መዝሙር 10:1-18
ל [ላሜድ]
10 ይሖዋ ሆይ፣ ርቀህ የምትቆመው ለምንድን ነው?
በመከራ ጊዜ ራስህን የምትሰውረው ለምንድን ነው?+
2 ክፉ ሰው በእብሪት ተነሳስቶ ምስኪኑን ያሳድዳል፤+ይሁንና በወጠነው ሴራ ይያዛል።+
3 ክፉው ሰው በራስ ወዳድነት ምኞቱ ይኩራራልና፤*+ስግብግብ የሆነውንም ሰው ይባርካል፤*נ [ኑን]
ይሖዋንም ያቃልላል።
4 ክፉው ሰው ከትዕቢቱ የተነሳ ምንም ምርምር አያደርግም፤“አምላክ የለም” ብሎ ያስባል።+
5 መንገዱ ሁልጊዜ የተሳካ ነው፤+ሆኖም ፍርድህ እሱ ሊገነዘበው ከሚችለው በላይ ነው፤+በጠላቶቹ ሁሉ ላይ ያፌዛል።*
6 በልቡ እንዲህ ይላል፦ “ፈጽሞ አልናወጥም፤*ከትውልድ እስከ ትውልድምንም መከራ አይደርስብኝም።”+
פ [ፔ]
7 አፉ በእርግማን፣ በውሸትና በዛቻ የተሞላ ነው፤+ከምላሱ ሥር ችግርና ጉዳት የሚያስከትል ነገር አለ።+
8 በመንደሮቹ አጠገብ አድብቶ ይጠብቃል፤ከተደበቀበት ቦታ ወጥቶ ንጹሑን ሰው ይገድላል።+
ע [አይን]
ዓይኖቹ ያልታደለውን ሰለባ ይጠባበቃሉ።+
9 በጎሬው ውስጥ እንዳለ* አንበሳ በተደበቀበት ቦታ አድፍጦ ይጠብቃል።+
ምስኪኑን ሰው ለመያዝ ይጠባበቃል።
ምስኪኑን ሰው መረቡ ውስጥ አስገብቶ ይይዘዋል።+
10 ሰለባው ይደቅቃል፤ ደግሞም ይወድቃል፤ያልታደሉ ሰዎች መዳፉ ውስጥ ይወድቃሉ።
11 በልቡ እንዲህ ይላል፦ “አምላክ ረስቷል።+
ፊቱን አዙሯል።
ፈጽሞ ልብ አይልም።”+
ק [ኮፍ]
12 ይሖዋ ሆይ፣ ተነስ።+ አምላክ ሆይ፣ እጅህን አንሳ።+
ምስኪኖችን አትርሳ።+
13 ክፉው ሰው አምላክን ያቃለለው ለምንድን ነው?
በልቡ “ተጠያቂ አታደርገኝም” ይላል።
ר [ረሽ]
14 አንተ ግን ችግርንና መከራን ትመለከታለህ።
ደግሞም አይተህ እርምጃ ትወስዳለህ።+
ያልታደለው ሰለባ ወደ አንተ ይጮኻል፤+አንተ አባት ለሌለው ልጅ* ረዳቱ ነህ።+
ש [ሺን]
15 ክፉና መጥፎ የሆነውን ሰው ክንድ ስበር፤+ከዚያ በኋላ ክፋቱን በምትፈልግበት ጊዜጨርሶ አታገኘውም።
16 ይሖዋ ለዘላለም ንጉሥ ነው።+
ብሔራት ከምድር ጠፍተዋል።+
ת [ታው]
17 ይሖዋ ሆይ፣ የዋሆች የሚያቀርቡትን ልመና ግን ትሰማለህ።+
ልባቸውን ታጸናለህ፤+ ደግሞም ትኩረት ትሰጣቸዋለህ።+
18 በምድር ላይ ያለ ሟች የሆነ ሰው ከእንግዲህ እንዳያሸብራቸው፣+አባት ለሌለው ልጅና ለተደቆሱ ሰዎች ፍትሕ ታሰፍናለህ።+