19. ከይሖዋ ጋር ያለህን ወዳጅነት አጠናክር አጫውት 19. ከይሖዋ ጋር ያለህን ወዳጅነት አጠናክር ይቅርታ፣ ማጫወቻው መሥራት አልቻለም። ይህን ቪዲዮ አውርድ ጽሑፉን አሳይ ጽሑፉን ደብቅ 1 ይሖዋ ይወድሃል “አምላክ ዓለምን እጅግ ከመውደዱ የተነሳ በልጁ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ ሲል አንድያ ልጁን ሰጥቷል።”—ዮሐንስ 3:16 አምላክ እንደሚወድህ ያሳየው እንዴት ነው? መዝሙር 91:2 ይሖዋ መጠጊያችን ነው። ችግር ሲያጋጥመን ይረዳናል። መዝሙር 37:29 ለወደፊቱ ጊዜ አስደሳች ተስፋ ሰጥቶናል። 1 ጢሞቴዎስ 6:12, 19 አምላክ ምንም ዓይነት ችግር በሌለበት ዓለም ውስጥ የዘላለም ሕይወት ይሰጠናል። ውብ በሆነች ገነት ውስጥ ሰላም፣ ደስታና የተሟላ ጤንነት አግኝተን እንኖራለን። 2 ይሖዋ እንድትወደው ይፈልጋል “አምላክህን ይሖዋን በሙሉ ልብህ፣ በሙሉ ነፍስህና በሙሉ አእምሮህ ውደድ።”—ማቴዎስ 22:37 ለአምላክ ያለህ ፍቅር ምን እንድታደርግ ያነሳሳሃል? ሉቃስ 17:12-17 አምላክ ላደረገልህ ነገር በሙሉ አመስጋኝ ሁን። ማቴዎስ 7:16-20 በየቀኑ የአምላክን ፈቃድ በማድረግ ለእሱ ያለህን ፍቅር አሳይ። 1 ዮሐንስ 5:3 የአምላክን ትእዛዛት ጠብቅ። 1 ጢሞቴዎስ 6:18 ለሌሎች መልካም ለማድረግ የተቻለህን ያህል ጥረት አድርግ። 3 ከይሖዋ ጋር ያለህን ወዳጅነት አጠናክር ‘ከአምላክ ፍቅር አትውጡ።’—ይሁዳ 21 ከይሖዋ ጋር ያለህን ወዳጅነት ለማጠናከር ምን ሊረዳህ ይችላል? 1 ተሰሎንቄ 5:17 ዘወትር ጸልይ። ማቴዎስ 28:19, 20፤ 2 ጢሞቴዎስ 4:2 ስለ አምላክ መንግሥት ለሌሎች ለመናገር ጥረት አድርግ። ምሳሌ 2:1-5 ስለ ይሖዋ መማርህን ቀጥል። ዕብራውያን 10:24, 25 አዘውትረህ በስብሰባዎች ላይ ተገኝ። ክርስቲያን ወንድሞችህና እህቶችህ ወደ ይሖዋ ይበልጥ እንድትቀርብ ይረዱሃል። ተመለስ ቀጥል አትም አጋራ አጋራ 19. ከይሖዋ ጋር ያለህን ወዳጅነት አጠናክር ክለሳ 19: ከይሖዋ ጋር ያለህን ወዳጅነት አጠናክር የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ክለሳ 19: ከይሖዋ ጋር ያለህን ወዳጅነት አጠናክር https://assetsnffrgf-a.akamaihd.net/assets/ct/1add6d1d93/images/syn_placeholder_sqr.png bhssm ገጽ 19