5. ቤዛው—ከሁሉ የላቀ የአምላክ ስጦታ

5. ቤዛው—ከሁሉ የላቀ የአምላክ ስጦታ

1 ሁላችንም ቤዛ ያስፈልገናል

‘የሰው ልጅ የመጣው በብዙ ሰዎች ምትክ ሕይወቱን ቤዛ አድርጎ ለመስጠት ነው።’—ማቴዎስ 20:28

ቤዛ የሚያስፈልገን ለምንድን ነው?

  • ዘፍጥረት 3:17-19

    አዳም አምላክን ባለመታዘዙ ከይሖዋ ጋር የነበረውን ልዩ ዝምድና፣ ፍጹም የሆነ ሕይወቱንና በገነት ውስጥ የመኖር መብቱን አጥቷል።

  • ሮም 5:12

    አዳም በሠራው ጥፋት የተነሳ ኃጢአትና ሞት ወርሰናል።

  • ኤፌሶን 1:7

    ቤዛው፣ ይሖዋ ሰዎችን ከኃጢአትና ከሞት ባርነት ነፃ ለማውጣት ያደረገው ዝግጅት ነው።

2 ይሖዋ ቤዛ አዘጋጅቶልናል

“እኛ በእሱ አማካኝነት ሕይወት ማግኘት እንድንችል አምላክ አንድያ ልጁን ወደ ዓለም ልኮታል።”—1 ዮሐንስ 4:9

ይሖዋ ቤዛውን ያዘጋጀው እንዴት ነው?

  • መዝሙር 49:7, 8

    ማናችንም ብንሆን አዳም ላጣው ፍጹም ሕይወት ቤዛ መክፈል አንችልም።

  • ሉቃስ 1:35

    ይሖዋ በጣም የሚወደውን ልጁን ወደ ምድር በመላክ ፍጹም ሰው ሆኖ እንዲወለድ አድርጓል።

  • ሮም 3:23, 24፤ ዕብራውያን 9:24

    ኢየሱስ ከሞት ከተነሳ በኋላ ወደ ሰማይ ተመልሶ በመሄድ የፍጹም ሕይወቱን ዋጋ በይሖዋ ፊት ቤዛ አድርጎ አቅርቧል።

3 ቤዛው አስተማማኝ ተስፋ እንዲኖረን አስችሏል

“እንባን ሁሉ ከዓይናቸው ያብሳል፤ ከእንግዲህ ወዲህ ሞት አይኖርም።”—ራእይ 21:4

ከቤዛው ምን ጥቅም እናገኛለን?

4 ለቤዛው አድናቆት እንዳለን ማሳየት ይኖርብናል

‘አምላክ በልጁ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው ሲል አንድያ ልጁን ሰጥቷል።’—ዮሐንስ 3:16

አምላክ ለሰጠን ስጦታ ማለትም ለቤዛው አድናቆት እንዳለን ማሳየት የምንችለው እንዴት ነው?

  • ዮሐንስ 17:3

    ስለ ይሖዋና ስለ ኢየሱስ ለማወቅ እንዲሁም እነሱን ለመምሰል ጥረት አድርግ።

  • ሉቃስ 22:19

    በየዓመቱ በሚከበረው የክርስቶስ ሞት መታሰቢያ በዓል ላይ ተገኝ።

  • ዮሐንስ 3:36፤ ያዕቆብ 2:26

    ‘በኢየሱስ አምናለሁ’ ማለት ብቻ በቂ አይደለም። ኢየሱስ ያስተማረውን ትምህርት ተግባራዊ አድርግ።