መኃልየ መኃልይ 2:1-17
2 “እኔ ግን በባሕር ዳርቻ ላይ የሚበቅል የሳሮን አበባ* ነኝ፤የሸለቆም አበባ ነኝ።”+
2 “ፍቅሬ በሴቶች መካከል ስትታይበእሾህ መካከል እንዳለ አበባ ናት።”
3 “ውዴ በወንዶች መካከል ሲታይበዱር ዛፎች መካከል እንዳለ የፖም ዛፍ ነው።
በጥላው ሥር ለመቀመጥ እጅግ እጓጓለሁ፤ፍሬውም ለአፌ ጣፋጭ ነው።
4 ወደ ግብዣ ቤት* ወሰደኝ፤የፍቅር ዓርማውንም በእኔ ላይ አውለበለበ።
5 በዘቢብ ቂጣ ኃይሌን አድሱልኝ፤+በፖም አበረታቱኝ፤በፍቅሩ ተይዤ ታምሜአለሁና።
6 ግራ እጁን ተንተርሻለሁ፤ቀኝ እጁም አቅፎኛል።+
7 የኢየሩሳሌም ሴቶች ልጆች ሆይ፣ በራሱ እስኪነሳሳ ድረስፍቅርን በውስጤ እንዳትቀሰቅሱ ወይም እንዳታነሳሱ፣
በሜዳ ፍየሎችና+ በመስክ ላይ ባሉ አጋዘኖች አምላችኋለሁ።+
8 እነሆ፣ ውዴ ተራሮቹን እየወጣና
በኮረብቶቹ ላይ እየዘለለ ሲመጣድምፁ ይሰማኛል!
9 ውዴ፣ የሜዳ ፍየል ወይም የአጋዘን ግልገል+ ይመስላል።
በመስኮት በኩል ትኩር ብሎ እየተመለከተ፣በፍርግርጉ በኩል አጮልቆ እያየከግድግዳችን ጀርባ ቆሟል።
10 ውዴ እንዲህ አለኝ፦
‘ፍቅሬ ሆይ፣ ተነሽ፤የእኔ ቆንጆ፣ ነይ አብረን እንሂድ።
11 እነሆ፣ ክረምቱ አልፏል።
ዝናቡ ቆሟል፤ ደግሞም ጠፍቷል።
12 በምድሩ ላይ አበቦች አብበዋል፤+ተክሎች የሚገረዙበት ጊዜ ደርሷል፤+በምድራችንም ላይ የዋኖስ ዝማሬ ተሰምቷል።+
13 የበለስ ዛፏ መጀመሪያ ላይ ያፈራቻቸው ፍሬዎች በስለዋል፤+የወይን ተክሎቹም አብበው መዓዛቸውን ሰጥተዋል።
ፍቅሬ ሆይ፣ ተነሽና ነይ፤የእኔ ቆንጆ፣ ነይ አብረን እንሂድ።
14 በዓለቶች መሃል በሚገኝ መሸሸጊያ፣በገደላማ ስፍራ ባለ ሰዋራ ቦታ ያለሽ ርግቤ ሆይ፣+እስቲ ልይሽ፤ ድምፅሽንም ልስማው፤+ድምፅሽ ማራኪ፣ ቁመናሽም ያማረ ነውና።’”+
15 “ቀበሮዎቹን ይኸውም የወይን እርሻዎቹን የሚያበላሹትንትናንሽ ቀበሮዎች ያዙልን፤የወይን እርሻችን አብቧልና።”
16 “ውዴ የእኔ ነው፤ እኔም የእሱ ነኝ።+
መንጋውን በአበቦች መካከል እየጠበቀ ነው።+
17 የቀኑ ነፋስ መንፈስ ከመጀመሩና ጥላው ከመሸሹ በፊትውዴ ሆይ፣ እንደ ሜዳ ፍየልወይም በመካከላችን ባሉት ተራሮች* ላይ እንደሚገኝ የአጋዘን ግልገል በፍጥነት ተመለስ።+