መዝሙር 105:1-45

  • ይሖዋ በታማኝነት ለሕዝቡ ያከናወናቸው ሥራዎች

    • አምላክ ቃል ኪዳኑን ያስታውሳል (8-10)

    • “የቀባኋቸውን አገልጋዮቼን አትንኩ” (15)

    • አምላክ ባሪያ በነበረው በዮሴፍ ተጠቀመ (17-22)

    • አምላክ በግብፅ ያከናወናቸው ተአምራት (23-36)

    • እስራኤል ከግብፅ ወጣ (37-39)

    • አምላክ ለአብርሃም የገባውን ቃል አስታወሰ (42)

105  ይሖዋን አመስግኑ፤+ ስሙን ጥሩ፤ሥራውን በሕዝቦች መካከል አስታውቁ!+   ለእሱ ዘምሩ፤ የውዳሴም መዝሙር ዘምሩለት፤አስደናቂ በሆኑት ሥራዎቹ ሁሉ ላይ አሰላስሉ።*+   በቅዱስ ስሙ ተኩራሩ።+ ይሖዋን የሚፈልጉ ሰዎች፣ ልባቸው ሐሴት ያድርግ።+   ይሖዋንና ብርታቱን ፈልጉ።+ ፊቱን ሁልጊዜ እሹ።   ያከናወናቸውን አስደናቂ ሥራዎች፣ተአምራቱንና የተናገረውን ፍርድ አስታውሱ፤+   እናንተ የአገልጋዩ የአብርሃም ዘሮች፣+እሱ የመረጣችሁ የያዕቆብ ልጆች፣+ ይህን አስታውሱ።   እሱ ይሖዋ አምላካችን ነው።+ ፍርዱ በመላው ምድር ላይ ነው።+   ቃል ኪዳኑን ለዘላለም፣የገባውን ቃል* እስከ ሺህ ትውልድ ያስታውሳል፤+   ከአብርሃም ጋር የገባውን ቃል ኪዳን፣+ለይስሐቅም በመሐላ የገባውን ቃል አይረሳም፤+ 10  ቃሉን ለያዕቆብ ድንጋጌ፣ለእስራኤልም ዘላቂ ቃል ኪዳን አድርጎ አቋቋመ፤ 11  “የከነአንን ምድርርስትህ አድርጌ እሰጥሃለሁ” አለ።+ 12  ይህን የተናገረው በቁጥር ጥቂት፣አዎ፣ በጣም ጥቂት በነበሩ ጊዜ ነው፤+ በምድሪቱም ላይ የባዕድ አገር ሰዎች ነበሩ።+ 13  እነሱም ከአንዱ ብሔር ወደ ሌላው ብሔር፣ከአንዱም መንግሥት ወደ ሌላው ሕዝብ ተንከራተቱ።+ 14  ማንም እንዲጨቁናቸው አልፈቀደም፤+ይልቁንም ለእነሱ ሲል ነገሥታትን ገሠጸ፤+ 15  “የቀባኋቸውን አገልጋዮቼን አትንኩ፤በነቢያቴም ላይ አንዳች ክፉ ነገር አታድርጉ” አላቸው።+ 16  በምድሪቱ ላይ ረሃብን ጠራ፤+የምግብ አቅርቦታቸው እንዲቋረጥ አደረገ።* 17  ባሪያ እንዲሆን የተሸጠውን ሰው፣ ዮሴፍንከእነሱ አስቀድሞ ላከው።+ 18  እግሮቹን በእግር ብረት አሰሩ፤*+አንገቱም ብረት ውስጥ ገባ፤* 19  የይሖዋ ቃል አጠራው፤ይህም የሆነው የተናገረው ቃል እስኪፈጸም ድረስ ነው።+ 20  ንጉሡ ልኮ አስፈታው፤+የሕዝቦቹም ገዢ ነፃ አወጣው። 21  የቤቱ ጌታ አድርጎ ሾመው፤የንብረቱ ሁሉ ገዢ አደረገው፤+ 22  ይህም ደስ ባሰኘው* መንገድ በመኳንንቱ ላይ እንዲሠለጥን፣*ሽማግሌዎቹንም ጥበብ እንዲያስተምር ነው።+ 23  ከዚያም እስራኤል ወደ ግብፅ መጣ፤+ያዕቆብም በካም ምድር የባዕድ አገር ሰው ሆኖ ኖረ። 