6. ስንሞት ምን እንሆናለን? አጫውት 6. ስንሞት ምን እንሆናለን? ይቅርታ፣ ማጫወቻው መሥራት አልቻለም። ይህን ቪዲዮ አውርድ ጽሑፉን አሳይ ጽሑፉን ደብቅ 1 አንድ ሰው ሲሞት ሕይወቱ ያበቃል “ሙታን . . . ምንም አያውቁም።”—መክብብ 9:5 ስንሞት ምን እንሆናለን? መዝሙር 146:3, 4፤ መክብብ 9:6, 10 ስንሞት ምንም ነገር ማየት፣ መስማትም ሆነ ማሰብ አንችልም። ዮሐንስ 11:11-14 ኢየሱስ ሞትን ከእንቅልፍ ጋር አመሳስሎታል። 2 ይሖዋ የሰው ልጆች እንዲሞቱ አይፈልግም “ከመልካምና ክፉ እውቀት ዛፍ . . . አትብላ፤ ምክንያቱም ከዚህ ዛፍ በበላህ ቀን በእርግጥ ትሞታለህ።”—ዘፍጥረት 2:17 የምንሞተው ለምንድን ነው? ዘፍጥረት 3:1-6 ሰይጣን፣ ሔዋን የይሖዋን ትእዛዝ ብትጥስ እንደማትሞት በመንገር አታለላት። ሆኖም አዳምና ሔዋን፣ የይሖዋን ትእዛዝ በመጣስ ኃጢአት ስለሠሩ ለተወሰኑ ዓመታት ከኖሩ በኋላ ሞቱ። ዘፍጥረት 3:19 አዳም ሲሞት ሕይወት የሌለው ወይም በድን ሆኗል። ሮም 5:12 ኃጢአት ከመጀመሪያዎቹ ወላጆቻችን የወረስነው ከባድ በሽታ ነው ሊባል ይችላል። ሁላችንም ኃጢአተኞች ሆነን ስለምንወለድ እንሞታለን። 1 ቆሮንቶስ 15:26 መጽሐፍ ቅዱስ ሞትን ጠላት በማለት ይጠራዋል። 3 ስለ ሞት እውነቱን ማወቃችን ነፃ ያወጣናል “እውነትንም ታውቃላችሁ፤ እውነትም ነፃ ያወጣችኋል።”—ዮሐንስ 8:32 ስለ ሞት እውነቱን ማወቃችን ከሐሰት ትምህርቶች ነፃ የሚያወጣን እንዴት ነው? 1 ዮሐንስ 4:8 ‘ይሖዋ ሰዎችን በገሃነም ያቃጥላል’ ብሎ ማስተማር እሱን እንደመሳደብ ይቆጠራል። ይሖዋ፣ ሰዎችን እንዲህ ባለ መንገድ ፈጽሞ አያሠቃይም! ራእይ 4:11 ብዙዎች የሞቱ ሰዎችን ስለሚፈሩ ይሖዋን ማምለክ ሲገባቸው የሙታን መናፍስትን ያመልካሉ። እውነተኛው አምላክ ይሖዋ ስለሆነ ሊመለክ የሚገባው እሱ ብቻ ነው። ተመለስ ቀጥል አትም አጋራ አጋራ 6. ስንሞት ምን እንሆናለን? ክለሳ 6: ስንሞት ምን እንሆናለን? የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ክለሳ 6: ስንሞት ምን እንሆናለን? https://assetsnffrgf-a.akamaihd.net/assets/ct/1add6d1d93/images/syn_placeholder_sqr.png bhssm ገጽ 6