18. ራሴን ለአምላክ መወሰንና መጠመቅ ይኖርብኛል? አጫውት 18. ራሴን ለአምላክ መወሰንና መጠመቅ ይኖርብኛል? ይቅርታ፣ ማጫወቻው መሥራት አልቻለም። ይህን ቪዲዮ አውርድ ጽሑፉን አሳይ ጽሑፉን ደብቅ 1 መጠመቅ ይኖርብኛል? “ውኃ ይኸውና፤ እንዳልጠመቅ የሚከለክለኝ ምን ነገር አለ?”—የሐዋርያት ሥራ 8:36 መጠመቅ ያለብህ ለምንድን ነው? የምትጠመቀውስ እንዴት ነው? መጠመቅህ፣ ለቀድሞው አኗኗርህ እንደሞትክና የአምላክን ፈቃድ ለማድረግ አዲስ ሕይወት እንደጀመርክ ያሳያል። ማቴዎስ 28:19, 20 ይሖዋን ማገልገል ከፈለግክ መጠመቅ ይኖርብሃል። መዝሙር 40:8 መጠመቅህ፣ አምላክን ማገልገል እንደምትፈልግ ያሳያል። ማቴዎስ 3:16 ልክ እንደ ኢየሱስ ሙሉ በሙሉ ውኃ ውስጥ መግባት ወይም መጥለቅ ይኖርብሃል። 2 ይሖዋ ከአቅምህ በላይ የሆነ ነገር አይጠብቅብህም “አምላክን መውደድ ማለት ትእዛዛቱን መጠበቅ ማለት ነውና፤ ትእዛዛቱ ደግሞ ከባድ አይደሉም።”—1 ዮሐንስ 5:3 ራስህን ለይሖዋ መወሰን ሊያስፈራህ የማይገባው ለምንድን ነው? መዝሙር 103:14፤ ኢሳይያስ 41:10 ራስህን ለይሖዋ ለመወሰን ፍጹም መሆን አይጠበቅብህም። ይሖዋ ትክክል የሆነውን ነገር ማድረግ እንድትችል ይረዳሃል። ቆላስይስ 1:10 ለይሖዋ ያለህ ፍቅር ‘እሱን ባሳዝነውስ’ የሚለውን ፍርሃት እንድታሸንፍ ይረዳሃል። 3 ከጥምቀት በፊት ልትወስዳቸው የሚገቡ እርምጃዎች “አምላኬ ሆይ፣ ፈቃድህን ማድረግ ያስደስተኛል፤ ሕግህም በልቤ ውስጥ ነው።”—መዝሙር 40:8 ራስህን ለይሖዋ ለመወሰን ምን ማድረግ ይኖርብሃል? ዮሐንስ 17:3 የአምላክን ቃል አጥና ስለ ይሖዋና ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ለማወቅ ጥረት አድርግ። ስለ እነሱ ይበልጥ ባወቅክ መጠን ለእነሱ ያለህ ፍቅርም እያደገ ይሄዳል። ዕብራውያን 11:6 እምነትህን አጠናክር አምላክ ቃል የገባቸው ነገሮች እንደሚፈጸሙ እንዲሁም የኢየሱስ መሥዋዕት ከኃጢአትና ከሞት ነፃ ሊያወጣን እንደሚችል ሙሉ እምነት ይኑርህ። የሐዋርያት ሥራ 3:19 ንስሐ ግባ ከዚህ በፊት በሠራኸው መጥፎ ነገር ከልብ ማዘን ይኖርብሃል። ተመለስ ቀደም ሲል የነበረህን መጥፎ አኗኗር ትተህ ትክክል የሆነውን ነገር ማድረግ ይጠበቅብሃል። 1 ጴጥሮስ 4:2 ራስህን ወስን ራስህን ለይሖዋ ስትወስን፣ እሱን ብቻ ለማምለክ እንዲሁም በሕይወትህ ውስጥ የእሱን ፍላጎት ለማስቀደም በጸሎት ቃል ትገባለህ። ተመለስ ቀጥል አትም አጋራ አጋራ 18. ራሴን ለአምላክ መወሰንና መጠመቅ ይኖርብኛል? ክለሳ 18: ራሴን ለአምላክ መወሰንና መጠመቅ ይኖርብኛል? የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ክለሳ 18: ራሴን ለአምላክ መወሰንና መጠመቅ ይኖርብኛል? https://assetsnffrgf-a.akamaihd.net/assets/ct/1add6d1d93/images/syn_placeholder_sqr.png bhssm ገጽ 18