መክብብ 11:1-10

  • በተከፈተልህ አጋጣሚ ተጠቀም (1-8)

    • “ቂጣህን በውኃ ላይ ጣል” (1)

    • ከማለዳ እስከ ምሽት ዘርህን ዝራ (6)

  • የወጣትነት ዕድሜህን በማስተዋል ተጠቀምበት (9, 10)

11  ቂጣህን በውኃ ላይ ጣል፤*+ ከብዙ ቀናት በኋላ መልሰህ ታገኘዋለህና።+    ካለህ ነገር ላይ ለሰባት፣ እንዲያውም ለስምንት አካፍለህ ስጥ፤+ በምድር ላይ የሚመጣውን አደጋ* አታውቅምና።  ደመናት ውኃ ካዘሉ በምድር ላይ ዶፍ ያወርዳሉ፤ እንዲሁም ዛፍ በስተ ደቡብ ወይም በስተ ሰሜን ከወደቀ በዚያው በወደቀበት ይቀራል።  ነፋስን የሚጠባበቅ አይዘራም፤ ደመናትንም የሚመለከት አያጭድም።+  መንፈስ፣ በእርጉዝ ሴት ውስጥ በሚገኝ ሕፃን አጥንቶች* ላይ እንዴት እንደሚሠራ እንደማታውቅ ሁሉ፣+ ሁሉንም ነገር የሚያከናውነውን የእውነተኛውን አምላክ ሥራም አታውቅም።+  በማለዳ ዘርህን ዝራ፤ እስከ ምሽትም ድረስ እጅህ ሥራ አይፍታ፤+ ይህ ወይም ያ የትኛው እንደሚያድግ ወይም ደግሞ ሁለቱም ይጸድቁ እንደሆነ አታውቅምና።  ብርሃን ደስ ያሰኛል፤ ፀሐይንም ማየት ለዓይን መልካም ነው።  ሰው የቱንም ያህል ብዙ ዓመት ቢኖር በእያንዳንዱ ቀን ደስ ይበለው።+ ሆኖም በጨለማ የተዋጡት ቀናት ብዙ ሊሆኑ እንደሚችሉ መዘንጋት አይኖርበትም፤ የሚመጣው ሁሉ ከንቱ ነው።+  አንተ ወጣት፣ በወጣትነትህ ጊዜ ደስ ይበልህ፤ በወጣትነትህም ዘመን ልብህ ደስ ይበለው። የልብህን መንገድ ተከተል፤ ዓይንህ በሚመራህም መንገድ ሂድ፤ ሆኖም ስለ እነዚህ ነገሮች ሁሉ እውነተኛው አምላክ ወደ ፍርድ እንደሚያመጣህ* እወቅ።+ 10  ስለዚህ የሚያስጨንቁ ነገሮችን ከልብህ አስወግድ፤ ጎጂ ነገሮችንም ከሰውነትህ አርቅ፤* ወጣትነትና የለጋነት ዕድሜ ከንቱ ናቸውና።+

የግርጌ ማስታወሻ

ወይም “ስደድ።”
ወይም “ክፉ ነገር።”
ቃል በቃል “ማህፀን ውስጥ ባሉ አጥንቶች።”
ወይም “እንደሚጠይቅህ።”
ቃል በቃል “ከሥጋህ አርቅ።”