መዝሙር 112:1-10

  • ጻድቅ ሰው ይሖዋን ይፈራል

    • “በልግስና የሚያበድር ሰው ይሳካለታል” (5)

    • “ጻድቅ ለዘላለም ሲታወስ ይኖራል” (6)

    • ለጋስ ለድሆች ይሰጣል (9)

112  ያህን አወድሱ!*+ א [አሌፍ] ይሖዋን የሚፈራና+ב [ቤት] ትእዛዛቱን እጅግ የሚወድ ሰው ደስተኛ ነው።+ ג [ጊሜል]   ዘሮቹ በምድር ላይ ኃያላን ይሆናሉ።ד [ዳሌት] ደግሞም የቅኖች ትውልድ ይባረካል።+ ה []   በቤቱ ሀብትና ንብረት አለ፤ו [ዋው] ጽድቁም ለዘላለም ይኖራል። ז [ዛየን]   ለቅኖች በጨለማ ውስጥ እንደ ብርሃን ያበራል።+ ח [ኼት] ሩኅሩኅና* መሐሪ+ እንዲሁም ጻድቅ ነው። ט [ቴት]   በልግስና የሚያበድር ሰው ይሳካለታል።+ י [ዮድ] ጉዳዩን በፍትሕ ያከናውናል። כ [ካፍ]   እሱ ፈጽሞ አይናወጥም።+ ל [ላሜድ] ጻድቅ ለዘላለም ሲታወስ ይኖራል።+ מ [ሜም]   ክፉ ወሬ አያስፈራውም።+ נ [ኑን] በይሖዋ ስለሚተማመን ልቡ ጽኑ ነው።+ ס [ሳሜኽ]   ልቡ አይናወጥም፤* አይፈራምም፤+ע [አይን] በመጨረሻም ጠላቶቹን በድል አድራጊነት ይመለከታል።+ פ []   በብዛት* አከፋፈለ፤ ለድሆችም ሰጠ።+ צ [ጻዴ] ጽድቁ ለዘላለም ይኖራል።+ ק [ኮፍ] የገዛ ብርታቱ* በክብር ከፍ ከፍ ይላል። ר [ረሽ] 10  ክፉ ሰው አይቶ ይበሳጫል። ש [ሺን] ጥርሱን ያፋጫል፤ ቀልጦም ይጠፋል። ת [ታው] የክፉዎች ምኞት ይከስማል።+

የግርጌ ማስታወሻ

ወይም “ሃሌሉያህ!” “ያህ” የይሖዋ ስም አጭር መጠሪያ ነው።
ወይም “ቸርና።”
ወይም “ቆራጥ ነው፤ ጽኑ ነው።”
ወይም “በልግስና።”
ቃል በቃል “የገዛ ቀንዱ።”