ሆሴዕ 2:1-23
2 “ወንድሞቻችሁን ‘ሕዝቤ!’*+
እህቶቻችሁን ደግሞ ‘ምሕረት የተደረገልሽ ሴት!’* በሏቸው።+
2 እናታችሁን ክሰሷት፤ እሷ ሚስቴ ስላልሆነች፣+እኔም ባሏ ስላልሆንኩ ክሰሷት።
ከእሷ ዘንድ ዘማዊነቷን፣*ከጡቶቿም መካከል ምንዝሯን ታስወግድ፤
3 አለዚያ ራቁቷን አስቀራታለሁ፤ በተወለደችበት ቀን እንደነበረችውም አደርጋታለሁ፤እንደ ምድረ በዳ፣ውኃ እንደሌለበትም ምድር አደርጋታለሁ፤በውኃ ጥምም እገድላታለሁ።
4 ወንዶች ልጆቿ የምንዝር* ልጆች ስለሆኑምሕረት አላደርግላቸውም።
5 እናታቸው አመንዝራለችና።*+
እነሱን የፀነሰችው ሴት አሳፋሪ ድርጊት ፈጽማለች፤+‘አጥብቀው የሚወዱኝን፣ደግሞም ምግቤንና ውኃዬን፣የሱፍ ልብሴንና በፍታዬን እንዲሁም ዘይቴንና መጠጤን የሚሰጡኝን ተከትዬ እሄዳለሁ’ ብላለችና።+
6 ስለዚህ መንገዷን በእሾህ አጥር እዘጋለሁ፤መውጫ መንገድ እንዳታገኝምዙሪያዋን በድንጋይ አጥራለሁ።
7 አጥብቀው የሚወዷትን ተከትላ ትሄዳለች፤ ሆኖም አትደርስባቸውም፤+ትፈልጋቸዋለች፤ ሆኖም አታገኛቸውም።
ከዚያም ‘ተመልሼ ወደ መጀመሪያው ባሌ እሄዳለሁ፤+ከአሁኑ ኑሮዬ ይልቅ የበፊቱ ይሻለኛልና’ ትላለች።+
8 እህሉን፣ አዲሱን የወይን ጠጅና ዘይቱን የሰጠኋትእንዲሁም ለባአል አምልኮ የተጠቀሙበትን ብርና ወርቅ+በብዛት እንድታገኝ ያደረግኩት እኔ እንደሆንኩ አልተገነዘበችም።+
9 ‘ስለዚህ ሐሳቤን ቀይሬ፣ እህሌን በጊዜው፣አዲሱን የወይን ጠጄንም በወቅቱ እወስዳለሁ፤+እርቃኗን የምትሸፍንበትንም የሱፍ ልብሴንና በፍታዬን እነጥቃታለሁ።
10 አሁንም ኀፍረተ ሥጋዋን አጥብቀው በሚወዷት ፊት እገልጣለሁ፤ከእጄም የሚያስጥላት ሰው አይኖርም።+
11 ደስታዋን፣ በዓሏን፣ የወር መባቻዋንና ሰንበቷን ሁሉእንዲሁም የተወሰኑትን የበዓል ወቅቶቿን ሁሉ አስቀራለሁ።+
12 “አጥብቀው የሚወዱኝ ውሽሞቼ ለእኔ የሰጡኝ ደሞዜ ናቸው” የምትላቸውን
የወይን ተክሏንና የበለስ ዛፏን አወድማለሁ፤ጫካም አደርጋቸዋለሁ፤የዱር አራዊትም ይበሏቸዋል።
13 ለባአል ምስሎች መሥዋዕት ባቀረበችባቸው፣+ በጉትቻዋና በጌጦቿ በተንቆጠቆጠችባቸውእንዲሁም አጥብቀው የሚወዷትን በተከተለችባቸው ቀናት የተነሳ ተጠያቂ አደርጋታለሁ፤እኔንም ረስታኝ ነበር’+ ይላል ይሖዋ።
14 ‘ስለዚህ አግባብቼ አሳምናታለሁ፤ወደ ምድረ በዳ እመራታለሁ፤ልቧን በሚማርክ መንገድ አናግራታለሁ።
15 ከዚያን ጊዜ አንስቶ የወይን እርሻዎቿን መልሼ እሰጣታለሁ፤+የአኮርም ሸለቆ*+ የተስፋ በር እንዲሆናት አደርጋለሁ፤በዚያም እንደ ልጅነቷ ጊዜናከግብፅ ምድር እንደወጣችበት ቀን መልስ ትሰጠኛለች።+
16 በዚያም ቀን’ ይላል ይሖዋ፣‘ባሌ ብለሽ ትጠሪኛለሽ፤ ከእንግዲህ ጌታዬ* ብለሽ አትጠሪኝም።’
17 ‘የባአልን ምስሎች ስሞች ከአንደበቷ አስወግዳለሁ፤+ስማቸውም ከእንግዲህ አይታወስም።+
18 በዚያም ቀን ለእነሱ ጥቅም ስል ከዱር አራዊት፣+ከሰማይ ወፎችና መሬት ለመሬት ከሚሳቡ ፍጥረታት ጋር ቃል ኪዳን አደርጋለሁ፤+ቀስትን፣ ሰይፍንና ጦርነትን ከምድሪቱ አስወግዳለሁ፤+ያለስጋት እንዲያርፉም* አደርጋለሁ።+
19 ለዘላለም አጭሻለሁ፤በጽድቅ፣ በፍትሕ፣ በታማኝ ፍቅርናበምሕረት አጭሻለሁ።+
20 በታማኝነት አጭሻለሁ፤አንቺም በእርግጥ ይሖዋን ታውቂያለሽ።’+
21 ‘በዚያም ቀን መልስ እሰጣለሁ’ ይላል ይሖዋ፤‘ለሰማያት መልስ እሰጣለሁ፤እነሱ ደግሞ ለምድር መልስ ይሰጣሉ፤+
22 ምድር ደግሞ ለእህሉ፣ ለአዲሱ የወይን ጠጅና ለዘይቱ መልስ ትሰጣለች፤እነሱም ለኢይዝራኤል* መልስ ይሰጣሉ።+
23 በምድር ላይ ለራሴ እንደ ዘር እዘራታለሁ፤+ደግሞም ምሕረት ላልተደረገላት* ለእሷ ምሕረት አደርግላታለሁ፤ሕዝቤ ያልሆኑትን* “እናንተ ሕዝቤ ናችሁ” እላቸዋለሁ፤+
እነሱ ደግሞ “አንተ አምላኬ ነህ” ይላሉ።’”+