መኃልየ መኃልይ 3:1-11

  • ልጃገረዷ (1-5)

    • ‘የምወደውን ፈለግኩት’ (1)

  • የጽዮን ሴቶች ልጆች (6-11)

    • የሰለሞን አጀብ

3  “ሌሊት በአልጋዬ ላይ ሆኜየምወደውን* ሰው ለማግኘት ተመኘሁ።+ ፈለግኩት፤ ግን አላገኘሁትም።+   ተነስቼ በከተማዋ ውስጥ እዘዋወራለሁ፤የምወደውን* ሰውእስቲ በጎዳናዎቹና በአደባባዮቹ ልፈልገው። ፈለግኩት፤ ግን አላገኘሁትም።   በከተማዋ ውስጥ የሚዘዋወሩት ጠባቂዎች አገኙኝ።+ እኔም ‘የምወደውን* ሰው አይታችሁታል?’ ብዬ ጠየቅኳቸው።   ከእነሱ ገና እልፍ እንዳልኩየምወደውን* ሰው አገኘሁት። አጥብቄም ያዝኩት፤ወደ እናቴ ቤት፣ ወደ ፀነሰችኝም ሴት እልፍኝእስካስገባው ድረስ አለቀኩትም።+   የኢየሩሳሌም ሴቶች ልጆች ሆይ፣ በራሱ እስኪነሳሳ ድረስፍቅርን በውስጤ እንዳትቀሰቅሱ ወይም እንዳታነሳሱ በሜዳ ፍየሎችና በመስክ ላይ ባሉ አጋዘኖች አምላችኋለሁ።”+   “በከርቤና በነጭ ዕጣን፣ጥሩ መዓዛ ባላቸውም የነጋዴ ቅመማ ቅመሞች ታውዶ፣+እንደ ጭስ ዓምድ ከምድረ በዳ እየመጣ ያለው ይህ ነገር ምንድን ነው?”   “እነሆ፣ ይህ የሰለሞን ድንክ አልጋ ነው። ከእስራኤል ኃያላን የተውጣጡስልሳ ኃያላን አጅበውታል፤+   ሁሉም ሰይፍ የታጠቁናበውጊያ የሠለጠኑ ናቸው፤እያንዳንዳቸውም በሌሊት የሚያጋጥሙ አስፈሪ ነገሮችን ለመከላከልሰይፋቸውን ወገባቸው ላይ ታጥቀዋል።”   “ይህ፣ ንጉሥ ሰለሞን ከሊባኖስ እንጨት+ለራሱ ያሠራው የንጉሥ ድንክ አልጋ* ነው። 10  ዓምዶቹን የሠራው ከብር፣መደገፊያዎቹን ደግሞ ከወርቅ ነው። መቀመጫው በሐምራዊ ሱፍ የተሠራ ነው፤ውስጡንም የኢየሩሳሌም ሴቶች ልጆችበፍቅር ተነሳስተው ለብጠውታል።” 11  “እናንተ የጽዮን ሴቶች ልጆች ሆይ፣ወጥታችሁ ንጉሥ ሰለሞንን ተመልከቱ፤በሠርጉ ዕለት፣ልቡ ሐሴት ባደረገበት በዚያ ቀን፣እናቱ+ የሠራችለትን የሠርግ አክሊል* ደፍቷል።”

የግርጌ ማስታወሻ

ወይም “ነፍሴ የምትወደውን።”
ወይም “ነፍሴ የምትወደውን።”
ወይም “ነፍሴ የምትወደውን።”
ወይም “ነፍሴ የምትወደውን።”
ከፍተኛ ሥልጣን ያለውን ሰው ተሸክሞ ለመውሰድ የሚያገለግል መሸፈኛ ያለው ድንክ አልጋ።
ወይም “የአበባ ጉንጉን።”