መኃልየ መኃልይ 6:1-13
6 “ከሴቶች ሁሉ እጅግ የተዋብሽ ሆይ፣ውድሽ የት ሄደ?
ለመሆኑ ውድሽ የሄደው በየት በኩል ነው?
አብረንሽ እንፈልገው።”
2 “ውዴ መንጋውን በአትክልት ቦታዎቹ መካከል ለማሰማራትናአበቦችን ለመቅጠፍየቅመማ ቅመም ተክሎች መደብ ወዳለበትወደ አትክልት ቦታው ወርዷል።+
3 እኔ የውዴ ነኝ፤ውዴም የእኔ ነው።+
እሱ መንጋውን በአበቦች መካከል እየጠበቀ ነው።”+
4 “ፍቅሬ ሆይ፣ አንቺ እንደ ቲርጻ*+ ቆንጆ ነሽ፤+እንደ ኢየሩሳሌምም ውብ ነሽ፤+በዓርማዎቻቸው ዙሪያ እንደተሰለፉ ወታደሮች እጅግ ታምሪያለሽ።+
5 ስሜቴን አውከውታልና፣ዓይኖችሽን+ ከእኔ ላይ አንሺ።
ፀጉርሽ ከጊልያድ እየተግተለተለ እንደሚወርድየፍየል መንጋ ነው።+
6 ጥርሶችሽ ታጥበው እንደወጡ፣ሁሉም መንታ መንታ እንደወለዱየበግ መንጋ ናቸው፤ከመካከላቸውም ግልገሉን ያጣ የለም።
7 በመሸፈኛሽ ውስጥ ያሉት ጉንጮችሽ*የተከፈለ ሮማን ይመስላሉ።
8 እርግጥ 60 ንግሥቶች፣80 ቁባቶችናቁጥራቸው በውል የማይታወቅ ቆነጃጅት ሊኖሩ ይችላሉ።+
9 እንከን የሌለባት ርግቤ+ ግን አንድ ብቻ ናት።
እሷ ለእናቷ ብርቅዬ ልጅ ናት።
በወለደቻት ዘንድ እጅግ ተወዳጅ* ናት።
ሴቶች ልጆች አይተዋት ‘የታደልሽ ነሽ’ ይሏታል፤ንግሥቶችና ቁባቶችም ያወድሷታል።
10 ‘እንደ ማለዳ ወጋገን የምታበራ፣*እንደ ሙሉ ጨረቃ ውብ የሆነች፣እንደ ፀሐይ ብርሃን የጠራች፣በዓርማዎቻቸው ዙሪያ እንደተሰለፉ ወታደሮች እጅግ የምታምረው ይህች ሴት ማን ናት?’”+
11 “በሸለቆው* ውስጥ ያቆጠቆጡትን ተክሎች ለማየት፣ደግሞም ወይኑ ለምልሞ፣*የሮማን ዛፎቹም አብበው እንደሆነ ለመመልከትየገውዝ ዛፎች ወዳሉበት ወደ አትክልት ቦታው ወረድኩ።+
12 ምንም ሳይታወቀኝምኞቴ* የተከበሩ* ወገኖቼየያዟቸው ሠረገሎች ወዳሉበት ወሰደኝ።”
13 “አንቺ ሱላማዊት፣ ተመለሺ፤ ተመለሺ!
እናይሽ ዘንድተመለሺ፤ ተመለሺ!”
“በሱላማዊቷ ላይ የምታፈጡት ለምንድን ነው?”+
“እሷ የመሃናይምን ጭፈራ* ትመስላለች!”