24  አምላክ ሕዝቡ እየተባዛ እንዲሄድ አደረገ፤+ከጠላቶቻቸው ይበልጥ ኃያላን አደረጋቸው፤+ 25  ሕዝቡን ይጠሉ ዘንድ፣በአገልጋዮቹም ላይ ያሴሩ ዘንድ የጠላቶቻቸው ልብ እንዲለወጥ ፈቀደ።+ 26  አገልጋዩን ሙሴን፣+የመረጠውንም አሮንን ላከ።+ 27  እነሱም ምልክቶቹን በመካከላቸው፣ተአምራቱን በካም ምድር አደረጉ።+ 28  ጨለማን ላከ፤ ምድሪቱም ጨለመች፤+እነሱ በቃሉ ላይ አላመፁም። 29  ውኃዎቻቸውን ወደ ደም ለወጠ፤ዓሣዎቻቸውንም ገደለ።+ 30  ምድራቸው፣ የነገሥታታቸውም እልፍኞች እንኳ* ሳይቀሩበእንቁራሪቶች ተጥለቀለቁ።+ 31  ተናካሽ ዝንቦች እንዲወሯቸው፣ትንኞችም በግዛቶቻቸው ሁሉ እንዲርመሰመሱ አዘዘ።+ 32  በዝናባቸው ፋንታ በረዶ አወረደባቸው፤በምድራቸውም ላይ መብረቅ* ላከ።+ 33  ወይናቸውንና የበለስ ዛፋቸውን መታ፤በግዛታቸው ውስጥ ያሉትንም ዛፎች አወደመ። 34  አንበጦች፣ ስፍር ቁጥር የሌላቸው ኩብኩባዎችምእንዲወሯቸው አዘዘ።+ 35  እነሱ በአገሪቱ የሚገኘውን አትክልት ሁሉ በሉ፤የምድሪቱንም ምርት ፈጁ። 36  ከዚያም በአገራቸው ያሉትን በኩራት ሁሉ፣የፍሬያቸው* መጀመሪያ የሆኑትን መታ።+ 37  ሕዝቡ ብርና ወርቅ ይዞ እንዲወጣ አደረገ፤+ከነገዶቹም መካከል የተሰናከለ አልነበረም። 38  በወጡ ጊዜ ግብፅ ሐሴት አደረገ፤እስራኤላውያንን* እጅግ ፈርተዋቸው ነበርና።+ 39  እነሱን ለመሸፈን ደመናን ዘረጋ፤+ በሌሊትም ብርሃን እንዲሰጥ እሳትን ላከ።+ 40  ሥጋ እንዲሰጣቸው በጠየቁት ጊዜ ድርጭት ላከላቸው፤+ከሰማይም ምግብ እያወረደ ያጠግባቸው ነበር።+ 41  ዓለትን ሰነጠቀ፤ ውኃም ተንዶለዶለ፤+በበረሃ እንደ ወንዝ ፈሰሰ።+ 42  ለአገልጋዩ ለአብርሃም የገባውን ቅዱስ ቃል አስታውሷልና።+ 43  ስለዚህ ሕዝቡን በታላቅ ደስታ፣የተመረጡ አገልጋዮቹንም በእልልታ አወጣቸው።+ 44  የሌሎችን ብሔራት ምድር ሰጣቸው፤+እነሱም ሌሎች ሕዝቦች ለፍተው ያፈሩትን ወረሱ፤+ 45  ይህን ያደረገው ድንጋጌዎቹን እንዲጠብቁ፣+ሕጎቹንም እንዲያከብሩ ነው። ያህን አወድሱ!*

የግርጌ ማስታወሻ

“አስደናቂ ስለሆኑት ሥራዎቹ ሁሉ ተናገሩ” ማለትም ሊሆን ይችላል።
ቃል በቃል “ያዘዘውን ቃል።”
ቃል በቃል “እያንዳንዱን የዳቦ በትር ሰበረ።” ዳቦ ለማስቀመጥ የሚያገለግሉ በትሮችን ሊያመለክት ይችላል።
ቃል በቃል “አጎሳቆሉ።”
ወይም “ነፍሱ ብረት ውስጥ ገባች።”
ቃል በቃል “መኳንንቱን እንዲያስር።”
ወይም “ነፍሱን ደስ ባሰኘው።”
ወይም “ክፍሎች እንኳ።”
ወይም “የእሳት ነበልባል።”
ወይም “ዘር የመተካት ችሎታቸው።”
ቃል በቃል “እነሱን።”
ወይም “ሃሌሉያህ!” “ያህ” የይሖዋ ስም አጭር መጠሪያ ነው።