ሆሴዕ 14:1-9

  • ወደ ይሖዋ ለመመለስ የቀረበ ልመና (1-3)

    • የከንፈር ውዳሴ ማቅረብ (2)

  • “ከዳተኛነታቸውን እፈውሳለሁ” (4-9)

14   “እስራኤል ሆይ፣ በበደልህ ስለተሰናከልክወደ አምላክህ ወደ ይሖዋ ተመለስ።+   ይህን ቃል ይዛችሁ ወደ ይሖዋ ተመለሱ፤እንዲህ በሉት፦ ‘በደላችንን ይቅር በለን፤+ መልካም የሆነውንም ነገር ተቀበለን፤እኛም ወይፈኖች እንደምናቀርብ፣ የከንፈራችንን ውዳሴ እናቀርብልሃለን።*+   አሦር አያድነንም።+ ፈረሶችን አንጋልብም፤+ከእንግዲህም ወዲህ የገዛ እጆቻችን የሠሩትን “አምላካችን ሆይ!” አንልም፤አባት የሌለው ልጅ ምሕረት ያገኘው በአንተ ነውና።’+   እኔም ከዳተኛነታቸውን እፈውሳለሁ።+ በገዛ ፈቃዴ እወዳቸዋለሁ፤+ምክንያቱም ቁጣዬ ከእሱ ተመልሷል።+   እኔ ለእስራኤል እንደ ጠል እሆናለሁ፤እሱም እንደ አበባ ያብባል፤እንደ ሊባኖስ ዛፎችም ሥሮቹን ይሰዳል።   ቀንበጦቹ ይንሰራፋሉ፤ውበቱ እንደ ወይራ ዛፍ፣መዓዛውም እንደ ሊባኖስ ዛፍ ይሆናል።   እነሱም ዳግመኛ በጥላው ሥር ይኖራሉ። እህል ያበቅላሉ፤ እንደ ወይን ተክልም ያብባሉ።+ ዝናው* እንደ ሊባኖስ የወይን ጠጅ ይሆናል።   ኤፍሬም ‘ከእንግዲህ ከጣዖቶች ጋር ምን ጉዳይ አለኝ?’ ይላል።+ መልስ እሰጠዋለሁ፤ ደግሞም እጠብቀዋለሁ።+ እኔ እንደለመለመ የጥድ ዛፍ እሆናለሁ። ከእኔም ፍሬ ታገኛላችሁ።”   ጥበበኛ ማን ነው? እነዚህን ነገሮች ያስተውል። ልባም የሆነ ማን ነው? እነዚህን ነገሮች ይወቅ። የይሖዋ መንገዶች ቀና ናቸውና፤+ጻድቃንም በመንገዶቹ ላይ ይሄዳሉ፤በደለኞች ግን በእነሱ ይሰናከላሉ።

የግርጌ ማስታወሻ

ቃል በቃል “እኛም በምላሹ የከንፈሮቻችንን ወይፈኖች እናቀርባለን።”
ቃል በቃል “መታሰቢያው።”