2. መጽሐፍ ቅዱስ—ከአምላክ ያገኘነው ስጦታ አጫውት 2. መጽሐፍ ቅዱስ—ከአምላክ ያገኘነው ስጦታ ይቅርታ፣ ማጫወቻው መሥራት አልቻለም። ይህን ቪዲዮ አውርድ ጽሑፉን አሳይ ጽሑፉን ደብቅ 1 መጽሐፍ ቅዱስ የአምላክ ቃል ነው “ቅዱሳን መጻሕፍት ሁሉ በአምላክ መንፈስ መሪነት የተጻፉ ናቸው።”—2 ጢሞቴዎስ 3:16 መጽሐፍ ቅዱስ ከሌሎች መጻሕፍት የተለየ ነው የምንለው ለምንድን ነው? መጽሐፍ ቅዱስ ከሁለት ሺህ ስምንት መቶ በላይ በሚሆኑ ቋንቋዎች የተተረጎመ ሲሆን በቢሊዮን በሚቆጠሩ ቅጂዎች ታትሟል። ከየትም ልናገኘው የማንችለውን እውቀት ይሰጠናል። 1 ተሰሎንቄ 2:13 የመጽሐፍ ቅዱስ ባለቤት አምላክ ነው። 2 ጴጥሮስ 1:21 አምላክ ሐሳቡን ለማስተላለፍ በሰዎች ተጠቅሟል። 2 መጽሐፍ ቅዱስ ትንቢቶችን የያዘ መጽሐፍ ነው ‘አምላክ ሊዋሽ አይችልም።’—ቲቶ 1:2 በመጽሐፍ ቅዱስ መተማመን የምትችለው ለምንድን ነው? ኢሳይያስ 44:27–45:2 መጽሐፍ ቅዱስ ባቢሎን ድል እንደምትደረግ ከሁለት መቶ ዓመታት በፊት ትንቢት ተናግሮ ነበር። 2 ጢሞቴዎስ 3:1-5 በዛሬው ጊዜ፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢቶች እየተፈጸሙ ነው። ዘኁልቁ 23:19 መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ወደፊቱ ጊዜ የሚናገራቸው ትንቢቶች መፈጸማቸው እንደማይቀር እርግጠኛ መሆን እንችላለን። 3 መጽሐፍ ቅዱስ የተጻፈው አንተን ለመርዳት ነው “የሚጠቅምህን ነገር የማስተምርህ . . . እኔ ይሖዋ አምላክህ ነኝ።”—ኢሳይያስ 48:17 ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ምን ትምህርት አገኘህ? ኢዮብ 26:7፤ ኢሳይያስ 40:22 መጽሐፍ ቅዱስ ከሳይንስ አንጻር የሚናገረው ነገር ትክክል ነው። ዘኁልቁ 20:2-12 የመጽሐፍ ቅዱስ ጸሐፊዎች ሁሉንም ነገር በሐቀኝነት ጽፈዋል። ማቴዎስ 5-7 ኢየሱስ ደስተኞች መሆንና ከሌሎች ጋር ተስማምተን መኖር የምንችለው እንዴት እንደሆነ፣ መጸለይ ያለብን እንዴት እንደሆነ እንዲሁም ለገንዘብ ምን አመለካከት ሊኖረን እንደሚገባ የሚገልጽ ምክር ሰጥቷል። 4 መጽሐፍ ቅዱስ ሕይወትህን ሊለውጠው ይችላል “የአምላክ ቃል ሕያውና ኃይለኛ ነው።”—ዕብራውያን 4:12 የአምላክ ቃል ምን ጥቅሞች ያስገኝልሃል? የአምላክን ዓላማ ለመረዳት ያስችልሃል። ማንነትህን በትክክል እንድታውቅ ይረዳሃል። አምላክ ከአንተ የሚፈልገው ነገር ምን እንደሆነ እንድታውቅ ይረዳሃል። አምላክ መጽሐፍ ቅዱስን እንደ ውድ ስጦታ በመመልከት እንድታነበውና እንድታጠናው ይፈልጋል። ተመለስ ቀጥል አትም አጋራ አጋራ 2. መጽሐፍ ቅዱስ—ከአምላክ ያገኘነው ስጦታ ክለሳ 2: መጽሐፍ ቅዱስ—ከአምላክ ያገኘነው ስጦታ የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ክለሳ 2: መጽሐፍ ቅዱስ—ከአምላክ ያገኘነው ስጦታ https://assetsnffrgf-a.akamaihd.net/assets/ct/1add6d1d93/images/syn_placeholder_sqr.png bhssm ገጽ 2