መዝሙር 108:1-13

  • በጠላት ላይ ድል ለመቀዳጀት የቀረበ ጸሎት

    • “የሰው ማዳን ከንቱ ነው” (12)

    • “አምላክ ኃይል ይሰጠናል” (13)

መዝሙር። የዳዊት ማህሌት። 108  አምላክ ሆይ፣ ልቤ ጽኑ ነው። በሁለንተናዬ እዘምራለሁ፤ ደግሞም አዜማለሁ።+   ባለ አውታር መሣሪያ ሆይ፣ አንተም በገና ሆይ፣+ ተነሱ። እኔም በማለዳ እነሳለሁ።   ይሖዋ ሆይ፣ በሕዝቦች መካከል አወድስሃለሁ፤በብሔራትም መካከል የውዳሴ መዝሙር እዘምርልሃለሁ።   ታማኝ ፍቅርህ ታላቅ ነውና፤ እንደ ሰማያት ከፍ ያለ ነው፤+ታማኝነትህም እስከ ደመናት ድረስ ነው።   አምላክ ሆይ፣ ከሰማያት በላይ ከፍ ከፍ በል፤ክብርህ በምድር ሁሉ ላይ ይሁን።+   የምትወዳቸው ሰዎች እንዲድኑበቀኝ እጅህ ታደገን፤ ደግሞም መልስ ስጠኝ።+   አምላክ በቅድስናው* እንዲህ ብሏል፦ “ሐሴት አደርጋለሁ፤ ሴኬምን ርስት አድርጌ እሰጣለሁ፤+የሱኮትንም ሸለቆ* አከፋፍላለሁ።+   ጊልያድም+ ሆነ ምናሴ የእኔ ናቸው፤ኤፍሬምም የራስ ቁሬ ነው፤*+ይሁዳ በትረ መንግሥቴ ነው።+   ሞዓብ መታጠቢያ ገንዳዬ ነው።+ በኤዶም ላይ ጫማዬን እጥላለሁ።+ በፍልስጤም ላይ በድል አድራጊነት እጮኻለሁ።”+ 10  ወደተመሸገችው ከተማ ማን ይወስደኛል? እስከ ኤዶም ድረስ ማን ይመራኛል?+ 11  አምላክ ሆይ፣ ገሸሽ ያደረግከን አንተ አይደለህም?አምላካችን ሆይ፣ ከሠራዊታችን ጋር አብረህ አትወጣም።+ 12  ከጭንቅ እንድንገላገል እርዳን፤+የሰው ማዳን ከንቱ ነውና።+ 13  አምላክ ኃይል ይሰጠናል፤+ጠላቶቻችንንም ይረጋግጣቸዋል።+

የግርጌ ማስታወሻ

“በቅዱስ ስፍራው” ማለትም ሊሆን ይችላል።
ወይም “ረባዳማ ሜዳ።”
ቃል በቃል “ለራሴ ምሽግ ነው።”