ሆሴዕ 9:1-17
9 “እስራኤል ሆይ፣ ሐሴት አታድርግ፤+እንደ ሌሎቹ ሕዝቦች ደስ አይበልህ።
ምንዝር በመፈጸም* ከአምላክህ ርቀሃልና።+
በየእህል አውድማ ላይ ለዝሙት አዳሪ የሚከፈለውን ደሞዝ ወደኸዋል።+
2 ሆኖም የእህል አውድማውና የወይን መጭመቂያው አይመግባቸውም፤አዲሱም የወይን ጠጅ ይቋረጥባቸዋል።+
3 በይሖዋ ምድር ላይ አይኖሩም፤+ይልቁንም ኤፍሬም ወደ ግብፅ ይመለሳል፤በአሦርም የረከሰ ነገር ይበላሉ።+
4 ከእንግዲህ ለይሖዋ የወይን ጠጅ መባ አያፈሱም፤+መሥዋዕታቸውም አያስደስተውም።+
እንደ እዝን እንጀራ ናቸው፤የሚበሉትም ሁሉ ራሳቸውን ያረክሳሉ።
ምግባቸው ለራሳቸው ብቻ* ነውና፤ወደ ይሖዋ ቤት አይገባም።
5 የምትሰበሰቡበትና* ለይሖዋ በዓል የምታከብሩበት ቀን ሲደርስምን ታደርጉ ይሆን?
6 እነሆ፣ ምድሪቱ በመውደሟ ለመሸሽ ይገደዳሉ።+
ግብፅ ትሰበስባቸዋለች፤+ ሜምፊስ ደግሞ ትቀብራቸዋለች።+
ከብር የተሠሩ ውድ ንብረቶቻቸውን ሳማ ይወርሰዋል፤በድንኳኖቻቸውም ውስጥ እሾሃማ ቁጥቋጦ ይበቅላል።
7 ምርመራ የሚካሄድበት ጊዜ ይመጣል፤+የበቀል ቀን ይመጣል፤እስራኤልም ይህን ይወቅ!
የእነሱ ነቢይ ሞኝ፣ በመንፈስ የሚናገረውም ሰው እንደ እብድ ይሆናል፤ምክንያቱም በደልህ ብዙ ነው፤ በአንተም ላይ የሚደርሰው ጥላቻ በዝቷል።”
8 የኤፍሬም ጠባቂ+ ከአምላኬ ጋር ነበር።+
አሁን ግን የነቢያቱ+ መንገዶች ሁሉ እንደ ወፍ አዳኝ ወጥመዶች ናቸው፤በአምላኩ ቤት ጠላትነት አለ።
9 በጊብዓ ዘመን እንደነበረው፣ ጥፋት በሚያስከትሉ ነገሮች ተዘፍቀዋል።+
እሱ በደላቸውን ያስባል፤ በሠሩትም ኃጢአት የተነሳ ይቀጣቸዋል።+
10 “እስራኤልን በምድረ በዳ እንዳለ ወይን ሆኖ አገኘሁት።+
አባቶቻችሁን ለመጀመሪያ ጊዜ ባፈራ የበለስ ዛፍ ላይ እንደ ጎመራ የበለስ ፍሬ ሆነው አየኋቸው።
ሆኖም ወደ ፌጎር ባአል ሄዱ፤+ለአሳፋሪውም ነገር* ራሳቸውን አሳልፈው ሰጡ፤+እንደወደዱትም ነገር አስጸያፊዎች ሆኑ።
11 የኤፍሬም ክብር እንደ ወፍ በሮ ይጠፋል፤መውለድ፣ ማርገዝም ሆነ መፀነስ የለም።+
12 ልጆች ቢያሳድጉም እንኳአንድም ሰው እስከማይቀር ድረስ የወላድ መሃን አደርጋቸዋለሁ፤+አዎ፣ ከእነሱ በራቅኩ ጊዜ ወዮላቸው!+
13 በግጦሽ ስፍራ የተተከለው ኤፍሬም ለእኔ እንደ ጢሮስ ነበር፤+አሁን ግን ኤፍሬም ልጆቹን ለእርድ አሳልፎ ይሰጣል።”
14 ይሖዋ ሆይ፣ ልትሰጣቸው የሚገባውን ስጣቸው፤የሚጨነግፍ ማህፀንና የደረቁ* ጡቶች ስጣቸው።
15 “ክፉ ድርጊታቸውን ሁሉ በጊልጋል ፈጸሙ፤+ እኔም በዚያ ጠላኋቸው።
በሠሩት ክፉ ድርጊት የተነሳ ከቤቴ አባርራቸዋለሁ።+
ከእንግዲህ ወዲያ ፍቅሬን እነፍጋቸዋለሁ፤+አለቆቻቸው ሁሉ እልኸኞች ናቸው።
16 ኤፍሬም ጉዳት ይደርስበታል።+
ሥራቸው ይደርቃል፤ አንዳችም ፍሬ አያፈሩም።
ቢወልዱ እንኳ የሚወዷቸውን ልጆቻቸውን እገድላለሁ።”
17 እሱን ስላልሰሙት+አምላኬ ይተዋቸዋል፤በብሔራትም መካከል ተንከራታች ይሆናሉ።+