መክብብ 1:1-18

  • “ሁሉም ነገር ከንቱ ነው!” (1-11)

    • ‘ምድር ለዘላለም ጸንታ ትኖራለች’ (4)

    • የተፈጥሮ ዑደቶች ቀጣይ ናቸው (5-7)

    • “ከፀሐይ በታች ምንም አዲስ ነገር የለም” (9)

  • የሰው ጥበብ ውስን ነው (12-18)

    • ነፋስን ማሳደድ (14)

1  በኢየሩሳሌም የነገሠው+ የሰብሳቢው*+ የዳዊት ልጅ ቃል።   ሰብሳቢው “የከንቱ ከንቱ* ነው!የከንቱ ከንቱ ነው! ሁሉም ነገር ከንቱ ነው!” አለ።+   ሰው ከፀሐይ በታች በትጋት ከሚያከናውነውና ከሚለፋበት ሥራ ሁሉየሚያገኘው ጥቅም ምንድን ነው?+   ትውልድ ይሄዳል፤ ትውልድ ይመጣል፤ምድር ግን ለዘላለም ጸንታ ትኖራለች።*+   ፀሐይ ትወጣለች፤* ደግሞም ትጠልቃለች፤ከዚያም ዳግመኛ ወደምትወጣበት ቦታ ለመመለስ ትጣደፋለች።*+   ነፋስ ወደ ደቡብ ይነፍሳል፤ ወደ ሰሜንም ዞሮ ይሄዳል፤ክብ እየሠራ ያለማቋረጥ ይሽከረከራል፤ ደግሞም ነፋሱ ዑደቱን ይቀጥላል።   ጅረቶች* ሁሉ ወደ ባሕር ይፈስሳሉ፤ ሆኖም ባሕሩ አይሞላም።+ ጅረቶቹ እንደገና ይፈስሱ ዘንድ ወደሚነሱበት ወደዚያው ቦታ ተመልሰው ይሄዳሉ።+   ሁሉ ነገር አሰልቺ ነው፤ሁሉንም ነገር ሊገልጽ የሚችል ሰው የለም። ዓይን አይቶ አይጠግብም፤ጆሮም ሰምቶ አይሞላም።   ከዚህ በፊት የነበረው ነገር ወደፊትም ይሆናል፤ከዚህ በፊት የተደረገውም ነገር እንደገና ይደረጋል፤ከፀሐይ በታች ምንም አዲስ ነገር የለም።+ 10  አንድ ሰው “ተመልከት፣ ይህ አዲስ ነገር ነው” ሊል የሚችለው ነገር ይኖራል? ከጥንት ጀምሮ የነበረ ነው፤ከእኛ ዘመን በፊት የነበረ ነው። 11  በቀድሞ ዘመን የነበሩትን ሰዎች ማንም አያስታውሳቸውም፤ከጊዜ በኋላ የሚመጡትንም የሚያስታውሳቸው አይኖርም፤ከእነሱ በኋላ የሚነሱት ሰዎችም እንኳ አያስታውሷቸውም።+ 12  እኔ ሰብሳቢው በኢየሩሳሌም፣ የእስራኤል ንጉሥ ነበርኩ።+ 13  ከሰማይ በታች የተሠራውን ነገር ሁሉ ይኸውም አምላክ የሰው ልጆች እንዲጠመዱበት የሰጣቸውን አሰልቺ ሥራ በጥበብ+ ለማጥናትና ለመመርመር ከልቤ ጥረት አደረግኩ።+ 14  ከፀሐይ በታች የተሠራውን ሥራ ሁሉ ተመለከትኩ፤እነሆ፣ ሁሉም ከንቱ ነፋስንም እንደማሳደድ ነው።+ 15  የተጣመመ ነገር ሊቃና አይችልም፤የሌለም ነገር በምንም መንገድ ሊቆጠር አይችልም። 16  እኔም በልቤ እንዲህ አልኩ፦ “እነሆ፣ ከእኔ በፊት በኢየሩሳሌም ከነበሩት ሁሉ እጅግ የላቀ ጥበብ አገኘሁ፤+ ልቤም ከፍተኛ ጥበብና እውቀት አገኘ።”+ 17  እኔም ጥበብንና እብደትን* እንዲሁም ሞኝነትን ለመረዳት ከልቤ ጥረት አደረግኩ፤+ ይህም ቢሆን ነፋስን እንደማሳደድ ነው። 18  ጥበብ ሲበዛ ብስጭትም ይበዛልና፤በመሆኑም እውቀትን የሚጨምር ሁሉ ሥቃይንም ይጨምራል።+

የግርጌ ማስታወሻ

የዚህ መጽሐፍ ስያሜ በዕብራይስጥ ቆኼሌት ሲሆን ቃሉ “ሰብሳቢ፣ ሰዎችን አንድ ላይ የሚሰበስብ” የሚል ትርጉም አለው።
ወይም “ዋጋ ቢስ።”
ቃል በቃል “ትቆማለች።”
ወይም “ብርሃን ትፈነጥቃለች።”
ወይም “እያለከለከች ትመለሳለች።”
ወይም “የክረምት ጅረቶች፤ ወቅት ጠብቀው የሚፈስሱ ጅረቶች።”
ወይም “ከልክ ያለፈ ቂልነትን።”