ሆሴዕ 6:1-11
6 “ኑ ወደ ይሖዋ እንመለስ፤እሱ ቦጫጭቆናል፤+ ሆኖም ይፈውሰናል።
እሱ መቶናል፤ ሆኖም ቁስላችንን ይጠግናል።
2 ከሁለት ቀናት በኋላ ያነቃናል።
በሦስተኛውም ቀን ያስነሳናል፤እኛም በፊቱ እንኖራለን።
3 ይሖዋን እናውቀዋለን፤ እሱን ለማወቅ ልባዊ ጥረት እናደርጋለን።
የእሱ መውጣት እንደ ንጋት ብርሃን የተረጋገጠ ነው፤እንደ ዶፍ ዝናብ፣ ምድርንም እንደሚያጠግበው የኋለኛው ዝናብወደ እኛ ይመጣል።”
4 “ኤፍሬም ሆይ፣ ምን ላድርግህ?
ይሁዳ ሆይ፣ ምን ላድርግህ?
ታማኝ ፍቅራችሁ እንደ ጠዋት ጉም፣ወዲያው እንደሚጠፋም ጤዛ ነውና።
5 ከዚህም የተነሳ በነቢያቴ አማካኝነት እቆራርጣቸዋለሁ፤+በአፌም ቃል እገድላቸዋለሁ።+
በእናንተም ላይ የምፈርደው ፍርድ እንደ ንጋት ብርሃን ያንጸባርቃል።+
6 ከመሥዋዕት ይልቅ ታማኝ ፍቅር፣*ሙሉ በሙሉ ከሚቃጠል መባም ይልቅ አምላክን ማወቅ ያስደስተኛልና።+
7 እነሱ ግን እንደ ተራ ሰዎች ቃል ኪዳኑን ተላለፉ።+
በዚያም እኔን ከዱኝ።
8 ጊልያድ የክፉ አድራጊዎች ከተማ ናት፤+ከተማዋ በደም ጨቅይታለች።+
9 የካህናቱ ማኅበር ሰውን አድብቶ እንደሚጠብቅ የወራሪዎች ቡድን ነው።
በሴኬም+ መንገድ ላይ ሰው ይገድላሉ፤ምግባራቸው አሳፋሪ ነውና።
10 በእስራኤል ቤት የሚሰቀጥጥ ነገር አይቻለሁ።
በዚያ ኤፍሬም ያመነዝራል፤+እስራኤል ራሱን አርክሷል።+
11 በአንጻሩ ግን ይሁዳ ሆይ፣ የሕዝቤን ምርኮኞች በምመልስበት ጊዜመከር ይጠብቅሃል።”+
የግርጌ ማስታወሻ
^ ወይም “ምሕረት።”