ሆሴዕ 7:1-16
7 “እስራኤልን ለመፈወስ በሞከርኩ ቁጥርየኤፍሬም በደል፣+የሰማርያም ክፋት ይገለጣል።+
እነሱ ያታልላሉና፤+ሌቦች ሰብረው ይገባሉ፤ የወራሪዎች ቡድን በውጭ ጥቃት ይሰነዝራል።+
2 እነሱ ግን ክፉ ድርጊታቸውን ሁሉ እንደማስታውስ ልብ አይሉም።+
የገዛ ድርጊታቸው ከቧቸዋል፤የሠሩት ሥራ ሁሉ በፊቴ ነው።
3 ንጉሡን በክፋታቸው፣መኳንንቱንም አታላይ በሆነ ድርጊታቸው ያስደስታሉ።
4 ሁሉም አመንዝሮች ናቸው፤አንድ ዳቦ ጋጋሪ እሳቱን አንዴ ካቀጣጠለው በኋላ፣ያቦካው ሊጥ ኩፍ እስኪል ድረስ እሳቱን መቆስቆስ እንደማያስፈልገው የጋለ ምድጃ ናቸው።
5 በንጉሣችን ክብረ በዓል ቀን፣ መኳንንቱ ታመሙ፤በወይን ጠጅ የተነሳ በቁጣ ተሞሉ።+
ንጉሡ ለፌዘኞች እጁን ዘረጋ።
6 እንደ ምድጃ የሚነድ ልብ ይዘው ይቀርባሉና።*
ዳቦ ጋጋሪው ሌሊቱን ሙሉ ይተኛል፤በማለዳ ምድጃው እንደሚንበለበል እሳት ይንቀለቀላል።
7 ሁሉም እንደ ምድጃ የጋሉ ናቸው፤ገዢዎቻቸውንም* ይውጣሉ።
ነገሥታታቸው ሁሉ ወድቀዋል፤+ከእነሱ መካከል ወደ እኔ የሚጮኽ ማንም የለም።+
8 ኤፍሬም ከብሔራት ጋር ይቀላቀላል።+
እሱ እንዳልተገላበጠ ቂጣ ነው።
9 እንግዶች ጉልበቱን በዘበዙ፤+ እሱ ግን ይህን አላወቀም።
ራሱንም ሽበት ወረሰው፤ እሱ ግን ይህን ልብ አላለም።
10 የእስራኤል ኩራት በራሱ ላይ መሥክሮበታል፤+ይህም ሁሉ ሆኖ ወደ አምላካቸው ወደ ይሖዋ አልተመለሱም፤+እሱንም አልፈለጉትም።
11 ኤፍሬም ማስተዋል እንደሌላት* ሞኝ ርግብ ነው።+
ግብፅን ተጣሩ፤+ ወደ አሦርም ሄዱ።+
12 የትም ቢሄዱ መረቤን በላያቸው እዘረጋለሁ።
እንደ ሰማይ ወፎች ወደ ታች አወርዳቸዋለሁ።
ለጉባኤያቸው በሰጠሁት ማስጠንቀቂያ መሠረት እገሥጻቸዋለሁ።+
13 ከእኔ ስለሸሹ ወዮላቸው!
በእኔ ላይ በደል ስለፈጸሙ ጥፋት ይምጣባቸው!
እነሱን ለመዋጀት ዝግጁ ነበርኩ፤ እነሱ ግን በእኔ ላይ ውሸት ተናገሩ።+
14 በአልጋቸው ላይ ሆነው ዋይ ዋይ ቢሉምእርዳታ ለማግኘት ከልባቸው ወደ እኔ አልጮኹም።+
ለእህላቸውና ለአዲስ የወይን ጠጃቸው ሲሉ ሰውነታቸውን ይተለትላሉ፤በእኔም ላይ ዓመፁ።
15 ያሠለጠንኳቸውና ክንዳቸውን ያበረታሁ ቢሆንምክፉ ነገር በማሴር በእኔ ላይ ተነስተዋል።
16 አካሄዳቸውን ለወጡ፤ ከፍ ወዳለ ነገር ግን አይደለም፤*ጅማቱ እንደረገበ ደጋን እምነት የማይጣልባቸው ሆነዋል።+
አለቆቻቸው እብሪተኛ ከሆነው አንደበታቸው የተነሳ በሰይፍ ይወድቃሉ።
በዚህም ምክንያት በግብፅ ምድር መሳለቂያ ይሆናሉ።”+