መኃልየ መኃልይ 7:1-13

  • ንጉሡ (1-9ሀ)

    • ‘አንቺ የተወደድሽ ልጃገረድ፣ እንዴት ደስ ታሰኛለሽ!’ (6)

  • ልጃገረዷ (9ለ-13)

    • “እኔ የውዴ ነኝ፤ እሱም የሚመኘው እኔን ነው” (10)

7  “አንቺ የተከበርሽ ልጃገረድ ሆይ፣እግሮችሽ በነጠላ ጫማሽ ውስጥ ሲታዩ እንዴት ያምራሉ! የዳሌዎችሽ ቅርጽየእጅ ባለሙያ የተጠበበባቸው ጌጦች ይመስላሉ።   እምብርትሽ እንደ ክብ ሳህን ነው። የተደባለቀ ወይን ጠጅ ከእሱ አይታጣ። ሆድሽ ዙሪያውን በአበቦች እንደታጠረየስንዴ ክምር ነው።   ሁለቱ ጡቶችሽ ሁለት ግልገሎችን፣የሜዳ ፍየል መንታዎችን ይመስላሉ።+   አንገትሽ+ በዝሆን ጥርስ የተሠራ ማማ ይመስላል።+ ዓይኖችሽ+ በባትራቢም በር አጠገብ እንዳሉትየሃሽቦን+ ኩሬዎች ናቸው። አፍንጫሽ ወደ ደማስቆ አቅጣጫ እንደሚመለከትየሊባኖስ ማማ ነው።   ራስሽ እንደ ቀርሜሎስ ተራራ+ አክሊል ሆኖልሻል፤ፀጉርሽ*+ ሐምራዊ ሱፍ+ ይመስላል። ንጉሡ በዘንፋላው ፀጉርሽ ተማርኳል።*   አንቺ የተወደድሽ ልጃገረድ ሆይ፣ ምንኛ ውብ ነሽ! እንዴትስ ደስ ታሰኛለሽ!በጣም ከሚያስደስቱ ነገሮች ሁሉ በላይ ትማርኪያለሽ!   ቁመናሽ የዘንባባ ዛፍ ይመስላል፤ጡቶችሽ ደግሞ የቴምር ዘለላ ይመስላሉ።+   እኔም እንዲህ አልኩ፦ ‘የቴምር ዘለላዎቹን መያዝ እንድችልዛፉ ላይ እወጣለሁ።’ ጡቶችሽ እንደ ወይን ዘለላ ይሁኑ፤የትንፋሽሽ መዓዛ እንደ ፖም ሽታ ይሁን፤   አፍሽም* እንደ ምርጥ ወይን ጠጅ ይሁን።” “ይህ የወይን ጠጅ ለውዴ እየተንቆረቆረ ይውረድ፤በተኙ ሰዎች ከንፈር በቀስታ ይፍሰስ። 10  እኔ የውዴ ነኝ፤+እሱም የሚመኘው እኔን ነው። 11  ውዴ ሆይ፣ ና፤ወደ መስክ እንሂድ፤በሂና ተክሎች+ መካከል እንቀመጥ። 12  ወይኑ ለምልሞ፣*አበባው ፈክቶ፣+የሮማን ዛፎቹም አብበው እንደሆነ ለማየት+በማለዳ ተነስተን ወደ ወይን እርሻዎቹ እንሂድ። እኔም በዚያ ለአንተ ያለኝን ፍቅር እገልጽልሃለሁ።+ 13  የዱዳይም* ፍሬዎቹ+ መዓዛቸውን ሰጥተዋል፤በደጆቻችንም ሁሉም ዓይነት ምርጥ ፍሬዎች አሉ።+ ውዴ ሆይ፣ አዲሶቹንም ሆነ በፊት የተቀጠፉትን ፍሬዎችለአንተ አስቀምጬልሃለሁ።

የግርጌ ማስታወሻ

ቃል በቃል “ራስሽ።”
ወይም “ታስሮ ተይዟል።”
ቃል በቃል “ላንቃሽም።”
ወይም “አቆጥቁጦ።”
እንግሊዝኛ፣ ማንድሬክ። ከድንች ዝርያ የሚመደብ ተክል ሲሆን ብርቱካንማ ቀለም ያለው ፍሬ ያፈራል።