ሆሴዕ 5:1-15

  • በኤፍሬምና በይሁዳ ላይ የተላለፈ ፍርድ (1-15)

5  “እናንተ ካህናት፣ ይህን ስሙ፤+እናንተ የእስራኤል ቤት ሰዎች፣ በትኩረት አዳምጡ፤እናንተም የንጉሡ ቤት ሰዎች፣ አዳምጡ፤ፍርዱ እናንተንም ይጨምራልና፤ምክንያቱም ለምጽጳ ወጥመድ፣በታቦርም+ ላይ የተዘረጋ መረብ ሆናችኋል።   ከትክክለኛው መንገድ የራቁት ሰዎች* ደም በማፍሰስ ወንጀል ተዘፍቀዋል፤*እኔም ለሁሉም ማስጠንቀቂያ እሰጣለሁ።*   ኤፍሬምን አውቀዋለሁ፤እስራኤልም ከእኔ የተሰወረ አይደለም። ኤፍሬም ሆይ፣ አሁን አንተ ሴሰኛ ሆነሃል፤*እስራኤል ራሱን አርክሷል።+   የሠሩት ሥራ ወደ አምላካቸው እንዲመለሱ አይፈቅድላቸውም፤ምክንያቱም በመካከላቸው የአመንዝራነት* መንፈስ አለ፤+ለይሖዋም እውቅና አይሰጡም።   የእስራኤል ኩራት በራሱ ላይ* መሥክሮበታል፤+እስራኤልና ኤፍሬም የሠሩት በደል አሰናክሏቸዋል፤ይሁዳም ከእነሱ ጋር ተሰናክሏል።+   መንጎቻቸውንና ከብቶቻቸውን ይዘው ይሖዋን ፍለጋ ሄዱ፤ሆኖም ሊያገኙት አልቻሉም። እሱ ከእነሱ ርቋል።+   እነሱ ይሖዋን ከድተዋል፤+ባዕድ ወንዶች ልጆች ወልደዋልና። አሁንም አንድ ወር፣ እነሱንና ድርሻቸውን* ይውጣል።*   በጊብዓ ቀንደ መለከት፣ በራማም+ መለከት ንፉ!+ ‘ቢንያም ሆይ፣ ከኋላህ ነን!’ ብላችሁ በቤትአዌን+ ቀረርቶ አሰሙ።   ኤፍሬም ሆይ፣ በምትቀጣበት ቀን መቀጣጫ ትሆናለህ።+ በእስራኤል ነገዶች መካከል በእርግጥ ምን እንደሚከሰት አሳውቄአለሁ። 10  የይሁዳ መኳንንት ወሰን እንደሚገፉ ሰዎች ናቸው።+ በእነሱ ላይ ቁጣዬን እንደ ውኃ አፈሳለሁ። 11  ኤፍሬም ተጨቁኗል፤ በፍርድ ተረግጧል፤ባላጋራውን ለመከተል ቆርጧልና።+ 12  በመሆኑም እኔ ለኤፍሬም እንደ ብል፣ለይሁዳ ቤት ደግሞ እንደ ነቀዝ ሆኛለሁ። 13  ኤፍሬም ሕመሙን፣ ይሁዳም ቁስሉን ሲመለከትኤፍሬም ወደ አሦር ሄደ፤+ ወደ ታላቅ ንጉሥም መልእክተኞች ላከ። ይሁንና ንጉሡ እናንተን ሊፈውሳችሁ አልቻለም፤ቁስላችሁንም ሊያድን አልቻለም። 14  እኔ ለኤፍሬም እንደ አንበሳ፣ለይሁዳም ቤት እንደ ደቦል አንበሳ እሆናለሁና። እኔ ራሴ ቦጫጭቄአቸው እሄዳለሁ፤+ነጥቄ እወስዳቸዋለሁ፤ የሚታደጋቸውም አይኖርም።+ 15  እሄዳለሁ፤ በደላቸው የሚያስከትልባቸውን መዘዝ እስኪሸከሙም ድረስ ወደ ስፍራዬ እመለሳለሁ፤በዚህ ጊዜም ሞገሴን* ይሻሉ።+ በጭንቀት በሚዋጡበት ጊዜ እኔን ይሻሉ።”+

የግርጌ ማስታወሻ

ወይም “ዓመፀኞቹ።”
ወይም “እጅግ ተጠላልፈዋል።”
ወይም “ሁሉንም እገሥጻለሁ።”
ወይም “እጅግ ነውረኛ ሆነሃል፤ አመንዝረሃል።”
ወይም “የነውረኝነት፤ የሴሰኝነት።”
ቃል በቃል “በፊቱ።”
“በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ እነሱም ሆኑ ድርሻቸው ይዋጣሉ” ማለትም ሊሆን ይችላል።
ወይም “መሬታቸውን።”
ቃል በቃል “ፊቴን።”