መዝሙር 114:1-8

  • እስራኤል ከግብፅ ወጣ

    • ባሕሩ ሸሸ (5)

    • ተራሮች እንደ አውራ በግ ዘለሉ (6)

    • ጠንካራውን ዓለት ወደ ውኃ ምንጮች ይለውጣል (8)

114  እስራኤል ከግብፅ ሲወጣ፣+የያዕቆብ ቤት ባዕድ ቋንቋ ከሚናገር ሕዝብ ተለይቶ ሲሄድ፣   ይሁዳ መቅደሱ፣*እስራኤልም ግዛቱ ሆነ።+   ባሕሩ ይህን አይቶ ሸሸ፤+ዮርዳኖስ ወደ ኋላ ተመለሰ።+   ተራሮች እንደ አውራ በግ፣ኮረብቶች እንደ ጠቦት ፈነጩ።+   አንተ ባሕር ሆይ፣ የሸሸኸው ምን ሆነህ ነው?+ ዮርዳኖስ ሆይ፣ ወደ ኋላ የተመለስከው ለምንድን ነው?+   ተራሮች ሆይ፣ እንደ አውራ በግ የዘለላችሁት፣እናንተ ኮረብቶች፣ እንደ ጠቦት የፈነጫችሁት ለምንድን ነው?   ምድር ሆይ፣ ከጌታ የተነሳ፣ከያዕቆብም አምላክ የተነሳ ተንቀጥቀጪ፤+   እሱ ዓለቱን ቄጠማ ወደሞላበት ኩሬ፣ጠንካራውንም ዓለት ወደ ውኃ ምንጮች ይለውጣል።+

የግርጌ ማስታወሻ

ወይም “ቅዱስ ስፍራው።”