መዝሙር 102:1-28
ጭቆና የደረሰበት ሰው ተስፋ በቆረጠና* ጭንቀቱን በይሖዋ ፊት ባፈሰሰ ጊዜ ያቀረበው ጸሎት።+
102 ይሖዋ ሆይ፣ ጸሎቴን ስማ፤+እርዳታ ለማግኘት የማሰማው ጩኸት ወደ አንተ ይድረስ።+
2 የሚያስጨንቅ ሁኔታ ባጋጠመኝ ጊዜ ፊትህን ከእኔ አትሰውር።+
ጆሮህን ወደ እኔ አዘንብል፤*ስጣራ ፈጥነህ መልስልኝ።+
3 የሕይወት ዘመኔ እንደ ጭስ እየበነነ ነው፤አጥንቶቼም እንደ ምድጃ ከስለዋል።+
4 እህል መብላት ረስቻለሁና፤ልቤ እንደ ሣር ጠውልጓል፤ ደርቋልም።+
5 እጅግ ከመቃተቴ የተነሳ+አጥንቶቼ ከቆዳዬ ጋር ተጣበቁ።+
6 የምድረ በዳ ሻላ* መሰልኩ፤በፍርስራሽ ክምር መካከል እንዳለች ጉጉት ሆንኩ።
7 እንቅልፍ አጥቼ አድራለሁ፤*በጣሪያ ላይ እንዳለች ብቸኛ ወፍ ሆንኩ።+
8 ጠላቶቼ ቀኑን ሙሉ ይሳለቁብኛል።+
የሚያፌዙብኝ ሰዎች ስሜን ለእርግማን ይጠቀሙበታል።
9 አመድን እንደ ምግብ እበላለሁና፤+የምጠጣውም ነገር ከእንባ ጋር ተቀላቅሏል፤+
10 ይህም የሆነው ከቁጣህና ከንዴትህ የተነሳ ነው፤እኔን ለመጣል ወደ ላይ አንስተኸኛልና።
11 የሕይወቴ ዘመን ፀሐይ ስትጠልቅ እንደሚጠፋ* ጥላ ነው፤+እኔም እንደ ሣር ጠወለግኩ።+
12 ይሖዋ ሆይ፣ አንተ ግን ለዘላለም ትኖራለህ፤+ዝናህም* ከትውልድ እስከ ትውልድ ይጸናል።+
13 በእርግጥ ትነሳለህ፤ ለጽዮንም ምሕረት ታሳያለህ፤+ለእሷ ሞገስህን የምታሳይበት ጊዜ ነውና፤+የተወሰነው ጊዜ ደርሷል።+
14 አገልጋዮችህ በድንጋዮቿ ደስ ይላቸዋልና፤+ለአፈሯም እንኳ ልዩ ፍቅር አላቸው።+
15 ብሔራት የይሖዋን ስም፣የምድር ነገሥታትም ሁሉ ክብርህን ይፈራሉ።+
16 ይሖዋ ጽዮንን ዳግመኛ ይገነባልና፤+በክብሩም ይገለጣል።+
17 የድሆችን ጸሎት በትኩረት ያዳምጣል፤+ጸሎታቸውን አይንቅም።+
18 ይህ የተጻፈው ለመጪው ትውልድ ነው፤+በመሆኑም ወደፊት የሚመጣው* ሕዝብ ያህን ያወድሳል።
19 ይሖዋ ከፍ ካለው ቅዱስ ስፍራው ወደ ታች ይመለከታልና፤+ከሰማይ ሆኖ ወደ ታች ምድርን ያያል፤
20 ይህም የእስረኛውን ሲቃ ለመስማት፣+ሞት የተፈረደባቸውንም ነፃ ለማውጣት ነው፤+
21 በመሆኑም የይሖዋ ስም በጽዮን፣ውዳሴውም በኢየሩሳሌም ይታወጃል፤+
22 ይህም የሚሆነው ሕዝቦችና መንግሥታትይሖዋን ለማገልገል አንድ ላይ በሚሰበሰቡበት ጊዜ ነው።+
23 ያለጊዜዬ ኃይል አሳጣኝ፤የሕይወት ዘመኔን አሳጠረ።
24 እኔም እንዲህ አልኩ፦“ከትውልድ እስከ ትውልድ የምትኖረው አምላኬ ሆይ፣+በሕይወት ዘመኔ እኩሌታ አታጥፋኝ።
25 አንተ ከብዙ ዘመናት በፊት የምድርን መሠረት ጣልክ፤ሰማያትም የእጆችህ ሥራ ናቸው።+
26 እነሱ ይጠፋሉ፤ አንተ ግን ትኖራለህ፤ሁሉም እንደ ልብስ ያረጃሉ።
እንደ ልብስ ትቀይራቸዋለህ፤ እነሱም ያልፋሉ።
27 አንተ ግን ያው ነህ፤ ዘመንህም ፍጻሜ የለውም።+
28 የአገልጋዮችህ ልጆች ያለስጋት ይኖራሉ፤ዘራቸውም በፊትህ ጸንቶ ይኖራል።”+