7. የሞቱ ሰዎች ይነሳሉ!

7. የሞቱ ሰዎች ይነሳሉ!

1 ይሖዋ ሞትን ያስወግዳል

“የመጨረሻው ጠላት፣ ሞት ይደመሰሳል።”—1 ቆሮንቶስ 15:26

መጽሐፍ ቅዱስ የምንወደው ሰው ሲሞትብን የሚያጽናናን እንዴት ነው?

  • 2 ቆሮንቶስ 1:3, 4

    የቤተሰባችን አባል ወይም የቅርብ ጓደኛችን ሲሞት ስሜታችን በጣም ይጎዳል። መጽሐፍ ቅዱስ ግን ያጽናናናል።

  • ኢሳይያስ 25:8፤ 26:19

    ይሖዋ ሞትን ለዘላለም ማስወገድ ይችላል። የሞቱ ሰዎችንም እንኳ ዳግመኛ በሕይወት እንዲኖሩ ያደርጋል።

2 በትንሣኤ ተስፋ መተማመን እንችላለን

“አንቺ ልጅ፣ ተነሽ!”—ማርቆስ 5:41

በትንሣኤ ተስፋ መተማመን የምንችለው ለምንድን ነው?

  • ዮሐንስ 11:1-44

    ኢየሱስ አልዓዛርን ከሞት አስነስቷል።

  • ማርቆስ 5:22-24, 35-42

    ኢየሱስ አንዲትን ልጅ ከሞት አስነስቷል።

  • ዮሐንስ 11:41, 42

    ኢየሱስ የሞቱትን ያስነሳው ከይሖዋ ያገኘውን ኃይል ተጠቅሞ ነው።

  • ዮሐንስ 12:9-11

    ኢየሱስ የሞቱትን ሲያስነሳ ብዙ ሰዎች ተመልክተዋል። የኢየሱስ ጠላቶችም እንኳ ኢየሱስ የሞቱትን ማስነሳት እንደሚችል ያውቁ ነበር።

3 ይሖዋ በቢሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን ከሞት ያስነሳል

“አንተ ትጣራለህ፤ እኔም እመልስልሃለሁ። የእጅህን ሥራ ትናፍቃለህ።”—ኢዮብ 14:13-15

ከሞት የሚነሱት እነማን ናቸው?

  • ዮሐንስ 5:28, 29

    ይሖዋ በትንሣኤ የሚያስባቸው ሁሉ እንደገና በሕይወት ይኖራሉ።

  • የሐዋርያት ሥራ 24:15

    ጻድቃንም ሆኑ ዓመፀኞች ከሞት ይነሳሉ።

  • ኢሳይያስ 40:26

    ይሖዋ የእያንዳንዱን ኮከብ ስም ማስታወስ ከቻለ፣ ከሞት የሚያስነሳቸውን ሰዎች የሚመለከቱ ዝርዝር ጉዳዮችን ማስታወስ እንደማይከብደው ጥርጥር የለውም።

4 አንዳንድ ሰዎች ከሞት ተነስተው ወደ ሰማይ ይሄዳሉ

“ለእናንተ ቦታ ለማዘጋጀት እሄዳለሁ።”—ዮሐንስ 14:2

ከሞት ተነስተው ወደ ሰማይ የሚሄዱት እነማን ናቸው?

  • 1 ጴጥሮስ 3:18

    ለመጀመሪያ ጊዜ ከሞት ተነስቶ ወደ ሰማይ የሄደው ኢየሱስ ነው።

  • ሉቃስ 12:32

    ኢየሱስ ከደቀ መዛሙርቱ መካከል ከሞት ተነስተው ወደ ሰማይ የሚሄዱት ጥቂት እንደሆኑ ተናግሯል።

  • ራእይ 14:1

    ይሖዋ በሰማይ እንዲኖሩ የመረጣቸው ሰዎች አጠቃላይ ቁጥር 144,000 ነው።