3. አምላክ ለሰዎች ያለው ዓላማ ምንድን ነው? አጫውት 3. አምላክ ለሰዎች ያለው ዓላማ ምንድን ነው? ይቅርታ፣ ማጫወቻው መሥራት አልቻለም። ይህን ቪዲዮ አውርድ ጽሑፉን አሳይ ጽሑፉን ደብቅ 1 አምላክ እኛን የፈጠረው በዓላማ ነው “ጻድቃን ምድርን ይወርሳሉ፤ በእሷም ላይ ለዘላለም ይኖራሉ።”—መዝሙር 37:29 አምላክ ለሰዎች ያለው ዓላማ ምንድን ነው? ዘፍጥረት 1:28 የአምላክ ዓላማ የሰው ልጆች ምድርን ገነት እንዲያደርጉና እንስሳትን እንዲንከባከቡ ነበር። ኢሳይያስ 46:9-11፤ 55:11 አምላክ ዓላማውን ይፈጽማል፤ ደግሞም እንዲህ እንዳያደርግ ሊከለክለው የሚችል ምንም ነገር የለም። 2 ሕይወት በመከራ የተሞላው ለምንድን ነው? “መላው ዓለም . . . በክፉው ቁጥጥር ሥር ነው።”—1 ዮሐንስ 5:19 ዓለምን የሚገዛው ማን ነው? ዮሐንስ 12:31 ኢየሱስ የዚህ ዓለም ገዢ ሰይጣን እንደሆነ ተናግሯል። ያዕቆብ 1:13-15 ሰይጣን የራሱ ያልሆነውን ነገር ተመኝቷል። ዘፍጥረት 2:17፤ 3:1-6 ሰይጣን ሔዋንን አታለላት፤ አዳምና ሔዋን አምላክን ባለመታዘዛቸው ከጊዜ በኋላ ሞቱ። ሮም 3:23፤ 5:12 ከአዳም ኃጢአት ስለወረስን እኛም እንሞታለን። 2 ቆሮንቶስ 4:3, 4 ሰይጣን ሰዎችን ያሳስታል። 3 የአምላክ መንግሥት መፍትሔ ይሰጣል “መንግሥትህ ይምጣ። ፈቃድህ . . . በምድርም ላይ ይፈጸም።”—ማቴዎስ 6:10 ይሖዋ ወደፊት ምን ያደርጋል? ዳንኤል 2:44 አምላክ ያቋቋመው መስተዳድር የዓለምን መንግሥታት ሁሉ አጥፍቶ ብቻውን ይገዛል። ራእይ 16:14-16 አምላክ በክፋት የተሞላውን ይህን ዓለም በአርማጌዶን ጦርነት ያጠፋዋል። ኢሳይያስ 9:6, 7 ይሖዋ ኢየሱስን በሰማይ ያለው መስተዳድር ንጉሥ አድርጎ ሾሞታል። ኢየሱስ ምድርን ይገዛል። 4 የአምላክ መንግሥት ምድርን ገነት ያደርጋታል “አንተ እጅህን ትዘረጋለህ፤ የሕያዋን ፍጥረታትንም ሁሉ ፍላጎት ታሟላለህ።”—መዝሙር 145:16 የአምላክ መንግሥት ምን ነገሮችን ያደርግልናል? መዝሙር 46:9 ጦርነት፣ ወንጀልና ዓመፅ ይወገዳል። ኢሳይያስ 32:18፤ 65:21-24 በአዲሱ ዓለም ውስጥ ሰዎች ሁሉ የሚያማምሩ ቤቶችና የአትክልት ቦታዎች ይኖሯቸዋል፤ በዚያም ተስማምተው በሰላም ይኖራሉ። መዝሙር 72:16 የተትረፈረፈ ምግብ ይኖራል። ኢሳይያስ 11:6-9 ሰዎችና እንስሳት በሰላም ይኖራሉ። ኢሳይያስ 33:24፤ የሐዋርያት ሥራ 24:15 የሚታመም ሰው አይኖርም፤ የሞቱ ሰዎች ይነሳሉ። ተመለስ ቀጥል አትም አጋራ አጋራ 3. አምላክ ለሰዎች ያለው ዓላማ ምንድን ነው? ክለሳ 3: አምላክ ለሰዎች ያለው ዓላማ ምንድን ነው? የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ክለሳ 3: አምላክ ለሰዎች ያለው ዓላማ ምንድን ነው? https://assetsnffrgf-a.akamaihd.net/assets/ct/1add6d1d93/images/syn_placeholder_sqr.png bhssm ገጽ 3