መኃልየ መኃልይ 1:1-17

  • ከመዝሙሮች ሁሉ የሚበልጥ መዝሙር (1)

  • ልጃገረዷ (2-7)

  • የኢየሩሳሌም ሴቶች ልጆች (8)

  • ንጉሡ (9-11)

    • “የወርቅ ጌጦች እንሠራልሻለን” (11)

  • ልጃገረዷ (12-14)

    • “ውዴ ለእኔ ጥሩ መዓዛ እንዳለው በከረጢት ያለ ከርቤ ነው” (13)

  • እረኛው (15)

    • ‘ፍቅሬ ሆይ፣ አንቺ ውብ ነሽ’

  • ልጃገረዷ (16, 17)

    • ‘ውዴ ሆይ፣ አንተ ውብ ነህ’ (16)

1  ከመዝሙሮች ሁሉ የሚበልጠው የሰለሞን+ መዝሙር፦*   “በከንፈሩ መሳም ይሳመኝ፤የፍቅር መግለጫዎችህ ከወይን ጠጅ ይልቅ ደስ ያሰኛሉና።+   የዘይትህ መዓዛ ደስ ይላል።+ ስምህ ጥሩ መዓዛ እንዳለው የሚፈስ ዘይት ነው።+ ቆነጃጅት የሚወዱህ ለዚህ ነው።   ይዘኸኝ ሂድ፤* አብረን እንሩጥ። ንጉሡ ወደ እልፍኞቹ አስገብቶኛል! በአንተ ደስ ይበለን፤ ሐሴትም እናድርግ። ከወይን ጠጅ ይልቅ የፍቅር መግለጫዎችህን እናወድስ።* አንተን መውደዳቸው* ተገቢ ነው።   የኢየሩሳሌም ሴቶች ልጆች ሆይ፣ እኔ ጥቁር ብሆንም ውብ ነኝ፤እንደ ቄዳር+ ድንኳኖች፣ እንደ ሰለሞን ድንኳኖችም+ ነኝ።   ጥቁር ስለሆንኩ ትኩር ብላችሁ አትዩኝ፤ፀሐይ ፊቴን አክስሎታልና። ወንድሞቼ በጣም ተቆጡኝ፤የወይን እርሻዎች ጠባቂ አደረጉኝ፤የገዛ ራሴን የወይን እርሻ ግን መጠበቅ አልቻልኩም።   “እጅግ የምወድህ* ፍቅረኛዬ፣መንጋህን የት እንደምታሰማራ፣+እኩለ ቀንም ላይ የት እንደምታሳርፍ ንገረኝ። በጓደኞችህ መንጎች መካከልበመሸፈኛ* ፊቷን ተሸፋፍና እንደምትቅበዘበዝ ሴት ለምን ልሁን?”   “አንቺ ከሴቶች ሁሉ እጅግ የተዋብሽ ሆይ፣ የማታውቂ ከሆነየመንጋውን ዱካ ተከትለሽ ሂጂ፤የፍየል ግልገሎችሽንም በእረኞቹ ድንኳኖች አጠገብ አሰማሪ።”   “ፍቅሬ ሆይ፣ የፈርዖንን ሠረገሎች በሚጎትቱ ፈረሶች መካከል እንዳለች ባዝራ* ውብ ነሽ።+ 10  ጉንጮችሽ በማስዋቢያ ተውበዋል፤*አንገትሽም በጨሌ ሐብል አጊጧል። 11  በብር ፈርጥ የተንቆጠቆጡየወርቅ ጌጦች* እንሠራልሻለን።” 12  “ንጉሡ ክብ ጠረጴዛው ጋ ተቀምጦ ሳለየሽቶዬ*+ መዓዛ አካባቢውን አወደው። 13  ውዴ ለእኔ ጥሩ መዓዛ እንዳለው በከረጢት ያለ ከርቤ+ ነው፤በጡቶቼ መካከል ያድራል። 14  ውዴ በኤንገዲ+ የወይን እርሻዎች መካከልእጅብ ብሎ እንደበቀለ የሂና ተክል+ ነው።” 15  “ፍቅሬ ሆይ፣ እነሆ፣ አንቺ ውብ ነሽ። እነሆ፣ አንቺ ውብ ነሽ። ዓይኖችሽ እንደ ርግብ+ ዓይኖች ናቸው።” 16  “ውዴ ሆይ፣ እነሆ፣ አንተ ውብ* ነህ፤ ደግሞም ደስ ትላለህ።+ አልጋችን በለምለም ቅጠል መካከል ነው። 17  የቤታችን* ተሸካሚዎች አርዘ ሊባኖሶች፣ጣሪያችንም የጥድ ዛፎች ናቸው።

የግርጌ ማስታወሻ

መኃልየ መኃልይ የሚለው የመጽሐፉ ስም “ከመዝሙሮች ሁሉ የሚበልጥ መዝሙር” የሚል ትርጉም አለው።
ቃል በቃል “እየሳብክ ውሰደኝ።”
ወይም “ከወይን ጠጅ ይልቅ ስለ ፍቅር መግለጫዎችህ እናውራ።”
ቆነጃጅቱን ያመለክታል።
ወይም “በሐዘን መሸፈኛ።”
ወይም “ነፍሴ እጅግ የምትወድህ።”
ወይም “ባዝራዬ።”
“በሹሩባዎች መካከል ሲታዩ ያምራሉ” ማለትም ሊሆን ይችላል።
ወይም “ክብ የወርቅ ጌጦች።”
ቃል በቃል “የናርዶሴ።”
ወይም “አንተ መልከ መልካም።”
ወይም “የታላቁ ቤታችን።”