ሆሴዕ 10:1-15

  • የተበላሸ ወይን የሆነው እስራኤል ጥፋት ይደርስበታል (1-15)

    • መዝራትና ማጨድ (12, 13)

10  “እስራኤል ፍሬ የሚሰጥ እየተበላሸ* ያለ ወይን ነው።+ ፍሬው በበዛ መጠን መሠዊያዎቹንም በዚያው ልክ አበዛ፤+ምድሩ የተሻለ ምርት ባስገኘ መጠን ይበልጥ ያማሩ የማምለኪያ ዓምዶችን ሠራ።+   ልባቸው ግብዝ* ነው፤በመሆኑም በደለኞች ናቸው። መሠዊያዎቻቸውን የሚሰባብር፣ ዓምዶቻቸውንም የሚያፈራርስ አለ።   እነሱም ‘ንጉሥ የለንም፤+ ይሖዋን አልፈራንምና። ንጉሥ ቢኖረንስ ምን ሊያደርግልን ይችላል?’ ይላሉ።   ከንቱ ቃል ይናገራሉ፤ በሐሰት ይምላሉ፤+ ቃል ኪዳንም ይገባሉ፤ስለዚህ የሚፈረደው ፍርድ በእርሻ ትልም ውስጥ እንዳለ መርዛማ አረም ነው።+   የሰማርያ ነዋሪዎች በቤትአዌን ስላለው የጥጃ ጣዖት ስጋት ያድርባቸዋል።+ ሕዝቡም ሆኑ በእሱና በክብሩ ሐሴት ያደረጉት የባዕድ አምላክ ካህናትለእሱ ያዝናሉ፤ከእነሱ ተለይቶ በግዞት ይወሰዳልና።   ለአንድ ታላቅ ንጉሥ እንደሚቀርብ ስጦታ ወደ አሦር ይወሰዳል።+ ኤፍሬም ውርደት ይከናነባል፤እስራኤልም በተከተለው ምክር የተነሳ ያፍራል።+   ሰማርያና ንጉሧ ተቆርጦ ውኃ ላይ እንደወደቀ ቅርንጫፍተጠራርገው ይጠፋሉ።+   የእስራኤል ኃጢአት+ የሆኑት በቤትአዌን+ የሚገኙ ከፍ ያሉ የማምለኪያ ቦታዎች ይወድማሉ።+ መሠዊያዎቻቸውን እሾህና አሜኬላ ይወርሷቸዋል።+ ሰዎች ተራሮቹን ‘ሸሽጉን!’ ኮረብቶቹንም ‘በላያችን ውደቁ!’ ይሏቸዋል።+   የእስራኤል ሰዎች ሆይ፣ ከጊብዓ ዘመን ጀምሮ ኃጢአት ሠርታችኋል።+ እነሱ በዚያ ጸንተዋል። በጊብዓ የተካሄደው ጦርነት የዓመፅን ልጆች አልፈጃቸውም።* 10  በፈለግኩ ጊዜ እገሥጻቸዋለሁ። ሁለቱ በደሎቻቸው በላያቸው በሚጫኑበት ጊዜ*ሕዝቦች በእነሱ ላይ ይሰበሰባሉ። 11  ኤፍሬም ማበራየት የምትወድ የተገራች ጊደር ነው፤በመሆኑም ያማረ አንገቷን አተረፍኩ። ሰውም ኤፍሬምን እንዲጋልብ አደርጋለሁ።*+ ይሁዳ ያርሳል፤ ያዕቆብም መሬቱን ለእሱ ያለሰልሳል። 12  ለራሳችሁ የጽድቅን ዘር ዝሩ፤ ታማኝ ፍቅርንም እጨዱ። ይሖዋን መፈለግ የምትችሉበት ጊዜ ከማለፉ በፊት፣+እሱም መጥቶ በጽድቅ መመሪያ እስኪሰጣችሁ ድረስ+ያልለማውን መሬት ለራሳችሁ እረሱ።+ 13  እናንተ ግን ክፋትን አረሳችሁ፤ዓመፅን አጨዳችሁ፤+የማታለልንም ፍሬ በላችሁ፤በገዛ ራሳችሁ መንገድ፣በተዋጊዎቻችሁም ብዛት ታምናችኋልና። 14  በሕዝባችሁ ላይ ሁከት ይነሳል፤እናቶች ከልጆቻቸው ጋር በተጨፈጨፉበት* የውጊያ ቀንሻልማን፣ ቤትአርቤልን እንዳወደመ ሁሉ፣የተመሸጉ ከተሞቻችሁ በሙሉ ይወድማሉ።+ 15  ቤቴል ሆይ፣ ክፋትሽ ታላቅ ስለሆነ እንዲሁ ይደረግብሻል።+ ጎህ ሲቀድ የእስራኤል ንጉሥ ፈጽሞ ይጠፋል።”*+

የግርጌ ማስታወሻ

“እየተንሰራፋ” ማለትም ሊሆን ይችላል።
ወይም “የማይታመን፤ መሠሪ።”
ወይም “ሙሉ በሙሉ አላጠፋቸውም።”
ቅጣታቸውን እንደ ቀንበር ሲሸከሙ ማለት ነው።
ወይም “በኤፍሬም ላይ ልጓም አስገባለሁ።”
ቃል በቃል “በተፈጠፈጡበት።”
ቃል በቃል “ጸጥ ይደረጋል።”