መዝሙር 110:1-7
የዳዊት መዝሙር። ማህሌት።
110 ይሖዋ ጌታዬን
“ጠላቶችህን ለእግርህ መርገጫ እስከማደርግልህ ድረስ+በቀኜ ተቀመጥ”+ አለው።
2 ይሖዋ የኃይልህን በትር ከጽዮን ይዘረጋል፤
“በጠላቶችህ መካከል በድል አድራጊነት ግዛ”*+ ይላል።
3 ወደ ጦርነት በምትዘምትበት ቀን*
ሕዝብህ በገዛ ፈቃዱ ራሱን ያቀርባል።በቅድስና ተውበህ ሳለ፣ ከንጋት ማህፀን እንደወጣ ጤዛ ያለ የወጣቶች ሠራዊት ከጎንህ ይሰለፋል።
4 ይሖዋ “እንደ መልከጼዴቅ፣+
አንተ ለዘላለም ካህን ነህ!” ሲል ምሏል፤+ደግሞም ሐሳቡን አይለውጥም።*
5 ይሖዋ በቀኝህ ይሆናል፤+በቁጣው ቀን ነገሥታትን ያደቃል።+
6 በብሔራት ላይ* የፍርድ እርምጃ ይወስዳል፤+ምድሪቱንም ሬሳ በሬሳ ያደርጋል።+
ሰፊ የሆነውን አገር* የሚገዛውን መሪ* ያደቀዋል።
7 እሱ* በመንገድ ዳር ካለው ጅረት ይጠጣል።
በመሆኑም ራሱን ቀና ያደርጋል።