮች መጸለይ እንችላለን?

“ከፈቃዱ ጋር በሚስማማ ሁኔታ እስከለመንን ድረስ ይሰማናል።”—1 ዮሐንስ 5:14

በጸሎታችን ውስጥ ልንጠቅሳቸው የምንችላቸው ነገሮች

  • ማቴዎስ 6:9, 10

    የይሖዋ ፈቃድ እንዲፈጸም መጸለይ ይኖርብናል።

  • 1 ዜና መዋዕል 29:10-13

    በጸሎታችን ላይ ይሖዋን ማመስገን አለብን።

  • ማቴዎስ 6:11-13

    የሚያስፈልገንን እንዲሁም ያስጨነቀንን ነገር በጸሎት ለአምላክ ልንነግረው እንችላለን።

  • ሉቃስ 11:13

    መንፈስ ቅዱስ ለማግኘት መጸለይ እንችላለን።

  • ያዕቆብ 1:5

    ጥሩ ውሳኔዎችን ማድረግ እንድንችል አምላክ ጥበብ እንዲሰጠን መጸለይ እንችላለን።

  • ፊልጵስዩስ 4:13

    ለመጽናት የሚያስችል ጥንካሬ እንዲሰጠን ወደ አምላክ መጸለይ እንችላለን።

  • ኤፌሶን 1:3, 7

    ለኃጢአታችን ይቅርታ ለማግኘት መጸለይ እንችላለን።

  • የሐዋርያት ሥራ 12:5

    ለሌሎች ሰዎች መጸለይ እንችላለን።

4 ይሖዋ ለጸሎታችን መልስ ይሰጣል

“ጸሎት ሰሚ የሆንከው አምላክ ሆይ፣ ሁሉም ዓይነት ሰው ወደ አንተ ይመጣል።”—መዝሙር 65:2

ይሖዋ ለጸሎታችን መልስ የሚሰጠው እንዴት ነው?