መኃልየ መኃልይ 8:1-14

  • ልጃገረዷ (1-4)

    • “እንደ ወንድሜ በሆንክ!” (1)

  • የልጃገረዷ ወንድሞች (5ለ)

    • ‘ውዷን ደገፍ ብላ የምትመጣው ይህች ማን ናት?’

  • ልጃገረዷ (5ለ-7)

    • “ፍቅር እንደ ሞት የበረታ ነው” (6)

  • የልጃገረዷ ወንድሞች (8, 9)

    • “እሷ ቅጥር ብትሆን . . . በር ብትሆን ግን . . .” (9)

  • ልጃገረዷ (10-12)

    • “እኔ ቅጥር ነኝ” (10)

  • እረኛው (13)

    • ‘ድምፅሽን ልስማው’

  • ልጃገረዷ (14)

    • ‘እንደ ሜዳ ፍየል ፍጠን’

8  “ምነው አንተ፣ የእናቴን ጡት እንደጠባ፣እንደ ወንድሜ በሆንክ! እንዲህ ቢሆን ኖሮ ውጭ ሳገኝህ በሳምኩህ ነበር፤+ማንም ባልናቀኝ ነበር።   እኔም ወዳስተማረችኝወደ እናቴ ቤት በወሰድኩህናወደዚያ ባስገባሁህ ነበር።+ ትጠጣው ዘንድ ቅመም የተጨመረበት ወይን ጠጅናየሮማን ጭማቂ በሰጠሁህ ነበር።   ግራ እጁን በተንተራስኩ፣ቀኝ እጁም ባቀፈኝ ነበር።+   የኢየሩሳሌም ሴቶች ልጆች ሆይ፣ በራሱ እስኪነሳሳ ድረስ ፍቅርን በውስጤ እንዳትቀሰቅሱ ወይም እንዳታነሳሱ አምላችኋለሁ።”+   “ውዷን ደገፍ ብላከምድረ በዳ የምትመጣው ይህች ማን ናት?” “ከፖም ዛፍ ሥር ቀሰቀስኩህ። በዚያ እናትህ አንተን ለመውለድ አማጠች። በዚያም ወላጅ እናትህ ምጥ ይዟት ነበር።   እንደ ማኅተም በልብህ፣እንደ ማኅተም በክንድህ አስቀምጠኝ፤ፍቅር እንደ ሞት የበረታ ነውና፤+ታማኝነትም* እንደ መቃብር* ጽኑ ነው፤ የፍቅር ወላፈን የእሳት ወላፈን ነው፤ የያህም* ነበልባል ነው።+   ጎርፍ ፍቅርን ሊያጠፋው አይችልም፤+ወንዞችም ጠራርገው ሊወስዱት አይችሉም።+ አንድ ሰው ለፍቅር ሲል የቤቱን ሀብት ሁሉ ለመስጠት ቢያቀርብሰዎች በጣም ይንቁበታል።”*   “ገና ጡት ያላወጣችትንሽ እህት አለችን።+ እሷን በሚጠይቁን ቀንለእህታችን ምን ብናደርግ ይሻላል?”   “እሷ ቅጥር ብትሆንበላይዋ ላይ የብር ጉልላት እንሠራለን፤በር ብትሆን ግንከአርዘ ሊባኖስ በተሠራ ሳንቃ እናሽጋታለን።” 10  “እኔ ቅጥር ነኝ፤ጡቶቼም እንደ ማማ ናቸው። በእሱም ፊትሰላም እንዳገኘች ሴት ሆንኩ። 11  ሰለሞን በበዓልሃሞን የወይን እርሻ ነበረው።+ እሱም የወይን እርሻውን ለጠባቂዎች በአደራ ሰጠ። እያንዳንዳቸውም ለሚያገኙት ፍሬ አንድ ሺህ የብር ሰቅል ያመጡ ነበር። 12  የራሴ የሆነ የወይን እርሻ አለኝ። ሰለሞን ሆይ፣ አንድ ሺው የብር ሰቅል* የአንተ ነው፤ሁለት መቶው ደግሞ ፍሬውን ለሚጠብቁት ነው።” 13  “አንቺ በአትክልት ቦታዎቹ የምትኖሪ ሆይ፣+ጓደኞቼ* ድምፅሽን ያዳምጣሉ። እስቲ እኔም ልስማው።”+ 14  “ውዴ ሆይ፣ ቶሎ ና፤እንደ ሜዳ ፍየልወይም የቅመም ተክሎች በሚበቅሉባቸው ተራሮች ላይ እንዳለየአጋዘን ግልገል ፍጠን።”+

የግርጌ ማስታወሻ

ወይም “ሙሉ በሙሉ ያደሩ መሆንም።”
ወይም “ሲኦል።” የሰው ልጆችን ሁሉ መቃብር ያመለክታል። የቃላት መፍቻውን ተመልከት።
“ያህ” የይሖዋ ስም አጭር መጠሪያ ነው።
“ይንቁታል” ማለትም ሊሆን ይችላል።
ቃል በቃል “አንድ ሺው።”
“ጓደኞችሽ” ማለትም ሊሆን ይችላል።